የዚህ ፅሁፍ አላማ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በአሜሪካ እየተዘጋጀባቸው ያለውን ታላቅ ተቃውሞ “ማሳበቅ” ሲሆን ቢቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞውን እንዲሰርዙት ባይችሉ ደግሞ ሌሎች ዘዴዎች በመጠቆም ለጠቅላይ ሚኒስትራችንን ያለንን ተቆርቋሪነት ማሳየት ነው። (መቼም ይቺን አንቀፅ ያነበበ የኢንሳ “ዘጊ” ብሎጋችንን በሰፊው እንደሚከፍተው እርግጠኛ ነኝ!)
ሰሞኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአሜሪካው ፕረዘዳንት ባራክ ኦባማ ጋር አሜሪካ ሊገናኙ ተቀጣጥረዋል። በነገራችን ላይ ኦባማ ናቸው የጋበዟቸው። (ለነገሩ ሰላም ከተመለሱ ኢቲቪ “ሀገራችን አስራ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ የግብዣ እድገት አሳየችች።” ብሎ እንዴት እንደተጋበዙ በዝርዝር ሳይነግርዎ ልሽቀዳደም ፈልጌ እንጂ ጆሮዎ “ስትራፖ” እስከሚይዘው ድረስ ይሰሙታል። በርግጥ ኢቲቪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተጋበዙት በሀገሪቱ ያለውን የምግብ እጥረት አስመልክቶ ምን ብናደርግላችሁ ነው የሚሻላችሁ? በሚል ለመማከር መሆኑን አይነግረንም።(“ይደብቁናል እኮ አባዬ…” አለ ያ ቀልደኛ))
ለማንኛውም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ በዋሽንግተን ካምፕዴቪድ አቶ መለስ ከግሩፕ ስምንት “ጂ8” ሀገራት ጋር ስብሰባ ይቀመጣሉ። ይሄ በርሳቸው ለምናምን ለኛ ታላቅ እመርታ ነው…! ቀኑንም እንደ ብሄራዊ በዓል ልናከብረው ይገባል። ችግሩ ግን ወዲህ ነው…
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሜሪካ ለዚህ ስብሰባ ሲመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን በዛ ተሰለፈው ይጠብቋቸዋል። ሰልፉ የእንኳን ደህና መጡ አይደለም። የተቃውሞ እንጂ ሰልፈኞቹ እቅፍ አበባ ይዘው አይደለም የሚጠብቋቸው እንቅልፍ የሚነሳ መፈክሮችን እንጂ! ምስኪን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰልፍ ወደ እርሳቸው ሳይመጣ እርሳቸው ወደ ሰልፉ ሲሄዱ በእውነቱ አንጀቴን በሉት።
በነገራችን ላይ ዛሬ አውራምባ ታይምስ ዌብ ሳይት ላይ ቀርበው የነበሩት ዶክተር ፍስሀ እሸቱ እንደነገሩን ከሆነ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ሊጮሁባቸው በቂ ዝግጅት አድርገዋል። (እዝች ጋ እናጋነው ካልን አንዳንዶቹም ድምፃዊያን የሚሰሩትን “ቮካል ኤክሰርሳይስ” ሰርተው ሁሉ ነው የሚጠብቋቸው) አሜሪካ እና አካባቢዋ የሚኖር ግለሰብ በዚህ ሰልፍ ላይ የሚቀር የለም ተብሏል። ለዚሁ የሚሆኑ በርካታ አውቶብሶችም እንደተዛጋጁ ሰምተናል።
በእውኑ ለጠቅላይ ሚኒስትሬ ተጨነቅሁ እናም ይህንን ምክር ልመክራቸው ወደድኩ
ይሄውልዎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እውነቱን ለመናገር እንደሰማነው ዝግጅት ከሆነ የሚገጥምዎትን ተቃውሞ መቋቋም የሚችሉ አይመስለኝም። እና “ምናባቴ ይሻለኛል…?” ያሉ እንደሆነ እንደሚከተለው እመክራለሁ፤
