በዛ ሰሞን ከተፈጠሩ የኢንተርኔት ቀልዳ ቀልዶች መካከል የብዙ ሰዎችን ልብ በሳቅ ፍርስ ያደረገችው ይህቺ ናት፤ ባለቤቷ ማን እንደሆን እንጃ… ማለቴን የተመለከተው ወዳጃችን “አክሊል” የቀልዱ ባለቤት ተቦርነ እንሆነ ነግሮኛል። ቀልድህ ይበረክ እንበለው እንጂ…

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ልጃቸው ስመሃል እና ባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ ሆነው በአውሮፕላን እየሄዱ ሳለ አዲሳባን ቁልቁል እየተመለከቱ እጅግ ሩሁሩህ እና ደግ የሆኑት አቶ መለስ ከኪሳቸው አዲስ አንድ ብር አወጡና “ይቺን አንድ ብር ወደ አዲሳባ ልወርውራትና አንድ ነዋሪ ላስደስት” አሉ። ይሄን ግዜ ወ/ሮ አዜብ፤ “ከፀደቁ አይቀር ይንጋለሉ…” ብለው ከተረቱ በኋላ፤ “አምሰት ብር ጣልና አምስት ሰዎችን አስደስት!” አለቻቸው። ልጃቸው ስምሃልም የልጅ ነገር፤ “ከይት ያመጣዋል!?” ብላ ሳትጨነቅ፤ “ዳዲ ስሞትልህ አስር ብር ጣልና አስር ሰዎችን አስደስት…!” አለቻቸው።

በዚህ ግዜ የቤተሰቡን ውይይት በአንክሮ ሲሰማ የነበረው አውሮፕላን አብራሪው “ጌታዬ ለምን ራስዎን ጥለው ሰማኒያ ሚሊዮን ህዝብ አያስደስቱም?” ብሏቸው እርፍ አለ።

ዛሬም ከእርሳቸው ራስ ላይ አልወረድኩም። (“ራሳቸው እንዴት ቢመችህ ነው…?” ብሎ ማሽሟጠጥ ከርሳቸውም ከኔም ጋር አያቀያይምም እና አትስጉ… የማሽሟጠጥ መብት እስከ “ፑንት” ተፈቅዷል።) (በሌላ ቅንፍ “ፑንት” ምንድነው? በልጅነታችን ብዙ ለማለት እንጠቀምበት ነበር። ከምን የመጣ እንደሆነ ግን አላውቅም…!)

አቶ መለስ ዜናዊ የአሜሪካ ስብሰባቸውን (አበሳቸውን ማለት ይቀላል) ጨርሰው ትላንት ማምሻውን አዲሳባ ገብተዋል። አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ዘመድዎ ጋር ዛሬ እና ትላንት ስልክ ቢደውሉ “ሆያ ሆዬ” ሲጨፍር እንደነበር ጎረምሳ፤ በሁለቱ ቀናት የተቃውሞ ሰልፍ ድምፃቸው ዝግት ብሎ ታገኟቸዋላችሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትራችን አበበ ገላው ያከናነባቸው ካባ በበርካቶች ዘንድ የተለየ ስሜት ፈጥሯል። በየፓልቶክ ሩሞች ውስጥ ከአመት በዓል የበለጠ ድግስ ሲደገስ ነበር። እንደ ምሳሌ  “የኢትዮጵያውያን ወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ” (ECADF) ቅዳሜና እሁድን በዝማሬ እና በመንዙማ ሳይቀር አምላካቸውን አመስግነዋል። አባላቶቹ በዚህ አላበቁም በመለው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያስተባበረ “ዘመቻ አበበ ገላው” በሚል ለኢሳት ቴሌቪዥን እገዛ ለማድረግ ገቢ ማሰባሰቢያ  ሁሉ አዘጋጅተዋል። (ስለ ECADF ካነሳን አይቀር አንዲት የስድስት አመት ህፃን ልጅ  በፓልቶክ ላይ የሰጠችው አስተያየት በጣም አስገርሞኛል።

በፓልቶክ ሩም አበበ ገላውን ኢንተርቪው እያደረጉት ነበር። በመሃል ይቺ ህፃን ልጅ ገባች። እንደሚከተለውም ተናገረች፤ “አበበ ገላው እግዚአብሄር ይባርክህ… መለስ ዜናዊ ደግሞ ለንቦጩን ጥሎ ሲያስቅ…” ብላ በህፃን አንደበቷ ፍልቅልቅ ስትል አስገረመችኝ! “የሚያድ ልጅ አይጥላህ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ” አለች ሙያዬ!

