ድሮ ድሮ አሉ የሰው ልጆች ቋንቋ ሁሉ አንድ ነበር። ታድያ ከእለታት በአንዱ ቀን ትልቅ ግንብ ገንብተው ፈጣሪያቸው ያለበት ሰባተኛው ሰማይ ላይ ደርሰው ምን እያደረገ እንደሆን ሊሰልሉት አሴሩ።

የሀሳባቸውን ለመሙላትም፤ አንድም የሰው ልጅ ሳይቀር ተሰባስበው በዚህ እኩይ ስራ ላይ ተጠመዱ። እግዜርም ይህ የማይሆን የቂል ሀሳባቸው እንደማይሳካ ያውቃልና፤ በሌሎች መልካም ስራዎች ላይ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ እንዲሁም በዚህ የተነሳ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመታደግ ብሎ ይህንን ስራ ሊያቋርጥባቸው ፈለገ። ከዛም ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ከዛስ…?  ከዛማ አንዱ ብሎኬት አምጣ ሲል ውሃ ሲያቀብለው፣ ሙገር ሲሚንቶን አቀብለኝ ሲል የቀበና አሸዋ ሲያመጣ ግንቡ በየት በኩል ይግባቡ በየት በኩልስ ይገንቡ!? ሀሳባቸው ከንቱ ሆኖ ቀረ።

ይህ ታሪክ አፈታሪክ ይሁን ሀይማኖታዊ ታሪክ እንጃ፤ ግና ከድሮም ጀምሮ ስንሰማው ኖረናል። ንግግራችን እና ቋንቋችን ለመልካም ካልሆነ ቢደበላለቅ በስንት ጣዕሙ! የሚል አንኳር ሃሳብም ይዟል። እውነትም አለው።

በዛ ሰሞን “ስካይፕ እና የመሳሰሉት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂዎች በኢትዮጵያ ምድር መጠቀም ሊያስቀጣ ነው።” ተብለን፤ “አይይይ… እንግዲህማ ምን ቀረ…? ከዚህ ቀጥሎ ህልማችንንም ቁዘማችንንም ፀሎታችንንም በአዋጅ የምንቀማበት ጊዜ ደረሰ አይደለምን!?”  ብለን እጅግ አድርገን ስናማርር ድንገት ከመንግስት ባለስልጣናት አንዱ ቤቴሌቪዥናችን ብቅ ብለው “ስካይፕም ሆነ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በአዋጅ ሊከለክሉ ነው የተባለው በሬ ወለደ ወሬ ነው” ብለው ተስፋ ሰጥተውን ነበር።

በነጋታው ደግሞ ሌላው ባለስልጣን ተነስተው፤ “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና በደህንነት ስጋት የእኛን ኪሎ የሚቀንሱ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ጥርቅም አድርገን እንዘጋለን ምን ታመጣላችሁ!?” አይነት ንግግር መናገራቸውን ሰማን!

እኔ የምለው አቶ ሽመልስ፤ የመንግስት ቃል አቃባይ ሆነው ሳለ ለምን ቃላባይ ሲያደርጉዎት ዝም ይላሉ!? እርሶ ያቀበሉት ቃል በነጋታው “ውሸቱን ነው አትስሙት!” ሲባሉ ጎረቤትዎስ፣ ለቤተሰብዎስ፣ ለባንኮኒ ጓደኞችዎስ ምን ስም ያሰጥዎታል? እንዴ ምንም ቢሆን ሁለት ፀጉር አብቀለዋልኮ… የማንም ማላገጫ ሲሆኑማ ዝም አይበሉ!? እውነቴን ነው የምልዎ እኔ ለርሶ በመቆርቆር ነው የምናገረው…! ከዚህ በኋላ፤ “ይህንን ቃል አቀብል” ሲባሉ “መጀመሪያ እውነት መሆኑን ማሉልኝና” በሉዋቸው እንጂ ዝም ብለውማ አይመኑ! እንዴነችና ስልጣኑ ባፍንጫዎ ይውጣ እንጂ የማንም መጫወቻማ አይሆኑም…!

