ሰሞኑን ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “አንድ ሀገር ብዙ ሃይማኖት” በሚል ርዕስ ዶክመንተሪ ፊልም አሳይቶን እንደ ቡና ደጋግመን ጠጥተነዋል።
ዶክመንተሪው ርዕሱ ደስ ይላል። እውነት ነው ኢትዮጵያ አንድ ናት እውነት ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሃይማኖት አለ መኖርም አለበት። (በመርህ ደረጃ ይሄ ትክክል ነው! (ወይ መርህ…! አትሉኝም!?)) የኢቲቪ ዶክመንተሪ ግን ሆነ ብሎም ይሁን ሰይጣን አሳስቶት አንዱን በአንዱ ላይ ጭራሽ የሚያነሳሳ ነው። ደግነቱ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነው። ደግነቱ ጣቢያው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው። እንጂ ሌላ “ጠብ ያለሽ በቲቪ ” ያለ ሀገር ቢሆን ኖሮ፤ ወይ ደግሞ ጣቢያው እምነት የሚጣልበት ቴሌቪዥን ጣቢያ ቢሆን ኖሮ አፋጅቶን ነበር! እያለ አስተያየቱን የሚሰጥ ሰው ተበራክቷል።

እስቲ በሰላም እየኖርን ያለንን ሰዎች ያኔ እንዲህ አድርገዋችሁ ነበር፣ ያኔ እንዲህ በድለዋችሁ ነበር እያሉ ማነካካት አግባብ ነው!? በእውነት ይደብራል።  ህዝቡ  እንደሆነ ነቄ ነው። ሙስሊሙም አብሮት ከኖረ ክርስቲያን ወንድሙ ጋር፣ ክርስቲያኗም ከቡና አጣጪ ሙስሊም እህቷ ጋር በኢቲቪ ቆስቋሽነት የተነሳ ለጠብ የሚጋበዙበት ዕድል የለም! በፈለጋችሁት እምላለሁ። ለማንኛውም አንድ ግጥም ብጤ እንሆ፤

ያኔ በደህናው ወቅት
ቆጥቤ እቁብ ጥዬ፣
የገዛሁት ቲቪ
ያወጋኛል ብዬ፣
አነሆ ዘንድሮ
አመሉን ቀይሮ፣
መረጃ ማቀበል
ማውጋቱንም ትቶ፣
ማዋጋት ጀመረ
ጎራ አስለይቶ።

በእውነቱ ይሄ ጉዳይ ያበሳጫል፣ ያቃጥላል፣ ያሳምማል። ብለን አብዝተን ስንማረር ደግሞ ግጥም ሁለት እንደሚከተለው ትወለዳለች፤

ሲበላሽ ሳስጠግን
ሳሰራው ከርሜ
ሲቃጠል ሳሳክም
በሌለኝ አቅሜ
ይክሰኛል ያልኩት
ይከፍላል ውለታ
ጭራሽ አሳመመኝ
ሰጠኝ ለበሽታ

ይቺኛዋ እንኳ የኔ ፈጠራ ውጤት አይደለችም። የሆነ ቦታ ነው የሰማኋት ወይ ከአዝማሪ ወይ ደግሞ ከእረኛ ነው የቀለብኳት። (ማን ብቻውን ይፎገራል!?) ለማንኛውም ይቺት፤

ማነው ጎበዝ ሰሪ
ማነው ጎበዝ ጠጋኝ
ኢቲቪን ሚያደርገው
እውነት እንዲያወራኝ!?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

3 responses »

 1. መለስ ናዚያዊ says:

  እኔ የምለው ሰዎቹ ጨርሰው አበዱ እንዴ እነዴት ነው ነገሩ ያ…………….ገር ካድሬ ሰብስበው እቱቱ ቡቱቱ ምናምን ምናምን ይሉናለ እኮ ነቄ ነንንንንንንንንንነ እእእ አይገባቸውም እነዴ ጨለሌዎች፡፡

 2. meretwork says:

  mot le woyane DELE LE EMYEE ETHIOPIA!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  THANKS!! Abte!!!!!! very soon Telat yedefa!!!!!!!!!!!!!! Free all prson”s!!!!!