ለማንኛውም አበበ ገላው ጠቅላይ ሚኒስትሩን አስታጥቆ ሸኝቷቸዋል። በዚህም በርካታ ዌብሳይቶች ደግሰዋል ፌስ ቡክም በአርበኞቹ የግጥም አዚም ተሞልቷል።

መረጃዬን ሚዛናዊ ለማድረግ ብዬ አይጋ ፎረምን እና ዋልታን ኢንፎርሜሽንን ለማየት ሙከራ አድርጌ ነበር። ትንሽ ጭር ያሉ ይመስላሉ። ሁለቱም ጥቁር አለበሱም አንጂ ሀዘን ላይ ናቸው። ባለፈው ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደነገጡ ግዜ አብረው የደነገጡ እስከ አሁንም ክውታቸው የለቀቃቸው አይመስሉም!  አይጋም ዋልታም በስሱ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዋሽንግተን ዲሲ ህዝቡ አቀባበል አደረገላቸው” የሚል ዜና ይዘው ወጥተዋል። ነገሩን ለተከታተለ ሰው፤ እነ አይጋ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ሽሙጥ ጀመሩ እንዴ ያሰኛል!

የሆነ ሆኖ አበበ ገላው የሰራው ጀብድ እስካሁንም ተወርቶ አላለቀም። በአለም አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አዋርዷቸዋል። ትዝ ይሎት እንደሆነ አዲሳባ በነበረው የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ቀጥታ ይመልሱልኝ!” ያላቸውን ሰውዬ አንስተን እንዴት ቢደፍራቸው ነው ብለን ቁጭታችንን ተናግረን ነበር። አሁን የባሰው መጣ! ወሬውም ደመቀ ለበርካቶችም የደስታ ቀን ሆነ።

አንዱ ወዳጄ፤ “ሲዋረዱ እንዲህ ከሆንን ቢወርዱ ምን ልንሆን ነው!?” ብሎ ጠይቆኝ ነበር፤ እኔም አልኩት “ውይ ተው ክፉ አትናገር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንኳንስ ከስልጣን ሲወርዱ እና የኪሏቸው መውረድ እንኳ ያስከፋኛል!” አልኩት! (እሰይ የኛ አሳቢ አይሉኝም!?)

ውይ ረስቼው አንዳንድ እጅግ በጣም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር የተለከፉ “ልክፍታሞች” (ይቺ ነገር ስድብ መሰለች ይቅርታ…) ለማንኛውም አበበ በለውንም ሆነ በጉዳዩ ላይ አስተያየት የምንሰጥ ግለሰቦችን አብጠልጥለውናል። “እንዴት እርሳቸውን የሚያክሉ ሰው አታከብሩም…?” ሲሉ ጠይቀውናል። እኔ በበኩሌ ሂሴን ውጣለሁ። “አንቱ” እያልኩ “ክቡር ሆይ” እያልኩ “አላከበርክም” ከተባልኩ እድሌ ነው እንግዲህ ለወደፊቱ ጥንቃቄ አደርጋለሁ።

ታድያ ከእነርሱ ምክር በኋላ አንድ ወዳጄን በፌስ ቡክ ሳወጋው ጠቅላይ ሚኒስትሩን አለቅጥ ዝርጥጥ ሲያደርጋቸው። “ተው እንጂ ወዳጄ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማክበር አለብን እኮ!” ብዬ ብገስፀው “መቼ ነው ቀብሩ?” ብሎኝ እርፍ አለ። “መቅበር አለብንኮ” እንዳላልኩት ያውቃል ሆነ ብሎ ነው። አያችሁ አይደል፤ በየት በኩል እናክብራቸው ታድያ…!? ወይ ደግሞ አንድ ቀን በስማቸው እንሰይም… ያመቱ የወሩ እያልን እናንግሳቸው ይሆን!?