እኔ የምለው አቶ በረከት፤ እኛማ እኮ እርሳቸውን አምነን ለስንት ወዳጆቻችን “ስካይፕ አልተከለከለም!” ብለን ነገርን መሰልዎ…!? ለወደፊቱም ቢሆን አቶ ሽመልስ የሚናገሩትን ለማረጋገጥ እርስዎ ጋር እንድንደውል ስልክዎን ቢሰጡን ደስ ይለኛል።

እዝችው ጋ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎትማ… አቶ ሽመልስ ባለፈው ጊዜ “ስካይፕ አይከለከልም” ብለው የዋሹን እለት አያይዘውም ስለ አቶ መለስ ጤና ነግረውን ነበር። “እኛ በአደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክስት ግርጥት ብለው ተመልክተናቸው እግዜር ይማራቸው እያልን እየፀለይን ነው አሁንስ ሻል አላቸው ወይ?” ብለን ብንጠይቃቸው፤ እርሳቸው ሆዬ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሙሉ ጤንነት ላይ ናቸው!” ብለው ነግረውናል። አሁን ሳስበው ግን ስካይፕ አይከለከልም ብለው እንደዋሹን ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ጤና አስመልክቶ የነገሩንን ለማመን ተቸግረናል። እና እርስዎ ቢነግሩን ደስ ይለናል! አለበለዛ ግን ህዝቡ፤ የአቶ ሽመልስን ንግግር ተቃራኒ ትርጉም በመውስድ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣር ተይዘዋል በቅርቡም ቀብር ሊሆን ይችላል!” ብሎ ቢያስብ እኔ የለሁበትም።

እኔ የምለው ወዳጄ፤ ባለስልጣኖቻችን እንደምን ያለ ተንኮል አስበው ይሆን ቋንቋቸው እንዲህ የተደበላለቀባቸው!?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

7 responses »

  1. Fibus Niggli says:

    በጣም ያስቃል አቤ ግሩም አቀራረብ ጉዳቸውን በደንብ አድርገህ ነው ያወጣሐው!

  2. Ermi says:

    now it gets really confusing … you mean ato shimeles word is not true … i don kw wt to do any more … abe please post a link … on what bereket semon said about skype … i will be waiting

  3. ABDUL says:

    እኔ የምለው አቶ ሽመልስ፤ የመንግስት ቃል አቃባይ ሆነው ሳለ ለምን ቃላባይ ሲያደርጉዎት ዝም ይላሉ!? እርሶ ያቀበሉት ቃል በነጋታው “ውሸቱን ነው አትስሙት!” ሲባሉ ጎረቤትዎስ፣ ለቤተሰብዎስ፣ ለባንኮኒ ጓደኞችዎስ ምን ስም ያሰጥዎታል

  4. በለው! says:

    …..የራስን ዕድል በራስ የመወሰን “ልዩነታችን ውበታችን”
    * ከዛም ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ከዛስ…? ከዛማ አንዱ ብሎኬት አምጣ ሲል ውሃ ሲያቀብለው፣ ሙገር ሲሚንቶን አቀብለኝ ሲል የቀበና አሸዋ ሲያመጣ ግንቡ በየት በኩል ይግባቡ በየት በኩልስ ይገንቡ!? ሀሳባቸው ከንቱ ሆኖ ቀረ።

    አፈ ታሪክ ዕውን ሲሆን…
    በዛ ሰሞን “ስካይፕ እና የመሳሰሉት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂዎች በኢትዮጵያ ምድር መጠቀም ሊያስቀጣ ነው።” ተብለን፤
    ፩) ከመንግስት ባለስልጣናት አቶ ሽመል ከማል በቴሌቪዥናችን ብቅ ብለው “ስካይፕም ሆነ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በአዋጅ ሊከለክሉ ነው የተባለው በሬ ወለደ ወሬ ነው” ብለው ተስፋ ሰጥተውን ነበር። እኛማ እኮ እርሳቸውን አምነን ለስንት ወዳጆቻችን “ስካይፕ አልተከለከለም!” ብለን ነገርን መሰልዎ…!?ለጊዜው ያልተከለከለው እስካይ (ሰማይ) ብቻ ነው!።

    ፪) በነጋታው ደግሞ አቶ በረከት ስምዎን ተነስተው፤ “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና በደህንነት ስጋት የእኛን ኪሎ የሚቀንሱ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ጥርቅም አድርገን እንዘጋለን ምን ታመጣላችሁ!?” አይነት ንግግር መናገራቸውን ሰማን!
    እኔ የምለው ወዳጄ፤ ባለስልጣኖቻችን እንደምን ያለ ተንኮል አስበው ይሆን ቋንቋቸው እንዲህ የተደበላለቀባቸው!?

