ይህ ፎቶግራፍ የተወሰደው “የበፍቄ አለም” ከተባለው ከወዳጃችን በፍቃዱ ብሎግ ነው። ፍቄ ምስጋናህን እንካ…!

ታድያስ አቶ መለስ ዛሬ እንኳ ልፅፍልዎ አላሰብኩም ነበር። አንድ የሚያበሳጭ ዜና አንብቤ እርሱን ልነግርዎ፣ እግረ መንገዴንም እግዜር ይማርዎ ልበልዎ ብዬ ነው፤

ሰሞኑን ባለፈው በምርጫ ዘጠና ሰባት ግዜ የታየብዎ አይነት ህመም ድጋሚ አገርሽቶብዎ ቤልጄም ብራሰልስ ሊታከሙ እንደሄዱ ሰማሁ። በልቤም እግዜር ይማራቸው ስል አሰብኩ። ነገር ግን በአገሬ መሬት በእርስዎ ቆራጥ አመራር እና በድርጅታችን ፈፃሚነት የሚከናወነውን ነገር ሳይ፤ እግዜር ይማራቸው ማለቴን እግዜሩ ቢሰማ “ተው… በስራዬ አትግባብኝ” ብሎ የሚገስፀኝ መሰለኝ! እንዴት ካሉኝ ለዚህ የሚሆን አንድ ማሳያ ከወደ ስር አቀርባለሁ። ከቸኮሉም ሌላውን ዘለው የመጨረሻውን አንቀፅ ማንበብ ይችላሉ። (ግን የት ይሄዳሉ… ለራስዎ በእግዜር እጅ ተይዘው!)

የህመምዎ ነገር ድሮም የተፈራ ነው። እንኳንስ በአበበ ገላው ላይ ያደረው መንፈስ እንደዛ ቀልቦን ገፎት ይቅርና እንዲሁም በየ ግምገማው በሚደረግ እሰጣ ገባ በተለይ ህውሃት ለሁለት ከመሰንጠቋ በፊት በነበሩት ከበድ ከበድ ያሉ ግምገማዎች እነ አቶ ስዬ እና አቶ ገብሩ እንዲሁም ሌሎች ዛሬ ከድርጅቱ የወጡ ግለሰቦች በሚያደርሱብዎ ግምገማ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ነፍስዎን ስተው ነበር እየተባለ ሲወራ ሰምቻለሁ። በርግጥ እውነት መሆኑን ምሎ ያረጋገጠልኝ ባይኖርም “እሳት ሳይኖር ጭስ አይፈጠርም” በሚለው አባባል መሰረት ነገሩ እውነት ሊሆን እንደሚችል ጠርጥሪያለሁ።

ያኔ በዘጠና ሰባቱም ምርጫም አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ለአደገኛ የእራስ መቃወስ ህመም ተዳርጋችሁ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናገረዋል። እንደውም የዛን ጊዜ ሁሉም በየጎጆው “አነዚህ ሰዎች አመራራቸው የተቃወሰው ለካስ ወደው አይደለም” ብሎ ከንፈሩን መጧል። የአቶ በረከትን በሚመለከት በቅርቡ መፅሀፋቸው የተመረቀ ጊዜ ሼክ ማህመድ አላሙዲን “እያንጠለጠልኩ ወስጄ አሳክመው ነበር” ብለው ነግረውናል። እንግዲህ የእርስዎ መፅሀፍ ደግሞ ሲታተም ማን እያንጠለጠለ ወስዶ ሲያሳክምዎ እንደነበር እንሰማ ይሆናል።

እኔ የምልዎ የአቶ በረከት ስምዖንን መፅሀፍ አይተው እርማት እንደሰጡ ሲነገር ሰምቼ ነበር… እውነት እርሶ አይተውት ነው ያሁሉ የሚያስተዛዝብ ነገር የተገኘበት…? እውነትም ሁላችሁም ታማችኋል ማለት ነው። እና እግዜር ይማራችሁ ብዬ እመርቃለሁ…! ግን አይመስለኝም። ለምን አይመስለኝም…?
ለምሳሌ ዛሬ እንዴት ያለ ኮሚክ ዜና ሰማሁኝ መሰልዎ…! “ዘ ዲክታተርስ” የሚለው የፈረንጅ ፊንም በኢትዮጵያ ሲኒማ ቤቶች እንዳይታይ ታገደ የሚል።