በመጨረሻም

በአሁኑ ጉዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተከትሎ አሜሪካ የሄደው የኢቲቪው ጋዜጠኛ አሸብር ነበር። ከዚህ በፊት አሹ እንዳስለመደን ሲመጡ አውሮፕላን ውስጥ ኢንተርቪው ሲያደርጋቸው እስከ አሁን አላሳየንም! ምነው…? ብሎ የሚጠይቅልኝ ማነው!?

ቪዲዮውን ላላያችሁት ወይም መድገም ለምትፈልጉ ወዳጆች፤

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

4 responses »

 1. Temesgen says:

  አቤ አዲሱ በሎገህን ማግኛ መንገድ አሪፍ ነው ተሳክቷ፡፡

 2. ነህምያ says:

  እዚህ አሜሪካ ነው አሉ የሆነው፡፡ መቼም የአሸብር ነገር ከተነሳ ብዬ ነው፡፡ እዚህ አሜሪካ አሸብር የሚባል ሰው ደንብ በመተላለፍ ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር አሉ፤ መቼም አሉን መያዝ መጥፎ አይደለም፡፡ እናም ወደ ፍሬ ጉዳዩ ለመግባት መንደርደር ተገቢነውና የተለመደው ግለ መረጃ (background information) መጠየቅ ተጀመረ

  Your Last Name …… መለሰ (መለሰ ዜናዊን ማለቴ አይደለም የአባቱን ስም
  ስለማላውቀው ነው)
  Your First Name …… Ashebir
  What is the equivalent word in English …..Terrorist
  What ….. Terorism
  OMG …. Let he be DEPORTED SOON

  ብለው መወሰናቸው ተሰምቷል፡፡ ለዚህም ማስረጃው ኢትዮጵያ ሄዶ ለዓመታት የሚቆየውን ወይም ላይመለስ ወደ አገረ የገባውን የአራዳ ልጆች አሪፍ ስም አውጥተውለታል Deportivo (ዲፖርቮ ላ ካሩኛ እንደማለት ግን አይመስለኝም)

  እናም አሸብር ሆዬ ተሸብራ በየት በኩል የአውሮፕላን ውስጥ ኩመካ ይምጣላት፡፡ አይ አቤ ማፍረሻ ተስፋዬን በናጣውም ሌላ ማፍረሻ በማግኘታችን ተጽናንተናል

  ከማይጨበጠው 11 በመቶ
  ማፍረሻ ተፈጥሯል ተስፋዬን ተክቶ
  (ያውም በጽሑፍ) ብለን ከቅንፍ ወጥተን፣ ከድረ ገጹም እንወጣለን፡፡

 3. Just Kidding says:

  አቤ እስክ ፑንት ማለት ከ አዲስ አበባ እስክ ፑንት ላንድ ማለት ነው

  LOL

 4. በለው! says:

  የተሸበረ ዜና “ከሮናልድ እሬገን መሰብሰቢያ አዳራሽ.. ለፈረደበት ድሃ ሕዘብ፡የወያኔ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በአሸብር(አሹ) አፍሪካን ወክለው ከተሰደዱ አራት መሪዎች ማ? ምን አለ?።
  *አቶ መልስ በአፍሪካ 70% በአነስተኛ ማሳ የሚተዳደሩ ገበሬዎች አሉ በጋዜጠኛቸውም አገላለፅ “ከምግብ ሰበል እና ሥጋ ፈጆታ 50ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በአመት ይደረጋል ይህም ወደ ውጭ ልካ ከምታገኘው ገቢ 5 ዕጥፍ ይልቃል።”
  አቶ መልስ ቅድሚያ የሰጡት ለፓርላማ ወንበር ቁጥር፤ ያላቸውን የእስርኛ ብዛት፤ የተገደለውን ህዝብ ቁጥር፤የተራበውንና ተሰደደውን ህዘብ ብዛት ከተወለደው ሕዝብ ቁጥር፤ደርግ ከሰራው ጋር ማወዳደር እንጂ በዚህ ዘመን ይህ ትውልድ ማግኘት የሚገባውን ያላገኘ ተዋረዶ፤ ተሰድቦ፤ ተንቆ፤ ተሸማቆ፤ሰብዓዊ መብቱ ተረግጦ፤ኖሮም ሞቶም ያልተከበረ መኖሩን ይክዳሉ…..

