ትላንት ሁለት አሳዛኝ ዜናዎች ሰምቼ ደብቶኝ ነበር የዋልኩት። ሲጠበቅ የነበረው የእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ “አሸባሪ ናችሁ!” በሚል ፍርድ መደምደሚያ አግኝቷል። ቀጣዩ ምን ይፈረድባቸው ይሆን? የሚለው ነው። ጊዜውን ጠብቆ አብሮ የምናየው ነው። ነገር ግን አንድ ጥይት እንኳ ተኩሰው የማያውቁ ግለሰቦች “አሸባሪ” ተብለው በይፋ ሲፈረድባቸው ስናይ ድብርት ሲያንሰን ነው!
ሌላው አሳዛኝ ዜና ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ በኮንቴይነር ውስጥ ታጭቀው እየኮበለሉ ከነበሩ መቶ ምናምን ስደተኞች መካከል ወደ አርባ አምስት የሚጠጉት ህይወት ማለፉ ነው። እኔ የምለው መከራችን አልበዛም ትላላችሁ!? እዛ እስር እዚህ ሞት… የት ሄደን እንፈንዳ…!?
ልብ አድርጉልን ከኛ የባሱ ካድሬዎች ሀገራችን እድገት በእድገት ናት ጥጋብ በጥጋብ ናት በሚሉበት በዚህ ወቅት ነው ይሄ ሁሉ ሰው በስደት ላይ የሚያልቀው! ውድ ካድሬዎቻችን አነዚህ ሰዎች ለሞት ያበቃቸው ስደት ከምን የመጣ ይመስላችኋል!? ወይስ ደልቶናል ጠግበናል የሚለው መግለጫ የፓርላማ አባላቱን ብቻ የሚመለከት ነው?
ወዳጄ በእውነቱ አሁንም ቢሆን ድብርት ላይ ነኝ! ለማንኛውም የአንዷለም አራጌን የመጨረሻ ንግግር እና የበዓሉ ግርማን አንዲት ግጥም እንደሚከተለው ልጋብዝዎ…
ለራሴ፣ ለልጆቼ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ !
ያሳለፍነው ግማሽ ምዕተ ዓመት የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰብአዊ ክብሩና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የታገለበት ዘመን ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ባለቤት ለመሆን እስካሁን አልታደለም፡፡ እኔም በተፈጠርኩበት በዚህ ዘመን ለራሴ፣ ለልጆቼና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ዴሞክራሲና ነፃነት እንደሚገባን በማመን አቅሜ በፈቀደው መጠን ታግያለሁ፡፡ ይኼን በማድረጌ በማንም ላይ በክፋት አልተነሳሁም፤ ይኼን በማድረጌ ህግ ጥሼ አላውቅም፤ ይኼን በማድረጌ በደሃዋ ሃገሬ ጥቅም ላይ አልተነሳሁም፤ ይሄን በማድረጌ ፈጣሪዬን፣ የኢትዮጵያን ህዝብም ሆነ ህሊናዬን የሚያሳዝን አንዳች ነገር ፈፅሜያለሁ ብዬ አላምንም፡፡ ፍፁም ሰላም ይሰማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ፍትህን ለምኜ ስነፈግ ይኼ የመጀርያዬ አይደለም፡፡ ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ፅዋ በፀጋ ከመጠጣት ውጪ ባልፈረፀምኩት ወንጀል ማቅለያ የመጠየቅን አማራጭ ህሊናዬ ስላልተወልኝ አዝናለሁ፡፡
ነፍሱን ይማረውና ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ በኦሮማይ መፅሐፉ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር።
sad story!!!!!
My heart goes out to all of the victims and their families.
እጅግ ዘግናኝና አሳዛኝ ዜና! መቼ ይሆን በቃችሁ የምንባለው? አሞራ እስከ መቼ ድረስ ነው የሚበላን? ኤሎሄ፤ኤሎሄ፤ኤሎሄ!!!
I couldn’t stop crying….
The expection of the rihgteous ones is a rejoicing” but the very hope of the wicked ones will perish”Because of the goodness of the righteous ones a town is elated,but when the wicked ones perish there is a joyful cry!!
May God bless you and keep you!
