ወዳጄ ኢዮብ ብርሃነ፤ “አንዲት ኢትዮጵያዊት ሞት ተፈረደባት” የሚል መረጃ አድርሶኝ ነበር። ከዚሁም ጋር “ካላመንከኝ እህቷን ደውለህ ማናገር ትችላለህ!” ብሎ የስልክ ቁጥሯንም አስቀምጦልኛል። እኔም የፈጀውን ይፍጅ ብዬ ደወልኩላት…

እርሷም ይህንን አረጋገጠችልኝ…!

ሰናይት ትባለለች። በዱባይ “አባደና” ሰፈር በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ ነበር።  በምትሰራበትም ቤት አሰሪዋ የምታደርስባትን ጥቃት ለመከላከል ስትል በወሰደችው ርምጃ ርጉዝ አስሪዋን ትገድላታለች። ከዛም ደም የነካ ልብሷን ስታቃጥል በቤት ውስጥ የነበረው የ2 ዓመት ህፃን በጭስ ታፍኖ ይሞታል።

ወድያውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ፍርድ ቤት የቀረበችው ሰናይት ፍርዷን ለሁለት አመታት ስትከታተል ቆይታ የሞት ፍርድ ተፈረደባት። ሰናይት በጠበቃዋ አመካኝነት “የሞት ፍርዱ ተገቢ አይደለም” ብላ ይግባኝ የጠየቀች ሲሆን ይግባኙም ድጋሚ ታይቶ በድጋሚም የሞት ፍርዱ ተበይኖባታል።

እህቷ እንደነገረችኝ ከሆነ “ከዚህ በኋላ ይግባኝ መጠየቅ አትችይም!” ተብላለች።

ወይ ጣጣችን…! ምን ማድረግ ይቻለን ይሆን? የእህቶቻችን ሰቆቃ ማብቂያው የት የሆን…!? በእውነቱ ይህንን ዜና ስፅፍ እየተሰማኝ ያለው ሀዘን ማቆሚያው መቼ ነው…? መቼ ነው ሀገራችን ለሁላችንም የምትበቃን…? መቼ ነው መሰደዳችን የሚቆመው? መቼ ነው…?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

7 responses »

 1. Aman says:

  So sad abt the ethiopian. But think the other way round! She killed i repeat she killed a pregnant woman. That’s so rude and inhuman. I think she deserve it! Try to be fair even if they(arabs) are monster with human face!

 2. fitih says:

  ene kemegidel memotin mertalehu abe…. be ergit yasazinal gin esti sidetun ersawuna yihe neger yetekesetew addis abeba bihon bileh asib. Andit yebet serategna … eshi aseriwan rasuan lemekelakel sitmokir gedelech …. hitsanu gin min bewetaw … beza lay setiyowa erguz nat…. le fird yechegere neger 😦

 3. Ayichew says:

  I’m sorry to see this bad news. ere weyew yemengist yaleh? ebakih fetari tareken. melkam astedader binorma man hagerun keyewun leko yiseded nebere tarik alba tiwlid, medresha bis, kertata, lemagn ena chigaram adirgew askerun eko! yesetiyewa memot ayidelem ahun asasabiw kezih behuala keziya yalu Ethiopians eta fenta new. yihich lij lezih wenjel yaderesat mekerana sikayu multo tetrefrifo new. Yemeriwochachin betesebina wushochachew saykeru chigirna rehabin besim enkuan ayawkutim wanawochum restewtal. hizbu terabe tetema tesedede enesu min gedoachew.

 4. betu says:

  betam yasazenal lejitom gene yeserachiw sera tegebey ayedelem lela amrachi mewesed techile neber 3 sew matefat eko kelale neger ayedelem eske bega laye beders belen enaseb ? egizeyabeher yerdat ye meheret amelak esu newena yedereselat

 5. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  አቤ ፡ ወያኔ እያለ መቼም መቼም ይሄ ሰቃይ አይቆምም ፡፡ ሁሌም የዜጎችችን ደም በከንቱ ፈሳል ፡፡ እውነቴን ነው አቤ በጣም ያማርራል ፡፡ ቆይ እኛ በቃ እንደዚ ዶሮ ሆንን ማለት ነው በየቦታው የምንገደለው ? አረ ዶሮም በየመንገዱ አይገደልም ፡፡ ምን ፍርጃ ነው እባካችው ?

