ትላንት የተጀመረው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌስቲባልን በያለንበት ሆነን በፎቶም በቪዲዮም አይተነው ነበር።

በነገራችን ላይ ይሄ በርካታ አመታትን ያስቆጠረው አንጋፋ የፌስቲቫል ዝግጅት  ESFNA በሚል መጠሪያ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ባለፉት ሰሞናት ከፍተኛ የይገባኛል ውዝግብ እና ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ፤ ዛሬ ዳላስ ላይ የከተሙት ዋናውን ስያሜ ሲይዙ፤ በሼክ መሃመድ አላሙዲን የሚመሩት “ሃብታሞቹ” ደግሞ የፈጀውን ይፍጅ ብለው ESFNA የሚለው ላይ ONE የሚል ጨምረውበት የራሳቸውን ቡድን በማዋቀር ዲሲ ላይ ከትመው ነበር። (አክትመው ብል ይሻላል መሰለኝ… እንዴት? ማለት የጨዋ ደንቡ ነውና እንዴት ብለውኝ ይምጡ በአዲስ መስመር…)

ፌስቲባሉ በዳላስ እና በዲሲ እኩል ነበር የተጀመረው። በመጀመሪያ በዲሲ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ፎቶግራፍ በፌስ ቡክ ላይ ተለጥፎ ተመለከትኩ። ስታድየሙ ባዶ ከመሆኑ የተነሳ የሚከራይ ቤት ነበር የሚመስለው። እውነቱን ለመናገር አንዱ ተንኮለኛ ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት ሄዶ ባዶውን ስታድየም ፎቶ አንስቶ የለጠፈልን ነበር የመሰለኝ። ትንሽ እናጋነው ብንል፤ የዲሲ ስታድየም  ራቁቷን የቆመች አዕምሮዋ የተናወጠ ሰው መስላ ነበር።

ነጋዴው ሼክ መሃመድ አላሙዲን ረብጣ ዶላራቸውን አፍስሰው ስፖንሰር ያደረጉት ዝግጅት፤ እርግጥ ነው ትልቅ ስታድየም፣ ትልቅ ስፒከር እና ጮክ ብሎ የሚናገር ሰውዬ መግዛት እንደቻለ በቪዲዮ ላይ ተመልክተናል።  ነገር ግን ተመልካች መግዛት አልቻለም። (በነገራችን ላይ በቪዲዮው እንዳየሁት ከሆነ ስታድየሙ ሲያስተጋባ፤ “እንዴት ነው ነገሩ እዚህ ቦታ የክብር እንግዳዋ የገደል ማሚቶ ነች እንዴ…!?” ብዬ ጠይቄ መልስ አላገኘሁም!) አንዳንድ

ሽሟጣጮችም፤ “ወይ እንደ ግንቦት ሃያ ሰልፍ አበል  ቢሰጡን ሰብሰብ ብለን አንሄድ ነበር። እነርሱ ግን ወይ አበል የላቸው ወይ አመል የላቸው ግራ የገባ ነገር ሆነብን” ሲሉ የማሽሟጠጥ ግዴታቸውን ተወጥተዋል። (በቅንፍም እንደው ለሽሙጥ እንዲመች ተብሎ እንጂ በዲሲው ድግስ ላይ “ዜር ፎር” በሚመስል መልኩ ተንጠባጥበው የተገኙት ተዳሚዎች አበላቸውን “ላፍ” ያደረጉ አባሎች መሆናቸው ጭምጭምታ አለ!)

በተቃራኒው ደግሞ ዳላስ ከተማ፤ ዋናው የሰሜን አሜሪካ ባህልና ስፖርት ፌስቲበል አዘጋጆች በምስኪን ድምፅ “አትመልከቺ ሱፍ አትዬ መኪና” ብለው ጠርተው እውነትም በርካታ ታዳሚ በስታድየሙ ተገኝቷል።

በተመለከትኩት ቪዲዮላይ የቴዲ አፍሮ “ጥቁር ሰው” ሙዚቃ ደምቆ ሲዘፈን ህዝቡ ባንዲራ ይዞ “ጀዲካ” እያለ ሲያስነካው ተመልክቻሁ። አሁንም ትንሽ ላጋን እና ስታድየሙድምቀት በአዲስ አበባ የ97ቱን ሰልፍ ይመስል ነበር።

እኔ የምለው ግን እነ ሼኩ ምን ነካቸው? ምንስ ሳውድ አረቢያ ቢኖሩ ስለ ኢትዮጵያውያኑ ባህል እና ወግ እንዴት አያውቁም? የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ ብዙ ጊዜ ከምስኪኖች ጋር ነው የሚቆመው ብዙ ጊዜ ከገንዘብ ይልቅ ፍቅር ነው የሚገዛው ከጉልበተኛው ይልቅም ልቡ ለምስኪን ታደላለች…! ይሄንን አለመረዳት ልቦና ማጣት ነው። አረ ይተዉ ሼኩ ወደ ልቦናዎ ይመለሱ… አቶ አብነት ቆይ እያጠራቀምኩልዎ ነው ሌላ ቀን እንነጋገራለን!