“ወደ ደቡብ አፍሪካ በኮንቴይነር ውስጥ ታጭቀው እየኮበለሉ ከነበሩ መቶ ምናምን ስደተኞች መካከል ወደ አርባ አምስት የሚጠጉት ህይወት ማለፉ ነው። እኔ የምለው መከራችን አልበዛም ትላላችሁ!?
በዛ ተንዛዛ “በቃ” ሲባል “በእቃ” የተባለ መስሎታል በእያይነቱ ግፍን እየሰፈረ ይሰጠናል ጎበዝ ” እንቢኝ ! እንበል !!!
*ከሁሉ አስቀድሞ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን ማድረግ የሚችል አምላክ ዓላማቸው ሳይሳካ በለጋ ዕድሜአቸው የተቀጩትን ነፍስ ይማር! ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሥለ እነሱም ላሰቡና ላዘኑ ሁሉ ጌታ ፅናቱን ይስጣቸው። በአጋጣሚ ከመፅዓቱ የተረፉትንም ጌታ ብርታትን ይስጥልን!
**ህዝባችን ጠግቦ ለሽርሽር ሳሆን መድረሻ አጥቶ፣ ተጨንቆ፣ ተማሮ፣ ተርቦ፣ተጠምቶ፣ተዋርዶ፣አዘኖ እና አፍሮ ነው ። ይህም ሐሰት ነው ወጣቱ ሥራ ንቆ ነው !እያላችሁ በውጭው ዓለም ወሬ በማናፈስ በእየ ኤምባሲው,በሃይማኖት ተቋም,በንግዱ ዘርፍ, በተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያ (ድረ ገፅ) ላይ ተለጥፋችሁና ተደብቃችሁ የምትቀሳፍቱ ውሸታሞች ሌቦች የእጃችሁን ታገኛላችሁ።
***በሀገርም ውስጥ ያላችሁ ካድሬ,አውርቶ አደር,የገበሬውን ልጅ ወደ ከተማ ሄዶ ድንጋይ እነዲሸከም የገፋፋችሁ,ሲሚንቶ ሲጠፋ ከሀገር ጥፋ እያላችሁ ያጠራቀማትን ነጥቃችሁ ዶላር ወደሚታፈስበት ሂድ ስትመለስ (ኢንቨስተር ትሆናለህ!) እያላችሁ ከመንግስት ባለሥልታናት ጋር ሻጭ እና ተቀባይ ሆናችሁ ዘመናዊ የሰው ልጅ ንግድን በሕጋዊ ፈቃድ የምትሰሩ
ደላሎች, የክልል ሹማምነቶች ከሗላ ዞራችሁ እናት አባቱን አፈናቅላችሁ ወራሽ ልጅ የለህም መሬቱ ይፈለጋል እያላችሁ ከተወለደበት አግብቶ ወልዶ ከከበደበት ቀዬ አዛውንቱን አፈናቅላችሁ፣ ቅሌን ጨርቄን ሳይል ገበሬውን ለማኝ ያደረጋችሁና በሀገሩ መጤ ሆኖ መብቱ በሕግ ተጠበቀ፣ እኩልነቱ በሕገ መንግስቱ እውን ሆነ ተረጋገጠ (ተረገጠ) የምትሉ፣ የዘረኝነት እና የተዋረደ ኑሮ በየትኛውም ሥርዓት ይህን ያህል ብልግና ደርሶ ነበር ለማለት ለማነፃፀርም ይከብዳል። ****የደርግም አፈ ቀላጤዎች፣ካድሬዎች፣ሠራዊቱን ጨምሮ የህዝብ ሰቆቃ ሲበዛ ፊቱን ወደ ሕዝብ መልሶ በሩን ከፍቶ አስገባችሁ ህዘቡም ጨዋነቱን ሰላም ወዳድ መሆኑን የዓለም ታዛቢን አስገርሞ “የዴሞክራሲ አብዮተኞችን” ተቀብሎ አብሮ ለመሥራት ሞክሯል የተሰጠው ምላሽ መሐይም፣ደንቆሮ፣ፈሪ፤ እየተባለ ስድብ እና ውርደትን ሆኗል። ወደፊት ይህ ሕዘብ የሚሰጠው ምላሽ ከደርግ ወደ ወያኔ የነበረውን አይነት ሽግግር ይኖራል ብላችሁ አፋችሁን ባትከፍቱ ጥሩ ነው።ህዝቡን እልህ ውስጥ ከታችሁ እርስ በእርሱ እንዲባላ መልካም ሐይማኖቱን፣ ሥነምግባሩን ትዕግስቱን አሟጦ ለበቅል ለመጠፋፋት እንዲነሳሳ ጥሩ ትምህርትን እየሰጣችሁ መሆኑን ከአሁኑ ልትገነዘቡ ይገባል “ትሻልን ፈትቼ ትብስን … አይ የዚህ ትውልድ መከራ እና ፍዳ !! የቀጣዩስ ትውልድ ዕጣ ፈንታ ? ? ይህ ህዝብ እየመረረው በመጣ ቁጥር የሚመረት የሸንኮራ አገዳ፣የስኳር ድንች፣ የሚገነባ የሱኳር ፋበሪካ ይበቃል ብዬ አልጠብቅም ሆኖም ከሚመረን ይማረን !!!