    – በእሳት የተፈተነና በመጠጥ የተፈተነ አንድ አደለም … ለመመሳሰል ሲባል መነፅር ማድረግ ማውለቅ ይኖራል። ብዙ ቦታ ብሔሮች (ክልሎች) ሞቅ እነዲላቸው እነዲፈነድቁ ያህል አንዴ ከማልን ሌላ ጊዜ ሬዲዋንን ብቅ ማድረግ ከመፎገር ያድናል። ሁለቱንም በደንብ አዳምጡ ፸ከመቶ የጠቅላይ ሚ/ኒስትሩን፣ ቃል,አቀማመጥ,ዓረፍተ ነገር (እንደወረደ) ይጠቀማሉ። አደጋው የሚጠቀሙበትን ቦታ ይሳሳታሉ በዚህም በማግስቱ እርማት ይደረግበታል።ለዚህም የሚቀመጡ ሳይሆን የሚያልፉ ወዶ ገቦችን በቴሌቪዥን መሰኮት ቶሎ ቶሎ ታያላችሁ።ጎንደሬው እንግሊዘኛ ሲቀድመው ስታዩ ይብላኝ ለክልላችሁ እና ለባንዲራችሁ እንዴትስ ትግባቡ በየትስ በኩል ትገነቡ መጠኑን አልቻላችሁ ስታደበላልቁት ሲቀጥን ሲፈርስ አዘንን ።
    ቋንቋውም ለመተማመን, አብሮ ለመኖር, አብሮ ሰርቶ ለማደግ አገዳችሁ ሁሌም ታለቅሳላችሁ እንዴትና ማን ይረዳችሁ??

  5. ሄሌሌ ሃንባቤ says:

    ወያኔዎች አንድን ሰዉ ቁልፍ ቦታ ላይ ለማስቀመጥ ሲፈልጉ ግለሰቡ እዉነትን ሽምጥጥ አድርጎ የሚክድ መሆን አለመሆኑን በቃለ መጠይቅ ይገመግሙታል። እዉነቱን ሽምጥጥ አድርጎ ከካደ ይህ ሰዉ ወደ ፊት ቢያዝም እኛን አያጋልጥም ብለዉ እንደሚያምኑ ቅርብነት በዘርም ሆነ በእምነት ከወያኔዎች ጋር ያለዉ ግለሰብ ሲናገር ጓደኛዬ ሰምቶ ጉድ መጺዉ ብሎ ነገረኝ። የጥያቄዎቹ መልሶች “እዉነት” ወይም “ዉሸት” ማለት ብቻ ነዉ። ጥያቄዎቹም እነዚህን ይመስላሉ፤ “እንቁላል የጓሮ አትክልት ነዉ”፣ “ዶሮ የጋማ ከብት ነዉ”፣ “በሬ ወላድ እንሰሳ ነዉ” ። የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ “እዉነት” ብሎ የመለሰ ግለሰብ ከፍተኛ ስልጣን የሰጠዋል። አቶ ሺመልስም ቢሆኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ወያኔዎች የሚፈልጉትን መልስ ባይመልሱላቸዉ ኖሮ አሁን የያዙትን ቁልፍ የመንግስት ስልጣን ባልያዙ ነበር ብዬ አምናለሁ። በእንግሊዝኛ ቋንቋ compulsive liar እየተባለ የሚታወቀዉ “የግዴታ ቀጣፊ” የሆነ ግለሰብ እንደ አቃቂ ጣቃ መቀደድና ቆሞ የሚሄድ ዉሸት መዋሸት ሙያዬ ብሎ የተያያዘ ፍጥረት ነዉ። ህሊናና ስነ ምግባር የጎደለዉ ቀጣፊ ለሆዱ ያደረ ስለሆነ ነገ አቶ ሺመልስ ከማል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቢሞቱም እንኳ ሞታቸዉን እንደ አጼ ምኒልክ ሞት ለሰባት አመት እየዋሸን በስልጣን ላይ መቆየት እንችላለን ብሎ ለወያኔዎች ከመናገር ወደ ሗላ ይላል ብዬ ለመናገር እጅግ ያዳግተኛል። አቶ ሺመልስ ከማል “እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነዉ” የሚለዉን ተረት አምኜ የተቀበልኩ ስለሆነ እናንተም ደግሞ እንደ እኔ እመኑ እያሉ ሳይሰብኩ አይቀሩም ብዬ እገምታለሁ። ቋንቋ እንኳ እንደ ገንዘብ የሚቸግራቸዉ አይመስሉም።