 3. በለው! says:

  “የኢቲቪ ዶክመንተሪ ግን ሆነ ብሎም ይሁን ሰይጣን አሳስቶት አንዱን በአንዱ ላይ ጭራሽ የሚያነሳሳ ነው። ደግነቱ ሀገሩ ኢትዮጵያ ነው። ደግነቱ ጣቢያው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው። እንጂ ሌላ “ጠብ ያለሽ በቲቪ ” ያለ ሀገር ቢሆን ኖሮ፤ ወይ ደግሞ ጣቢያው እምነት የሚጣልበት ቴሌቪዥን ጣቢያ ቢሆን ኖሮ አፋጅቶን ነበር!

  *ኢቲቪ ተሳሳተ ማለት መልስ ዜናዊ አላዋቂ ጋጠ-ወጥ ናቸው ብሎ እንደማስወራት ይቆጠራል። አራት ነጥብ።

  ኢቲቪ “አውቆ በስህተት” “ሳያውቅ በድፍረት” የሚያደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ከሚበረታቱት ጥቃቅንና መለስትኛ ተቋማት አልፎ ከመከከለኛና ካደጉት የውሸትና የማባላት ተሞክሮ ካላቸው ተቋማት የሚመደብ ብቸኛው የኢህአዴግ እጀ ሥራ ነው።
  እጀ ጥበብ ፩… ብሔርን በብሔር የማነሳሳትና ነጣጥለህ ግዛ ሃያ አንድ ዓመት ያዘለቀ ሥልት!!!!!
  **”እስቲ በሰላም እየኖርን ያለንን ሰዎች ያኔ እንዲህ አድርገዋችሁ ነበር፣ ያኔ እንዲህ በድለዋችሁ ነበር እያሉ ማነካካት አግባብ ነው!?

  እጀ ጥበብ ፪… በነፃ ፍላጎታችን በሕግ የበላይንት እና በራሳችን ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን በመነሳት…ሕገ መነግስት ገጽ ፭..
  ***አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ? ? ከአጋር የፖለቲካ ፓርቲ እና ከዚህ መነግስት በስተቀር ሕዝቡ አማራጭ የፖለቲካ ድርጅት አያስፈልገውም ማናቸውም የሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚቋቋሙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁሉ እንደ ሁለተኛ ማህበረሰብ ይቆጠራሉ። (ሽበሩ)

  እጀ ጥበብ ፫… መብታችንን እና ነፃነታችንን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን አስፈላጊነት በማመን… ሕገ መንግስት ገጽ ፮…
  ****አንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ ? ? ‘ፊሲካል’ ‘ፊዚካል’ የአቶ መለስን የቃላት ማጭበርበርን …የአቶ ተመስገን ዘውዴ ይህንን መልስ ያስታውሱ !! ” እኔ እንደ እርስዎ እንግሊዘኛውን ባላፏጭበትም” …ፊሲካል ባላንስ !!
  እንግዲህ አንዱ ሻጭ አንዱ ደላላ ሌላው ገዢ ሆኖ ለተበዘበዘች ሀገር የአንድን ፓረቲ የበላይነት ለመሸፈን ቆርጦ ለመቀጠል አንድ የቲቪ ጣቢያ አይበቃም? ?
  *******************************
  ዘመን አልፎ ዘመን መጥቷል !
  ድሮ ቀረ ማን አሮጌ ይጠግናል?
  መጣል ነው አሽቀንጥሮ ልዋጭ ባይ የትአል?
  ጊዜው ተጠቆሞ የመጣያ የባለሀብት ሆኗል !
  መካሪ አስተማሪ አስተባባሪ ይመጣል
  መልካም ሠሪ አዲስ መፍጠር ይቻላል !
  ይህንን ቀጣፊ ደባሪ ቲቪ ቀይሮ
  ሳቅ ጨዋታን መፍጠር አብሮ ::!!!
  ይመቻችሁ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s