አሜን በለው!
>>>የብሔር ብሔረሰቦች አባት ከተናገሩት “የሱዳን ሕዝብ የእኛን አትንካ ያነትን እንካፈል እየተባለ አነገቱን ደፍቶ ሲሞኝ የኖረ ሕዝብ ነው።የእኛ ዕድገት ለጎረቤቶቻችንም መዳረስ አለበት” በሰሜን ማስገንጠልን ወደብ ማሳጣትን ጀምረው ባድሜን ምራቂ ሰጥተው፣ ከወሎ እና ከጎነደር መሬት ቦጭቀው ለታጋይ ኢንቨስተሮች አካክሰው ከጎንደር እስከ ጋምቤላ መሬት ለጎረቤት ሀገር በመቸር ለኬንያና ጅቡቲ የመብራት መዳረስ ተግተው በመስራት ሥልጣናቸውን አረጋጉ የራሳችን ዜጎች የሚበሉት የለም፣ የሚሰፍሩበት የለም ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ የብሔሮች ዕኩልነት በቅሌት ተረጋገጠ…!!
ባለፉት ፲፪ ዓመታት ታየቶ በማይታወቅ መጠን የህዝብ ፍልሰት በዓለም ጨምሯል ባለፈው ፰፻፼ ሺህ ስደተኛ ፻፵፼ ሺህውን ኢትዮጵያ ተቀብላለች ? ማለትም ፲፰ ከመቶውን የኤርትራ,የሱዳን,የሱማሊያ መሆኑ ነው። ይህ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ድሮም የተመሰከረልን የእንግዳ ተቀባይነት የሕግና ፍርሃ እግዝሐብሔር ያለን ሕዘቦች ለመሆናችን ዓለም በድፍረት ይናገራል።
በዚያን ዘመን ግን ከሀገሩ ለትምህርት ውጪ የተላከ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ወይ ሀገሬ ብሎ አልቅሶ የሚመለስባት ሀገር በነበርች ጊዜ ነው። ለሥራም የመጡ የውጭ ዜጎች አንሄድም እያሉ አልቅሰው የሚቀሩ ነበሩ አሁንም አሉ። ዛሬ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የተከለከለች፣ ዜጎቿ የሚጠሏት፣ የሚሸሿት፣ የሚጠየፏት፣ድሃ የሀብታሞች መሬት፣በአብዮት የተቃጠለች ሀገር፣ኢኮኖሚዋ በወርቅና ቡና ሳሆይን በአህያ ቆዳ የሆነ፣ አማርጦ መብላት ሳይሆን አማሮ የሚኖርባት፣ጮማ የሚቆረጥባት ሳይሆን ተስፋ የተቆረጠባት ሀገር፣ዛሬ ኑሮ ውድነት እነኳ ሲነሳ ያለን የስደተኛ ቁጥር እየተባለ ፻፰፼ በራሳቸው ወጪ የሚኖሩ ሱማሌያውያን አሉብን አሜሪካ ለመውሰድ ቃል ከገባው ስደተኛ ውስጥ በ፪፼፫ዓ.ም በቁጥር ፭ ሱዳኖችን እና ፯፼ ኤርትራዊያንን ብቻ ነው የወሰደችው?
