ባለፈው ግዜ ቼልሲ ከባርሴሎና ጋር ሲጫወት በሩን ጥርቅም አድርጎ በፓስዋርድ ነበር የዘጋው። ለምን ዘጋ ያልን እንደሆነ በርካታ ምክንያቶችን መደርደር እንችላለን። ከእኛ ይልቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ኤርሚያስ የሆነ ነገር ብሎ እንደሆነ እንፈልግ እና እንመልከት። ምንም ካላለም ከቀጣዩ የዋንጫ ጨዋታ ጋር አያይዞ ዘርዘር ያለ አጥጋቢ ምክንያቶች እንደሚነግረን ተስፋ እናድርግ።

ትላንት አንድ ፈረንጅ ወዳጃችን፤ “ብሎጌ በተደጋጋሚ ተዘጋ ብዬ ዋይ ዋይ” ማለቴን ወሬ ሰምቶ ደውሎልኝ ነበር። እኔም ስለሁኔታው አስረዳሁት። “ብታምነም ባታምንም አስራ አንድ ግዜ ብሎጌ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተዘግቷል፤ ከዛም አልፎ ተርፎ አንዳንድ አክቲቭ የሆኑ ልጆች ፌስ ቡክ አካውንት ሁሉ እየተዘጋባቸው ድጋሚ እየከፈቱ ነው።” ብዬ ማቃጠር፤ ከዛልዎ ፈረንጁ ወዳጃችን በእንግሊዘኛ ተገርሞ ተገርሞ ተገርሞ ሲያበቃ ለመሆኑ “መንግስት ለምንድነው በዚህ ግዜ እንዲህ የሚያደርገው? ምርጫ እንኳ ቢኖር ድምፅ እንዳያሳጡኝ ብሎ ነው ይባላል? አሁን ግን ምን ሆኖ ነው…?” አለኝ። ለዚህ መልስ የለኝም። ስለዚህ እኔ ራሴ ይህንን ጥያቄ ልጠይቅ… መንግስት እንደ ቼልሲ ዘግቶ መጫወት ለምን ፈለገ?

ወሬዬን ልቀጥል ነበር ሳስበው ሁልግዜ እኔ ብቻ ሳወራ “ያንተ ወሬ ብቻ አላልቅ አለ!” እንዳይሉኝ ሰጋሁና ለምን መድረኩን ለአንባቢ ወዳጆቻችን አልተወውም አልኩ “እርስዎም ይሞክሩት” ብንለውም ይሆናል። እንደሚያውቁት ወይም ደግሞ ማወቅ እንደሚገባዎ  መንግስታችን የተለያዩ ዌብ ሳይቶችን ጥርቅም አድርጎ ዘግቷል። ለምን…? እባክዎን ወዳጄ ይሳተፉ… መንግስት ዘግቶ መጫወትን ለምን መረጠ…? እንደ “ሙዳችን” ፈቃድ መልስዎን ከፌስቡኩም ከብሎጉም ሰብሰብ አድርጌ ሌላ ጨዋታ ይወጣው ይሆናል።

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

5 responses »

  1. munia says:

    Very simple, because he thought he will win just like Chelsea. He totally changed his way of leadership into dictatorship. He thinks he can silence people by terrorizing, arresting and intimidation but he fails to remember what happened to his alike Gaddafi. Who knows soon it might be his turn. Oppressors will fall in their trap sooner or later.

  2. Etana says:

    ይሄ እኮ ቀላል ነው አቤ፤ ሜዳውን ሙሉ መሮጥና ማግባት ካቃተህ እግርም እየሰበርክ ትከላከላለህ። የኛ መንግስትም በ ምርጫ 97 ሙሉ ሜዳውን ከፍቶ ለመጫዎት ሞክሮ የነ ዶ/ር ብርሁኑንና ልደቱን የማጥቃት ስልት መመከት እንደማይቻል እንደ ቻይናና ቼልሲ ከመሳሰሉት በሙያው ልምድ ካካበቱ ቡድኖች ልምድ ቀምሮ ነው፤፤ ስለዚህ የኛ ጠቅላዮች የፖለቲካ ሜዳውን ከፍተን በውበትና በፉክክር ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ቢጫዎቱ የ 97 እጣ ገጥሟቸው ሩብ ፍፃሜ እንኩዋን ሊገቡ ቀርቶ ለውድድሩ እንኩዋን አትመጥኑም ይባሉ ነበር ሲል አንድ በቦለቲካና ኳስ እውቀቱ እልል የተባለለት ፀረ ኢህአዴግ ነግሮኛል፤
    የረባም አጥቂ እኮ የለውም መንግስታችን ከፌደራል ፖሊስ ውጭ። እነሱ ደሞ በጨዋታው ህግ መሰረት ነፍጥ መያዝ ስለማይፈቀድ ብቁ አይደሉም ሲል ይሄው ፀረ ምናምን አክሎ አስታውቋል፤፤

  3. Wegen says:

    Abe Mekelakel ena mekelkel are like air for them

    Metsaf Mekelkel , Menager Mekelkel , mederaget Mekelkel, Meret megzat Mekelkel,
    Meret meshet Mekelkel,Meselef mekelkel ,Demoz Chimari Mekelkel,
    Even during war time the boss of weyane had said they will fokes on `mekelakel“`

    I think we need first to get out for demonestration so that the word Mekelkel And Mekelakel be removed or at least to be banned from being used untill such time comew where there is a responsibel government for their proper usage.

  4. yiba says:

    you can make a mistake once like Chelsea did but not twice. Open competition is always in favour of those who play the game, the real game. When you know that you cannot play the game and you’re convinced that you will lose, you kill the game. I invite you to see the upcoming American Comedy called “The Dictator”, a story of a dictator who risked his life to ensure that democracy would never come to the country.

  5. Salewed Zeme says:

    Dear Abye

    Our friends are talking about the invitation of PM to the G8 submit. I don’t think Obama has to invite leaders from Eygpt, SA, Uganada. The issue to discuss is problem of food security, Ethiopia is the only country which suffer most. Thus, it is a must the leader of that country must, should and ought be invited and lectured. Because we are becoming nuisance to the world, we are not good news especially now……………
    Please teach them

    Adera mechem eskupini endematohgn new

Leave a comment