  ሰውዬው ገበያ እህል ሊሸጥ ወጣ አሉ (ዛሬ አደለም ድሮ ነው!) ሲመለስ ጎረቤቱ ሲያርስ አገኘው …
  አያ እከሌ እነደምን ዋልክ? እግዘሐብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ …..የእክሊት አባት…
  ገበያ አርፍደህ ነወይ ? … አዎን … ገበያ እረክሷል እንዴት ዋለ? ገበያው ጥሩ ነበር ባለፈው ሀምሳ ብር የገዛሁትን በሃምሳ ብር ሸጬ መጣሁ። ታዲያ ምን አተረፍክ ? ትረፉ ዘጥ ዘጥ ነው አለው አሉ።

  **ለዚህ መልስ የታንዛኒያው መሪ ተመሳሳይ መልስ አላቸው “የአፍሪካ ገበሬዎች ሁለት ኪሎ ጥጥ ከአንድ ዶላር በታች ዋጋ ለቻይና ይሸጣሉ። በምትኩ ግን ሁለት ካኒቴራ መልሰው እያንዳነዱን 20 ዶላር ሂሳብ ይሸጡልናል”
  እኛም ድሮውንም ያልነው የዚህ የ11% ዕድገት “ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል ሆኖብን ተው ብለናል አሁንም ዋ!ዋ!

  ***የቤኒኑ መሪ ግን የተለየ ሐሳብ አላቸው” ለአነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ ገበሬዎች መንገድ መሰራት አለበት ” ለአውርቶ አደሩ አምርተው እንዲያቀርቡ የጥቂቶች ኪስ ለማደለብ ነው ለመሆኑ ለገበሬው የማምረቻ መሳሪያ፤ማዳበሪያ፤ስለ ጤናው፤ስለ ከበቶቹ ቀለብ፤ስለ ልጆቹ ትምህርትና ልበሳቸው ያነሳ ነበር? ? ?

  ****የጋናው መሪ “እኔን ጠይቀኝ ይላሉ ከፍተኛውን የግብርና ዘርፍ ተማምኖ ለሚኖረው 70% ድሃ አፍሪካ ገበሬ እንዲለወጥ ከተፈለገ ቅደሚያ ተሰጠቶት መደገፍ አለበት።” ይላሉ(…..)
  ይህም ማለት በስኳር፤ በጨው፤ በማዳበሪያ፤በዘይት፤በዘር እህል እየደለሉ(እያስፈራሩ) ገዢውን መደብ እንዲመርጥ ማፈን ማስፈራራት አደለም።! መንገድ ሰራንልህ ብሎም ከማሳው ላይ ሄዶ ‘በኮሞዲቲ ኤክስቼንጅ’ ሥም የገዢው መደብ ለሚፈልጋቸው ተቀባዮች እንዲያስረክብ እነሱም ተቀብለው ከተማ ሳያስገቡ ለራሳቸው ጎሳ ነገድ በተመጣጣኝ ዋጋ ሲያቀርቡ ባልታወቀ መንገድም የባሕር ወደብ የሌላት ድሃ ሀገር ከ80 ሚሊዮን ሕዝቧ ተርፎ እንዴት በውጭው ዓለም ጤፍ እና ቡና እንዴት ሊረክስ ቻለ? ? ?”

  ይህንን ቱልቱላ ለመንፋት ነው ይህ ሁሉ ወጪ ?አዲስ አበባ፤ አውሮፓ፤ አሜሪካ ፤የትራንስፖርቱ፤የጋዜጠኛው፤የሆቴሉ፤ የደህንነቱ፤በእያንዳንዱ ስብሰባ ቢጠራቀም ይህ ወጪ በዓመት የብዙ ሕፃናት ነፍስ የሚያድን ለሆስፒታል ወይንም ለት/ቤት ወጪ ቢደረግ እና ይህንን ወሬ በሀገራቸው ተቀምጠው ‘በፌስ ቡክ’ ‘በእስካይብ’ ‘በኢሜል’ ቢያወሩት የተሻለ ቁጠባ ነው የሚል የፀና ዕምነት አለኝ። አለበለዚያ ‘ትሪሊኒየም’ ድህነትን አዘንጦ ሊመጣ ነውና ፀንታችሁ ጠበቁ በለው!! VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s