እውነቴን ነው የምልዎ ይሄ በጣም አሳዛኝ ዜና ነው።

ወይ ካድሬዎችዎ መንግስታችንን በጣም እያስፎገሩት ነው። ወይም ደግሞ እርስዎ ራስዎ ለይቶልዎታል።  እስቲ አሁን “ዘ ዲክታተር” ፊልምን ማገድ ማለት ምን ማለት ነው? እርግጥ ነው ሌላ ሰው ፊልሙን ከእርስዎ እና ከመንግስታችን ጋር ማመሳሰል ከጀመረ ቆይቷል። ነገር ግን እራሳችን በራሳችን “ፊልሙ እኛን የሚነካ ነው” ብለን ማገዳችን በእውነቱ ምህረት የማያሰጥ ወንጀል ነው። እንዲህ ስልዎ ለፊልም ተመልካቹ ተቆርቁሬ አይደለም። ከፈለጉ ልማልልዎ! ለድርጅታችን ተጨንቄ ነው። ይህ ፊልም እንዲታገድ ሲደረግ ትዕዛዝ ያስተላለፈው ግለሰብ “ድርጅታችንን እና እርስዎ መሪያችንን ሙልጭ አድርጎ ሰድቧል በድሏልም።” ብዬ ልናገር ነበር፤ ነገር ግን በአገሪቷ ካለ እርስዎ ቀጭን ትዕዛዝ የሚከናወን ነገር እንደሌለ ትዝ ሲለኝ እንደሚከተለው አሰብኩ፤

የተሰዉ ታጋዮች “አምባገነንነትን ለማጥፋት ነው የተሰዉት!” እያልን ለበርካቶች እንዳላስተማርን ዛሬ “ይህ ፊልም እኛን ይመለከታል” በሚል ስናግድ ራሳችንን በራሳችን “አምባ ገነነን ነን!” ብሎ የማወጅ ያህል ነው።  እኔ ግን የምልዎ እሺ ድርጅቷን ተዋት፣ ታጋዮቹንም እርሷቸው ግን የተሰዉ ታጋዮች አምላክ፤ የላይኛው እግዜር  ያን ሁሉ መስዋትነት ውሃ ሲያስበሉት አይቶ ምህረት የሚያደርግልዎ ይመስልዎታል…? እኔ ግን አይመስለኝም። ለማንኛውም እግዜር ይማርዎ!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

9 responses »

  1. ጦቢያ says:

    Man alebigninetachew kelik alefe ma neber ” zim yalen neger eferalehu ” yalew

    yehizbu zimita yazenagachew yimesilegnal

  2. yosef says:

    አቤ እኔም ከስንት ጊዜ ብኋላ ነው የመልስ ምቴን የምሰጥህ ምን ነው እስካሁን የት ነበርክ ትልኝ ይሆን? ጥያቄውን መነሳቱ አይቀርም ብየ ነው የምትሞነጫጭረው ነገር ሳላየው ቀሪቼ ደግሞ እንዳይመስልህ ብጨምቀው ጠብ የሚል ነገር ስላላገኘሁለት’ንጂ(ሁሉ መጣጥፍህ ትርኪመርኪ ነበር) የዛሬም’ኮ ምንም ፍረ ነገር የለውም ግን እንደው ሰው ነህና ተስፋ የሚሉት ትልቅ እንዳታጣ ብየ ነው በተርፈ ምን አለ አንተን የሚመስል ብጤህን ብትፈልግ ለነገሩ አንዳንተ በዚ ምድር የተፈጠረ አይመስልኝም

    • ሰላም ዮሴፍ በአቤ ፋንታ እኔ እንኳን ደህና መጣህ ልበልህ። ያው መቼም እኔን ታውቀኛለህ ዝም ብዬ አልተችህም። ደም ያለህ የኢህአዴግ ወዳጅ መሆንህን ስለማውቅ ለምትወደው ድርጅትህ እንዲህ ዘብ መቆምህን አደንቃለሁ። ነገር ግን እውነቱን ንገረኝ ካልክ የዛሬው አስተያየትህ ምንም ፍሬ የሌለው ሆኖ አግኝቼዋለሁ። አቤ ቢያንስ አንድ ፍሬ ያለው ተናግሯል። “ዘ ዲክታተር የተሰነውን ፊልም ለምን እንዲታገድ አደረጋችሁት? የሄ ራስን ዲክታት ብሎ የመስደብ ያህል አይደለምን!?” ብሎ ታማሚውን ጠቅላይ ሚኒስትር እና እናንተን አስታማሚዎቹነወ ይጠየወቃል። እናንተ ደግሞ ኢሄ ፍሬ የሌለው ንግግር ነው ትላላችሁ! እውነቱን ለመናገር ከእናንተ ይለቅ ለኢህአዴግ በትጋት እየሰራ ያለው አቤ ነው ብለህስ….? ምን ታመጣለህ!? ሃሃሃ