እዚህ ግራ የሚያጋባው ነገር ኢትዮጵያዊው ወጣት በእየ ወሩ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይሸጣል ፣ይደፈራል፣ ይታሰራል፣ይታመማል፣ ከቆሻሻ መድፊያ እየበላ በእየ መንገዱ ዳር ይተኛል፣የመንግስት ሆስፒታል ተጨናንቋል፣ህፃናት ይሞታሉ፣የመንግስት ት/ቤቶች ህፃናት ላይ ሊወድቁ ነው።በ፳፩ኛው ክ/ዘመን ንፁሕ ውሃ በዋና ከተማው የለም፣ዛሬም መብራት በወረፋ ነው፤፪፩ ዓመት መንግስት የሌላት እኛ የምናስጠጋቸው የምንከባከባቸው ሱማሌዎች ህገ መንግስት ካላት ከመካከለኛ ለማኞች ተርታ ተሰልፈን ፎቶ ከምንነሳ ማፈሪያዎች የተሻለ ኢንተርኔት አላቸው። ከብሔር ብሔረሰቦች ከቃላት ማምታታት ሁሉም ብሔሮች በአንድ ሀገር እኩል የመጠቀም መብት !!!
በተለያየ ቋንቋ ለአንድ ዓላማ በሕብረት ድምጻችንን ማሰማት ፍትህ! እኩልነት!ሰላም! ነፃነት! ነፃነት!ኢትዮጵያዊነት!!>>>>
…”ሲጠበቅ የነበረው የእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ “አሸባሪ ናችሁ!” በሚል ፍርድ መደምደሚያ አግኝቷል። ቀጣዩ ምን ይፈረድባቸው ይሆን? የሚለው ነው። ጊዜውን ጠብቆ አብሮ የምናየው ነው። ነገር ግን አንድ ጥይት እንኳ ተኩሰው የማያውቁ ግለሰቦች “አሸባሪ” ተብለው በይፋ ሲፈረድባቸው ስናይ ድብርት ሲያንሰን ነው!”
“ያለ ማስርጃ የታሰረ አንድም የለም !ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን የፓረረላማው ሰብሳቢ ዓቃቢው የመልስ ዜናዊ ቃል….ነበር ያሸባሪው አዋጅ ፮፻፭፪(፪፼፩) አነቀጽ(፫) (፬) አንቀጽ ፯(፪) በመተላለፍ በቀረበባቸው ፴ መስክሮች እና ፭፻፵ ማስረጃ መከላከል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ተብለው ለፍርድ ሀምሌ ፮/፪፼፬ ተቀጠረ።”
አንቀጽ ፫ የሽብርተኝነት ድርጊት…
-መንግስትን ሕዝብን ማስፈራራት የሕገ መንግስታዊ ኢኮኖሚያዊ ወይንም ማህበራዊ ተቋማትን በማናጋት ወይም መማፍረስ ሰው የገደለ፣ የሕዘብን ክፍል ደህንነት ወይም ጤና ለአደጋ ያጋለጠ፤እገታ ወይም ጠለፋ የፈፀመ፣በታሪካዊ ወይም ባህል ቅርስ ላይጉዳት ያደረሰ፤በቁጥጥር ሥር ያደረገ ያቋረጠ ወይም ያበላሸ እንደሆነ፡…
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ለመፈፀም የዛተን ጨምሮ ከ፲፭ ዓመት እስከ ሞት በሚደርስ ቅጣት ይቀጣል።
አንቀጽ ፬ ማቀድ መዘጋጀት ማሴር እና ሙከራ..
-ማንም ሰው የፖለቲካ የሀይማኖታዊ ወይም የአይዲዮሎጃዊ አላማን ለማራመድ በአንቀጽ ፫ ላይ የተዘረዘሩትን ለመፈጸም…
አንቀጽ ፯ (፪) በሽብርተኝነት ድርጅት ውስጥ ስለመሳተፍ…
-በሽብርተንነት ድርጅት ውስጥ በአመራርነት ወይም በውሳኔ ሰጪነት የሰራ ከ፳ ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ
እስራት…
ቀጥሎ የተጠቀሱት ሁለት አንቀፆች የተዘለሉት የቅጣት ጣራው በማነሱ ብቻ ነው።!!!? ? ?
