በስላቃዊ ጨዋታዎቹ የሚታወቀው ዘላለም ማልኮም ክበረት በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ ይህንን አስቀምጧል።
What a heartbreaking news?:
<<በአቧሬ አድዋ አደባባይ ፊት ለፊት ተሰቅሎ የነበረው እና ከ35,000 ብር በላይ የወጣበት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 4 ሜትር በ7 ሜትር እና ‘በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ ጀግና’ የሚል ፅሁፍ ያለበት ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች ተሰረቀ>>
እንኳን የዙፋኑን ወንበር አልሰረቁት እንጅ ይሄንስ ከደመወዛችንም ቢሆን ቆርጠን ወይም ቦንድ ገዝተንም ቢሆን እንተካዋለን፡፡ ካጠፋው ልታረም አለ ሰካራም፣ አይደለም እንዴ Abe ?
የሚያሳዝነው ደግሞ የሊቀ ሊቃውንት ምስል ከተሰቀለ ገና 5 ቀን እነኳን አልሆነውም እኮ፡፡ “ጠርጥር ከገንፎ ውስጥ አለ ስንጥር” ነውና ነገሩ የሽብር ሃይላትን እጅግ ጠረጠረኩ ለአቧሬና አካባቢው ህዝብ እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ መፅናናትን እማኛለሁ፡፡
Zelalem
በርግጥ እኔ በበኩሌ ይህንን የሚያክል የጠቅላይ ሚኒስትራችን ፎቶግራፍ ገና አምስት ቀን ባልሞላ ግዜ ውስጥ መወሰዱ ጥልቅ ሀዘን ቢሆንብኝም ምናልት “ለጤንነታቸው አመቺ የሆነ ቦታ” ተወስደው ሊሆን እንደሚችልም ጠርጥሬያለሁ። አሁንም ደግሜ እመኛለሁ። ፎቶግራፋቸው ብቻ ሳይሆን እርሳቸውንም “በቂ እንክብካቤ” ወደሚያገኙበት ቦታ ብናደርሳቸው አይከፋም…!
የምር ግን ይሄ ምን ያመለክታል…?
“ሰራቂው ለጠቅላይ ሚኒስትራችን ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል” እንዳትሉኝ ብቻ!
እርሳቸው ደግሞ እንደው ሁሌ ክፉክፉውን እያሰቡ መደንገጥ ያበዛሉ – በተለይ ደግሞ የአቶ ገላው ልጅ ባደባባይ ካሸማቀቃቸው በኋላ። ምናለበት እንደው ሌባ ሰረቀው ብለው ከማሰብ አፍቃሪወቼ እና አምላኪወቼ ታቦት መንገድ ዳር አይቀመጥም ብለው ወደ ቤት አስገብተው በግምጃ ጠቅልለው በቀን ሶስቴ እያሰገዱለት ይሆናል ብለው ቢያስቡ። አባይን ላደፈረሰ (አደራ ከምላሱ አልፈው በዋናም ለመድፈር እንዳይ ሞክሩ እና ምሁሩ መሪያችንን እንደ ጉቶ እያገላበጠ ወስዶ አባይ እራሱ አሸባሪ እንዳይባል) ምሁር ጀግና ምን ያንሰዋል?
hahahaha! nefesune liserekew selemichele kahunu neseha bigeba yeshalale
አዎ ወንድሜ ያለውን ጥልቅ ፉቅር በዝቶበት ስላላበቃው አንዱ ወንሜ ፉቅሩን ለመግለጽ ሸቀጥ መጠቅለያ ሊያደርገው ወስዶታል ታዲያኮ መታደል ነው ለፕሬዝዳችን በሸቀጥ መጠቅለያ ነት ወደየ ሰው ቤት መወሰዳቸው ነዋ ,,,,
ምናልባት ያልታወቁት ሰዎች ‘በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ ጀግና’ የሚለውን ፅሁፍ ‘በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን ባንዲራ የደፈረ ወራዳ ’ በሚል ፅሁፍ ለውጠው ሊያመጡት እንዳይሆን የሰረቁት
“በዘመነ ትውልድ ያልተደፈረውን አባይ የደፈረ ጀግና’ የሚል ፅሁፍ ያለበት ግዙፍ ምስል ባልታወቁ ሰዎች ተሰረቀ”