 6. እንደ እኔ says:

  ሰዉ ኢትዮጵያዊ ሰለሆነ ብቻ መጠየቅ የለበትም ማለት ነዉ? : ይህማ ምኑን ፍትሃዊ ሆን፡ ያጠፋ ሰዉ የ ጥፋቱን ተመጣጣኝ ዋጋ ሊያገኝ ይገባዋል: እንደተባለዉ ሁለት ሰዉ ከ ገደለች ፍርዱ ትክክል ነዉ ማለት ነዉ :
  ይህን ነገር ባንተ ወይም በ እኔ ቤት እንደሆነ እንሰብ አንድ ሁለት መቶ ወይም ሶስት መቶ ብር እየሰተህ የ ምታኖራት የ ቤት ሰራተኟ ዓለመግባባት ተፈጥሮ ከ በተሰብህ 2 ሰዎችን ብተገደል ምን ተላለህ : ወደ ክፍለ ሃገር ትሽኙታለህ ? ህምምምም ሰለዚህ ጭፍን አንሁን ባይ ነኝ::

 7. በለው! says:

  ***********************************************
  የገደለ ይገደል የሚል ሕግ መች ነበረን ?
  በዘመኑ የሕግ ሰውነታችን የታወቀልን
  ዘመን መጣ ይህ አዋራጅ አድሎኛ
  ቤታችንን ሰጠን ለባለሀብት ዘመነኛ
  እነሱ ሲበሉ እኛ እያዛጋን ይሻል ይሆን ብለን
  በባሕር ቀዘፍን ስንቱ አቋረጠ ስንቶችስ ሰመጥን ?

  ውድ ልጅ ሠናይት ምንኛ በረዳት
  ስቃይ መከራን ሲደራርቡባት
  አውልቃ አቃጠለች ግፉ ቢበዛባት
  ያቺ የቁጡ ደም አትንኩኝ ባይነት
  እርቃኗን ታየች ሰው ባለፈበት
  ዛሬም ከጭቆና ከስቃይ ከእንግልት
  ለሰላም የሸሻችሁ ከሰው ቤት
  ለምን? እንዴት? ለማን ብዬ? በሉ
  ለብቻችሁ አትውደቁ ሞኝ አትባሉ
  ለመብታችሁ በአንድነት ቆማችሁ ታገሉ።

  ሀገሩ የእናንተ ሰጪ ነሺ የሌለበት
  መብታችሁ እኮ ነው የድርሻዬ ማለት
  መማር መሥራት መኖር በነፃነት
  ጎበዝ ንቃ በሰው ሀገር አትሙት !
  ይሻልሃል በሀገርህ በቀዬህ ዕድር ባለበት
  ጠይቅ ? ተናገር ! ለመብትህ ተሟገት
  መጥፎ ዜና ይቁም ቀነ ቀጠሮ አያሻም
  ዱባይ ‘አባደና”ሌላውም ሰው መቅጠፉን ያቁም
  መብትህን አትለምን መነካትም የለበትም !

  በቃ! ሲባል መስማትን ካልቻለ
  “እንቢኝ” ማለት ማን ከለከለ ?
  በዘር በጎሳ በቋንቋ በፆታ ሳንበታተን
  ለክብራችን ለመብታችን ለኢትዮጵዊነታችን
  ፅናቱን ብርታቱን ባለንበት ያድለን
  አብረን እንኖራለን ነፍስ ይማር ሀዘንን ያርቅልን።
  *********************************
  በለው! ከሀገረ ካናዳ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s