***አንቀፅ ፭ ለሽብርተኝነት ድጋፍ ስለመስጠት… ከ፲ እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት
***አንቀፅ ፮ የሽብርተኝነትን ድርጊት ማበረታታት…ከ ፲ እስከ ፳ ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት
እነኝህን ንፁሃን ወጣት የኢትዮጵያ ልጆች እንደባዕድ የእድሜ ልክ ወይንም የሞት ፍርድ የሚስፈርድባቸው ምንድነው? ፩) ግለስቦቹ በቁጥጥር ሥር ከመዋላቸው ከሳምንት በፊት ባለ ሰባት ገፅ “ጥናታዊ ፅሑፍ “አቅርበዋል ፤ ፪) በጋዜጣ የሚፀፏቸው ጽሑፎች ፅንፈኞች ነበሩ “ትግሉ ወደ ሰላማዊ ተግባር ይሸጋገር”! ብለው መፈክር አሰሙ፤ ፫) ሕገ መንግስቱ በ፪፼፬ እንደሚወድቅ ተንብየዋል፤
፬) በሰላማዊ እና ሕጋዊ መንገድ ታሪክ ይሰራ ብለዋል፤
፭) የሌሎች ሀገሮች ላለፉት ሃያ ዓመታት ሥልጣን መቀያየሩን ኢትዮጴአ ያንን አለማስተናገዷን ተናግረዋል፤
፮) ኢህአዴግ ለሃያ ዓመታት(በኮንትራት) ፺፱.፮ በሕዝብ ተመርጦ ደክሞታል በሌላ ይቀየር ዕረፍት ያስፈልገዋል ብለዋል፤ ፯)ሀገሪቱ ለውጥ አርግዛለች ሥርዓቱን ለመጣል ብለው ጥሪ አስተላልፈዋል፤
፰)ተቃዋሚው በፓርላማ ያለው መቀመጫ ከ፻፸፰ ወደ አነድ ግለሰብ መቀምጫ በ፪፼፩ ዓ.ም ማደጉን አሰምተዋል፤ ፱) ሌሎች አምባገነን ሀገሮች ለደጋፊዎቻቸው ገንዘብ ሲለግሱ ኢህአዴግ ገንዘብ ወስዶ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ድለላ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስት ከ፩ ሚሊየን ወደ ፬ሚሊየን ደጋፊ እንዳለው አጋልጠዋል።
፲) የውጭ የበጎ አድራጊ ድርጅቶች በሀገር እንዲገቡ ግን ኢህአዴግ እጁን እነዳያስገባ ተከላክለዋል፤
፲፩)አብዮት ኮሌራ,አንበጣ,ከውጭ የሚገዛ ሳይሆን ሕዝቡ እራሱ ‘ሆ’ ብሎ ካልተነሳ የማይገኝ መሆኑን አላወቁም፤
በማለት የክስ ጭብጡን በዝርዝር የፃፉ ዘመነኛ ጋዜጠኛ(አድመኛ)(ምንደኞች) የጠ/ሚ ፓርላማ ፍርድ በመደገፍ …
“የሞተ ህዝብ አብዮት አይለኩስም” ሲሉም ሕዘብ የሚሳደቡ ካድሬዎችም አስገርመውናል፣ የብሔር ብሔረሰብ ለ፻ ዓመት ማንነታቸው በሕግ ዕውቅና ተነፍጓቸው የኖሩ ወፍ ዘራሽ, እንስሶች ናቸው ከኢህአዴግ ሌላ አማራጭ የላቸውም ይላሉ።
አይጋ ፎረም ፰/፳፪/፲፩ ኢበሳ ነመራ ካቀረበው ባለ ፳፬ ነጥብ ውንጀላ እና የአቃቢ ህጉና የአምንደኞችን የፓረቲ አመራሮችን በጨረፍታ ውስጣዊ ሚስጥር እስከ ፍርድ አካላቱ ዘርፍ ያለው ትስስር በጥቂቱ…
የተጠቀሱት አንቀጾችና ምስክሮች በማቀራረብ ሕግን እንደልብ ወለድ ድራማ ከሚያስቁ ማስረጃዎች ጋር እንመለከታለን<<<
ሞኛችሁን ፈልጉ ኢትዮጵያዊ ነኝ በለው!!!!