******በ********************************ለ*************************ው*****!
በጭራሽ አይደረግም ! ለዚያውም ፬ በ ፯ ሜትር ጎበዝ ባለፈው ይህ አበበ ገላው የሚባል ሰውዬ በ፳፩ኛው የግንቦት ሃያ በዓል መባቻ ሰሞን ሰውዬውን በልተው ጠጥተው እንዲህ በዓለም ህዝብ ፊት ያሸማቀቃቸው ምስላቸውማ 0 X 0 ተኮማትሮ ከተሰቀለበት ሥር መሬት ወድቆ ነውና ማታ በባትሪ ፈልጉት ።
ሁለተኛው ግምት ሰውዬው አባይን መድፈራቸውን ለማረጋገጥ በምስላቸው ሙከራ እየተደረገ ነው። ምስላቸው ሲንሳፈፍ ከተገኘ መልካም ካልተገኘ ደፈሩ የሚለው ቃል የተሳሳተ ነው ሰምጠዋል ነገር አለ በለው!
ሦስተኛው ግምቴ በ፳፻፩፭ ሥልጣኔን እለቃለሁ ስላሉ ወዳጆቻቸው ሰርቀው ውጭ ሀገር ከሉሲ አፅም ጋር ለዓለም አድናቂዎቻቸው ጂ 8 ላይ የተዋረደው መሪ እአሉ ሊያስጎበኙት ይሆናል የደበቁት።ታይሰን የቦክስ ግላቭ ፤የማይክል ጃክሰንም የዳንስ ግላቩ ለሽያጭ ቀርቦ የለ! ይሄኔ ነው ማቀርቀር… አቤ ይህንን ጉድ እንዳሰማ አደራ! ይሸበራል……
Demelash
I think TPLF itself stole the picture.
መድሃኒት ላይ “ህጻናት በማይደርሱበት ቦታ ይቀመጥ” የርሳቸውስ ፎቶ “አሸባሪዎች በማይይደርሱበት ቦታ ቢቀመጥስ?” እንዲያውም ቢደበቅስ? ወይስ ኢሳያስ ራሱ ለጉንበት በአላችን እንዲታይ አድርጎ ከሰራው በሁዋላ እስከሚቀጥለው ጉንበት ድረስ invisible እንዲሆን ሰርቶትስ ከሆነ?
ግን ጥያቄ አለኝ – ድሮ “ደፈረ” የሚለው ቃል ከግብር ሥጋ ወይም ከፍትፍት ሥጋ ወይም ከማንኛውም ሥጋ ነክ ወይም ሥጋ ተኮር የሆኑ ነገሮችን በማማከል ሲጠቀስ ነበር የምንሰማው እና እንዴት ሆኖ ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችንን “አባይን ደፈሩ” ተብለው ከነፎቶዋቸው እንደ “mug shot” ባደባባይ የሚሰቀለው? ሁኔታው በዚሁ ከቀጠል አደፋፈራቸውን የሚያሳይ ቭዲዮ ብቻ እንዳይወጣ ነው የፈራሁት – አቤ መላ በል እንጂ!
መድሃኒት ላይ “ህጻናት በማይደርሱበት ቦታ ይቀመጥ” ይባል እንደነበር ሁሉ የርሳቸውስ ፎቶ “አሸባሪዎች በማይይደርሱበት ቦታ ቢቀመጥስ?” እንዲያውም ቢደበቅስ? ወይስ ኢሳያስ ራሱ ለጉንበት በአላችን እንዲታይ አድርጎ ከሰራው በሁዋላ እስከሚቀጥለው ጉንበት ድረስ invisible እንዲሆን አድርጎት ከሆነ?
ግን ጥያቄ አለኝ – ድሮ “ደፈረ” የሚለው ቃል ከግብር ሥጋ ወይም ከፍትፍት ሥጋ ወይም ከማንኛውም ሥጋ ነክ ወይም ሥጋ ተኮር የሆኑ ነገሮችን በማማከል ሲጠቀስ ነበር የምንሰማው እና እንዴት ሆኖ ነው ጠቅላይ ሚኒስትራችንን “አባይን ደፈሩ” ተብለው ከነፎቶዋቸው እንደ “mug shot” ባደባባይ የሚሰቀለው? ሁኔታው በዚሁ ከቀጠል አደፋፈራቸውን የሚያሳይ ቭዲዮ ብቻ እንዳይወጣ ነው የፈራሁት – አቤ መላ በል እንጂ!