  6. meretwork says:

    I have to say” too this man” O , God, do deliver my soul from false lips,” From the tricky tongue” what will one give to you, and what will one add to you, o you tricky tongue? Psa..120-2,3,

  7. በለው! says:

    “የዓሳ ሽታ ከአናቱ” የዚህ ቡድን አባል ለመሆን ቀጣፊ ዋሾ መሆን እነጂ ሌላ መመዘኛ የለውም ለመሆኑ ሰውዬው የእድገት ተሞክሮ ሊያካፍሉ እንደ አበጡ ሄደው የሚቃረም ጠፍቶ ተንፍሰው አቀርቅረው ተመለሱ…

    ቀድሞውን ሰው በሰውነቱም መታወቅ መከበር ይገባዋል መሠረታዊ ፍላጎቱ ያልተሟላ ህዝብ በአለም ቁጥር ማብዣ እንዲሆን የተፈጠረ “ብዙና ተባዙ መሬትንም ሙሏት…” የተባለ እንጂ “መሬትንም ተጠቀሙባት …) “የሚለው ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተነፍጎ ለጥቂቶች ብቻ የተፈቀደ መሆኑ በጣም ያሳዝናል። በአብዛኛው ድሀ ሕዝብ ሲለመንበት በተስፋ ሲያድር ጥቂቶች በልተው በተፉት አደግን ተመነደግን የልመና ሥልትን እየቀያየሩ ከሀገር- ሀገር, ከአህጉር- አህጉር ከቦታ-ቦታ እየተዘዋወሩ የሚደረግ አላስፈላጊ ወጪ እራሱ ቢጠራቀም ብዙ ለውጥ ያመጣ ነበር። ስለ አየር መበከል ይወራል የአለም መንግስታት ውሎ አዳራቸው አውሮፕላን ላይ ነው፣ የጃቢው፣ የጋዜጠኛው፣ የሆቴሉ፣ የከተማ ጥበቃው፣…እና ሌሎችም ወጪዎች ሁሉ ታሳቢ መሆን አለባቸው ለማናቸውም..
    ጠ/ሚ (ለገሠ)መለሰ “ከወሬና ጉራ በቀር ለምነንም ያመጣነው ነገር የለም ዞሮ ዘሮ ሐሳቡ ጥሩ ነበር ማሰሪያው ገንዘብ ነው ያደጉም ሀገራት ገንዘብ የላቸውም”??እናንተ ስታድጉ እንሱ ሲድኸዩ ከእናንተ የዕድገታችሁን ተሞክሮ ለመቅሰም ለምነው ሲጋበዟችሁ ስትቀሳፍቱ አልነበረምን? አይ አቶ መለስ እግዝሐብሔር እውነትን ያናግርዎ ለሰሩትም፣ለሚሰሩትም፣ሊሰሩ ላሰቡት እና ለህመምዎ ሕዘቡ ከሚያማርር ይማርዎ! አኛስ ሁልግዜ የምንላችሁ ይህንኑ አደለም!?
    ሀገር ከመትዞሩ አንገታችሁን አዟዙሩ እርስ በእርሳችሁ ተወነባብዳችሁ ሕዘቡን አታወናብዱ ተግባቡ በለው!
    http://www.ethiotube.net/video/20592/PM-Meles-Zenawi-talks-about-his-trip-to-G20-

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s