ዘዴ አንድ
ራስዎን ይቀይሩ። እልም ያለ አሜሪካዊ ራፐር ለመምሰል ሙከራ ያድርጉ። ከዛ ማንም ሰው ወደ እርስዎ አያይም ወይም አይጠቋቆምብዎትም ከዛ… ከዛ ደግሞ በጆሮዎ ሁነኛ የሙዚቃ ማዳመጫ “ኤር ፎን” ያድርጉ። ያው የተቃዋሚዎቹ ጩኸት የማይቀር ስለሆነ “መለስ በቃ!” “ኦባማ ከአምባገነኖች ጋር መቀመጥህን አቁም” “መለስ ዜናዊ ወንጀለኛ ነው” “መለስ ዜናዊ ወዘተ ነው…” በሚሉ መፈክሮች አይምሮዎ እንዳይነካ እና እርዳታውን በሙሉ ልብዎ ከመጠየቅ እንዳያቅትዎ በኤር ፎኑ “አይ በላንዶ” የሚል ሙዚቃ ከፍ አድርገው ይክፈቱ።
ዘዴ ሁለት
የእንቅልፍ ኪኒን ይወሰዱ። የምሬን ነው የምልዎ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዉ አምርሮብዎታል። “በሰልፉ ላይ ዕድሜው ለአቅመ ተቃውሞ የደረሰ አንድ እንኳ የሚቀር ሰው የለም!” ብለው ሲመካከሩ በጆሮዬ ሰምቻለሁ። እርግጠኛ ነኝ የሚነሳብዎን የተቃውሞ መፈክር ሰምተው ሰው ይሆናሉ ብዬ አልገምትም። ስለዚህ በእውቅ ባለሞያ ተሰልቶ፤ ልክ ስብሰባው ቦታ ሲደርሱ ሊነቁ በሚችሉ መልኩ የተሰናዳ የእንቅልፍ ኪኒን ይውሰዱ። ከስብሰባውም ሲወጡ ያቺኑ ኪኒን የተቃውሞን ቦታ እስኪያልፉ ድረስ ታስተኛዎ ዘንድ ደግመው ይውሰዷት። ከዛም እኛ ራታችንን በእንቅልፍ እንደምንሸውደው እርስዎ ደግሞ ተቃውሞን በእንቅልፍ ሸወዱት ማለት ነው።
ዘዴ ሶስት
ከስብሰባው ይቅሩ። በበኩሌ በተቃዋሚዎቹ ብዛት እና በተቃውሞ ቃላቸው የተነሳ ያቺ በብስጭት ግዜ የምትነሳ ህመምዎ ተነስታብዎ አጓጉል ሆነው ከሚቀሩ ሶስተኛው እና የመጨረሻው ምክሬ ከስብሰባው ቢቀሩ ይሻላል የሚል ነው። አዎና… የእነሱ እርዳታ በአፍንጫዎ ጥንቅር ብሎ ይውጣ… ይሄንን ያህል እኛ ርሃብ ብርቃችን ነው እንዴ!? በብስጭት ርስዎ አንድ ነገር ከሚሆኑብን ርሃብ በስንት ጣዕሙ!
በመጨረሻም
ሁሉም ነገር ካልተሳካ ይቺን ምርቃት እነሆ… “እግዜር የስራዎን ይስጥዎ!”
Posted by abetokichaw on May 17, 2012 in Uncategorized.
11 Comments
Yimechik Abie, “ሰልፉ የእንኳን ደህና መጡ አይደለም። የተቃውሞ እንጂ ሰልፈኞቹ እቅፍ አበባ ይዘው አይደለም የሚጠብቋቸው እንቅልፍ የሚነሳ መፈክሮችን እንጂ!” .
We always follow you Abie!
ሁሉም ነገር ካልተሳካ ይቺን ምርቃት እነሆ… “እግዜር የስራዎን ይስጥዎ!” ሃሃሃሃሃሃሃ……አቦ ይመችህ ነፍሴ!!!
እኔ እዛ ብሆን ኖሮ መፈክር አይደለም ይዤ የምጠብቃቸው፣ ድምጼንም አላሰማም፡፡ የየኔሰው ገብሬን፣ አለም ደቻሳን፣ በዱባይ ተሰቅላ የተገኘችውን፣ የጉራፋርዳ ተፈናቃዮችን፣ የጋዜጠኞችን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በረሃብና በስደት የሚሰቃዩትንና በየጎዳናውና በስደት በየበረሀው የወደቁ ወገኖችን እና የሌሎችንም ፎቶግራፎች በትልቁ ሰቅየ የማያቁዋትን ግን የሚመሯትን ሀገር አስተዋውቃቸው ነበር፡፡
Death to Agazi Nazi Racist Meles Kendebbo !!!
በዛው ያስቀረው አይመልሰው
Amen!
ketelubet egha wetatoch nen engi ager atefi ayedelenem!! thanks!!