የሆነው ሆኖ ትላንት ዲሲ ጭር ብላ ውላለች ይህንን የሰማችው ዳላስ “እኔ ጭር ልበልልሽ” ብላ ተቆርቋሪነቷን ገልፃላታለች አሉ። በዳላስ የከተመው ህዝብም “ዶሮ በጋን” ለሆኑት የዲሲ አነስተኛና ጥቃቅን ታዳሚዎች እና አዘጋጆች አንድ የድሮ ዘፈን እየዘፈኑላቸው ነው አሉ፤

“በላሽው አንጀቴን በላሽው ጭር ባለው ሜዳ ዲሲ ላይ ያለሽው”

ወዳጄ፤ እስቲ ወዳጅነታችንን ያጠንክረው… እስቲ ሰላምና ፍቅሩን ያምጣልን… እስቲ ልዩነታችንን ያጥብብልን!

አሜን አሜን አሜን…!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

13 responses »

 1. ሄሌሌ ሃንባቤ says:

  ሚስኪን የዲሲ ታዳሚዎች ሆይ! ተዉ ተመለሱ ይሻላችሗል። ከሰፊዉ ህዝብ ተለይታችሁ የሚኖራችሁ ደስታ ያለ አይመስለኝም።
  በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ፣
  ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ
  እልም ካለዉ ገደል ገብተህ ቀረህ ወይ።
  ከላይ የተጠቀሰዉ ግጥም እንደናንተ ላሉ ተወናባጅ ታዳሚዎች ነዉ የተገጠመዉ ነገሩ ከገባችሁ ማለቴ ነዉ። ለማንኛዉም እኔ ለእናንተና ለሼክ አላሙዲን የመረጥኩላችሁ (ነፍሱን ይማረዉና) የታላቁን አርቲስት የጥላሁን ገሰሰን ዘፈን ነዉ። መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ!!

  http://www.myspace.com/music/player?sid=8168703&ac=now

 2. Hundanol says:

  nice Abe, But it is not Al Mouhdi that is sponsoring the Dc festival. TPLF is investing the money by the name of Alamouhdi. He is simply too greedy to do that.

 3. Tikidem says:

  hi, Abe, I appreciate you for your writing way, it is easy and precise. when I read your article , Always, I laughed for one hour, so, my office friend asked me, but how i explain, He didn’t understand or happy.

 4. Kulich says:

  Correction: The name of the group sponsored by Al Amoudi is AESAONE not ESFNAONE.

 5. Kulich says:

  Al Amoudi is adding fuel to the division of Ethiopians. I am not sure if he is doing this deliberately or not. I heard that people like Abinet are the real players of this nonsense. If I were him I would not give a penny for a group whose main aim is amassing money by creating a fake reason to split. Shame on you Al Amoudi!!!!

 6. NETSANET SOLOMON says:

  ABE IF YOU BELIEVE OR NOT HALF OF THE SOCCER PLAYERS ARE SOMALIANS. MY SOMALIAN COLLEGES WENT DC LAST SATURDAY. THEY TOLD ME THEIR COACH TOLD THEM THEY MUST BE SAY ”WE ARE ETHIOPIANS”. AND THERE IS NO WAY TO SPEECH THEIR LANGUAGE.
  THAT IS DC TOURNAMENT.

 7. በለው! says:

  *******************************************
  “በላሽው አንጀቴን በላሽው
  ጭር ባለው ሜዳ ዲሲ ላይ ያለሽው!”
  የምትመጡ መስሎን መንገዱን ብናየው
  ያልጠራነው ሆነ የሚመላለሰው
  አትላንታ ከዲሲ ከቶ እንዲህ ቅርብ ነው?
  ሽር ጉዱ በዝቶ ስንቱን ቀባጥረነው
  የህዝባችን ንብረት ሀብታም የዘረፈው
  አጨብጭበን ቀረን ሌላ ሀብታም በላው!!
  አባይም ሊደፈር ስቆ እያለፈ ነው
  ሀገርም ሲደፈር ትዕግስት ተደርጎ ነው
  ሕዘብ ግን ሲደፈር ምላሹ ይሄ ነው ።
  ይህ የማሳያው ነው ይቀጥላል በለው!።

 8. meretwork says:

  Hi Abe!! always I appreciat you when I read your article I began to loughed the holl day! Thank you Abe agen!! Ante betam gobez , ewunetegea fikr nhe ! berta gezew dersoale! ye birf Arebega ,warriors ,you are always to tell about the truth!!gene Asofariwoch- Hodamoch ke MAMA ETHIOPIA YEWUTA!!! Abe God bless you and keep you!!!