  3. Tobia says:

    (just click on the link to see the highlight )http://www.youtube.com/watch?v=E-2PVh-Ht3U

  4. በለው! says:

    *ለሰማችሁም፤ለተሰማችሁም፤ ለሚሰማችሁም ፤ይሰማናል ብላችሁ ጆሮአችሁን የቀሰራችሁ ጉዳዩ የሚመለከታችሁ… ሕግዝሐበሔር ያበርታችሁ እሳቸውንም ያርማቸው፤ጭንቅላቱን ሸጠን መጠቀም እንችላለን ላላችሁ መተኪያ የሌለው ሊቁ እያላችሁ የምትለቀልቁና የምትወቁም ብትሆኑ ጭንቅላታቸው ዕጢ አለበት ከተባለ መቼም ላለፉት ፵ ዓመታት ተንበርክከው ሲፀልዩልን ሳይሆን የማይድን ነቀርሳ(ዕጢ) ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ሲተክሉ ነው ።አራት ነጥብ።

    **መለስ ብለው ሳያያዩ በዚያው ከቀሩ ያሳዝናል። አሁን ችግር የሚያመጣብንን ነገር ከወዲሁ በእጅ ፅሑፋቸው የሚተውልን ኑዛዜ ቢቻል ፎርጅድ እንዳይሰራ በቻይና በሕንድ በኪዌይት ፓርላማዎች ቢቀመጥ ጥሩ ነው። ለመሆኑ አጽማቸው የሚያርፈው በየትኛው ክልል ነው? ይቃጠላሉ ወይስ ይቀበራሉ? ሀውልታቸው አባይ ላይ ? አፍሪካ አንድነት ቅጠር ግቢ? ቀለበት መንገዱ ዳር? አፈ-ጉባኤው እግር ሥር ?ኢፈርት ቢሮ ? አሰብ ወደቡ ላይ? በምስራቅ አፍሪካ ሰላም አሰከባሪ በደቡብ ሱዳን ወይንስ በሱማሊያ ይተከልላቸው ?

    ***ይልቁንስ አጎትዎ ሁሴን ኦባማ ፴፫ ሚሊየን የጡርታ ገንዘብ በሽልማት በእጅ አዙር አዘጋጅቶልዎታል እሷን ሳይልሱ እነዲች ብለው ይሞቱና!!! ታሪካቸው በየትኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ ይጻፍ? ሕዘቦች ካሉም የትኛው?

    ይህንን ያነሳነው “የአደጋ መከላከል እና ቅድመ ዝግጅት “በሚለው መርሆ እንጂ …. በሚሊኒየሙ ዕቅድ፣ በሕዳሴው ጉዞ፤ በግሎባላይዜሽን (ዓለም አንድ መንደር በመሆኗ) ፤በአመስት ዓመቱ የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን (የተለጠጠው) ዕቅድ የሚካተት ያለመሆኑን ለማይወዱን የእድገት እንቅፋት ሟርተኖች እያሳሰብን። ባለፈው የግንቦት ወር የጂ -፰ ስብሰባ ላይ በከፍትኛ ደርጃ ስንወደስ የደስታችን ተካፋዮች ለሆናችሁ ብቻ ይሆናል። አበበ ገላው ቀረ ! አበበ ጭንቅላቱ ሆነ !
    የውሸት አድናቆትም የጭንቅላት ዕጢ ይሆናል? አቤቶ በለው!

  5. Buta Madingo says:

    I wish to our P/M melese Zenawe all the best he was traveling for medical by Jet sitting on one of very comfortable sit and he must be tired when he come back he better come in by coffin lay down to be more comfortable until the end in this case all Ethiopian people will be ok ok ok

  6. Demelash says:

    really it is touchy, I know many TPLF/EPRDF fighters from my village. Most of them payed their priceless life to this revolution but i am so sad what now these handfull woyane doing in Ethiopia. they forcefully retired most Amhara and Tigre fighters in 1990EC and sent to Dansha a hostile place with 3000 birr compensation. But the rest are corrupt and live luxurious life. Abe as you said it was not for such lunatic governance our brother ans sis scarifies heir life. Shame on you Meles and former and current woyanes.

  7. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

    ወያኔ ፡ በመጀመሪያ በፈጣሪ ያምናል እንዴ ? ሲጀመር እኮ ሰው ባይሎጂካላዊ ኤለመንት ነው ብሎ የሚያምን ፡ የሰይጣን ስብስብ ነው ፡፡ መሪው ሲታመሙም እግዚያቤር ይማሮት ከማለት ይልቅ ቻይና ትርዳዎት ማለት ያሻላል ፡፡

  8. tesfayebek@yahoo.com says:

    kikiki dear abe thankyou

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s