የተዘጉ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊታዩ የማይችሉትን ዌብሳይቶች “Expat Shield” ወይም “Anchor Free” የተባሉትን ሶፍትዌሮች ከኢንተርኔት ላይ በነፃ ዳውንሎድ በማድረግና ኢንስቶል በማድረግ በቀላሉ ሊያኟቸው ይችላሉ፡፡ ፕሮግራሙ ከተጫነ በኋላ ታስክ ባሩ ላይ “Connect/On” ማለትና “Connected…Privacy is On” የሚለው መልዕክት እስኪመጣ መጠበቅ ይገባል፡፡ ይህ ሶፍትዌር ያላችሁበትን ኮምፒውተር አይ.ፒ አድራሻ በመደበቅ እነዚህን ብሎጎች አክሰስ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡
ጠይቅላይ ሚኒ… ይልቅ በእየቦታው አላግበብ ከድሃ ሕዘብ ግብር ሰብስበው እየከፍሉ ከወሸቋቸው አጉል ደጋፊዎችዎ ካድሬ አሰመሳይ ሆድ አደሮች ይልቅ ያራዳ ልጅ አቤን ፌስ ቡክዎ ላይ አድ ቢያደርጉት ይሻልዎታል።ጭራሽ ከውስጥም ከውጪም ያስቀመጧቸው ፎጋሪ ደጋፊዎችዎ ሕዘቡን እልህ ውስጥ ከተው ተዓምር ሊፈጠርልዎ ነው። እኔም እጮሃለሁ ተጠንቀቁ ነገር አለ በለው!
ዉይ! ዉይ! ውይ! ውይ! ውይ! ይሄን ሁሉ ተመክረዉ ሲያበቁ መጥተዉ ነው እንዲያ ሆነዉ የተመለሱት? ብቻ አሁንም ንገሯቸዉ ዘንድሮ አበበ ገላዉ ነዉ ያስደነገጣቸዉ ለከርሞዉ ራሳቸዉ ባራክ ኦባማ እንደሚሆኑ እኔ ጥርጥር የለኝም ሰዉዬዉ ትግስታቸዉ የተምሟጠጠ ይመስላል
SHIMUTEN and SILAKOCH by ABE. tamchagn
Fill in your details below or click an icon to log in:
You are commenting using your WordPress.com account. ( Log Out / Change )
You are commenting using your Facebook account. ( Log Out / Change )
Connecting to %s
Notify me of new comments via email.
Notify me of new posts via email.
Δ
Enter your email address to follow this blog and receive notifications of new posts by email.
Email Address:
Follow
Yimechik Abie, “ሰልፉ የእንኳን ደህና መጡ አይደለም። የተቃውሞ እንጂ ሰልፈኞቹ እቅፍ አበባ ይዘው አይደለም የሚጠብቋቸው እንቅልፍ የሚነሳ መፈክሮችን እንጂ!” .
We always follow you Abie!
ሁሉም ነገር ካልተሳካ ይቺን ምርቃት እነሆ… “እግዜር የስራዎን ይስጥዎ!”
ሃሃሃሃሃሃሃ……አቦ ይመችህ ነፍሴ!!!
እኔ እዛ ብሆን ኖሮ መፈክር አይደለም ይዤ የምጠብቃቸው፣ ድምጼንም አላሰማም፡፡ የየኔሰው ገብሬን፣ አለም ደቻሳን፣ በዱባይ ተሰቅላ የተገኘችውን፣ የጉራፋርዳ ተፈናቃዮችን፣ የጋዜጠኞችን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በረሃብና በስደት የሚሰቃዩትንና በየጎዳናውና በስደት በየበረሀው የወደቁ ወገኖችን እና የሌሎችንም ፎቶግራፎች በትልቁ ሰቅየ የማያቁዋትን ግን የሚመሯትን ሀገር አስተዋውቃቸው ነበር፡፡
Death to Agazi Nazi Racist Meles Kendebbo !!!
በዛው ያስቀረው አይመልሰው
Amen!
ketelubet egha wetatoch nen engi ager atefi ayedelenem!! thanks!!
የተዘጉ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ሊታዩ የማይችሉትን ዌብሳይቶች “Expat Shield” ወይም “Anchor Free” የተባሉትን ሶፍትዌሮች
ከኢንተርኔት ላይ በነፃ ዳውንሎድ በማድረግና ኢንስቶል በማድረግ በቀላሉ ሊያኟቸው ይችላሉ፡፡ ፕሮግራሙ ከተጫነ በኋላ ታስክ ባሩ ላይ “Connect/On” ማለትና “Connected…Privacy is On” የሚለው መልዕክት እስኪመጣ መጠበቅ ይገባል፡፡
ይህ ሶፍትዌር ያላችሁበትን ኮምፒውተር አይ.ፒ አድራሻ በመደበቅ እነዚህን ብሎጎች አክሰስ ማድረግ የሚያስችል ነው፡፡