 9. Demelash says:

  Hi Abe, I like your articles which comes out with different hot issues. Do you know that Shek Al Amudi is homosexual. not strict but I think he prefer to sleep with men than women. I heard that he had some crashes with some known Ethiopian Singers and some officials.
  The other point Have you read this week REPORTER, talk about the fruit of Ethiopian Education, graduates are working in coble stone project. I hope you have something to say about it. We did not go to Universities to be dingay terabi or our new Universities train their students like their stone head instructors to be stone head.

 10. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  legbachwe ena lerdu yalflgu swech mechresachwe bado bota laye megte nwe .bado bota mehinm yelalbet .lek end dc aynet.

 11. በለው! says:

  “የኢትየጵያ ገበሬዎች በዲሲ ከተማ ለሚገኙ ድብርት ለያዛቸው ዲያስፖራ የወያኔ ደጋፊዎች ከ ፪ሚሊ በላይ የፈጀ ዝግጅትታዋቂ አሜሪካን ዘፋኞችንና ወዶ ገባ’ የኢትዮጵያ ጥቃቅንና አነስተኛ’ ዳንኪረኞቸን ቀጥረው አዝናኑ’ “የዜናው ምንጭ http://www.ethiotube.net/video/20145/Mimi-Sibhatu-Zami-FM-Radio-ቢኒያም ከበደ ኢትዮ ፈርስት፣ዮሴፍ ግዛው ከአነንድ ኢትየጵያ ሬዲዮ፣ በሀገር ፍቅር፣በፅናት ታጅበው (ብሪቱ)
  “እናንት ለሆዳችሁ ያደራችሁ ባፋችሁ ወሬ የምትቆሉ በምላሳችሁ ቂጣ የምትገለበጡ ድብርተኖች ሆይ ! ጤፋችንን በላችሁ፣ ቡናችንን ጫናችሁ, መሬታችንንም አስነጠቃችሁ ,ቅመም ሳየቀር ከሾላ ገበያ ከእኛው እኩል ትሸምታላችሁ,እዚህም ብትመጡም ቦታ የላችሁ ፣ባላችሁበትም ካብ አይገባ ድንጋይ ለመጨፈር እነጂ ቁም ነገር የላችሁም፣መጥታችሁም ቦታ ማጣበብ፣ ሃይማኖት, ባሕል ቋንቋ በማጥፋት ሱሪአችሁን አንዠርግጋችሁ መሽመድምድ፤ እምብርታችሁን እያሳያችሁ,አጉል ግዳይ ባለሎቲ ሆናችሁ፣ ጭራቅ በገላችሁ አስቀርፃችሁ መቼም ገበሬው ያልሰራው ያላስተማራችሁ የለም የዛሬ የእናንተ(ታቱ) ነበር እኮ የክርስትና ሥም እንፅፍበት ነበር ከጥንቱ፣ በቅናሽ የአውሮፕላን ትኬት ተጋፍታችሁ መጣችሁ አሉ። በዝጉብኝ ቤት ለመሞላፈጥ፣ ለቀራችሁት መሄጃ ለሌላችሁ እኛም አዝነን ተቆጭተን በአላሙዲን በኩል ፣ በአብነት አጋፋሪው መሪነት በተላዩ ሆድ አደር አጫፋሪዎች ይቺን ወጪ ልከንላችሗል ተዘናኑ አትደበሩ ያንን የወያኔ ‘አምባሻው’ ያለበትን ባንዲራ እንዳትይዙ በጥቁር ሰው ሥም አደራ አደራ!! ይሁን ቃል ይከበር ቅዱስ ጊዮርጊስን በነጭ ፈርስ ዳላስ ልከነዋል ለእናንተ ብዙ አህዮች ስላሏችሁ ነው ጠልተናችሁ አደለም በለው!በድሃው ሕዝብ ገንዘብ ተዝናኑ ተበራገዱ ሕፃናት የሚልሱት የሚቀምሱት የለም!!!!!!

 12. ethio boy says:

  They will pay per dime and bring fans from Ethiopia next year cause they get good lesson this year. ha ha ha…

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s