“ቀጣዩ ምን ይፈረድባቸው ይሆን? የሚለው ነው። ጊዜውን ጠብቆ አብሮ የምናየው ነው። “በክስ መዝገባቸው ከሰፈረው
ከመፈክሩ እንጀምር …ፍትህ ..በተለወጠ አመራር! በተለወጠ ሠራተኛ! በተለወጠ ተቋም!
የፌ/መ/ቁ ፩፻፹/፬ የክሱ ይዘት ያው የፈረደበትን ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በፅሑፍ አሸበሮ ለመጣል…
የሚያነሳሱ ንግግሮችን እና ቃለ መጠይቆችን በመስጠት ፣አባላትን በመመልመል፤ መመሪያና የገንዘብና የሞራል ድጋፍ በመስጠት፤ ሻቢያ ያቀደውንና ያለመውን የትርምስና የብጥብጥ አመፅ ዓላማ ለማነሳሳት ተግባር በመፈፀምና እነዲፈፀም በማድረጋቸው፤ሰነዶች እና ፅሁፎችን በኢሜል ሀገር ውስጥ በማሰራጨት የሚሉ ልብወለዶችን ያካተተ ሲሆን…
አሁን ለመግደል(የሙት ፍርድ) ማድረግ አዋጪ ኢንቨስትመንት ሆኖ አልተገኝም ያለ ወጪ ከ፳ እስከ ፳፭ ዓመት አንዳንዶችን በዕድሜ ልክ ቅጣት አስፈራርቶ ወደ ይቅርታ እና ሽምግልና አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መደረስ መቻል አለበት።ስለዚህ ለሚቀጥለው ለመታሰር በአይነ ቁራኛ ለሚጠበቁ ተረኞች ይረዳ ዘንድ የገንዘብ የቅጣት ጣራውን ከፍ የማድረግ ቦንድ የማስገዛት አዲሱ ሥልት ይሆናል።
**ስለማስረጃ አቀራረብ ከቲዎድሮስ ካሳሁን (አፍሮ) አንድ እንዋስ ቴዲ ግለሰቡን መንገድ መሐል ላይ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ከአስር ደቂቃ ገጨው ግለሰቡ ስምንት ሰዓት ከአስራ አምስት ደቂቃ ዳግማዊ ምንይልክ ሆስፒታል ደረሰ!! ? ? ለመሆኑ አንቡላንሱ ክንፍ ነበረው ወይ ግለሰቡ እነደሚገጭ አውቆ በተጠንቀቅ ይጠባበቅ ነበርን ብለን ጠይቀን ተገርምን በሳቅ.ቅ.ቅ !
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
በዚህ የክስ መዝገብ ላይ ግን በምንም ዓይነት ሰዓት ቦታና ቀን አይገልፅም ወንጀል ሊፈፀም ነበር። ( ጥርጣሬያዊ ግምት)
አንቀጽ ፳፫ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች (፪) የስሚ ስሚ ወይንም በተዘዋዋሪ የተገኙ ማስረጃዎች…
ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ የታስሩት ሁሉ ወንጀለኛ ናቸው በቂ ማስረጃ አለን አሉ ሕዘቡ ከእሳቸው የስሚ ስሚ ሰማ በለው! የ ፴ የሰው የምስክሮች ቃል እና ፭፻፵ ማስርጃ በጨረፍታ ለናሙና የተወሰደ…..አንቀጽ ፳፬ ችሎቱ ያደረበትን አንብቡ!!
***ግለሰቡ ባለ አስራ አምስት ነጥብ የአመፅ ጥሪ ወረቀት ሲበትኑ ምን እንደሚል አላነበቡትም፤
***የሚበተነው ፪፼ ወረቀት ተባዝቶ ሊያልቅ ፪፻ ሲቀረው እቦታው ደርስኩ፤
***ፋሲል የእኔዓለም ፳፬ኛምስክር ተሰፋሁን አናጋው ሀይሌ ደውሎ አንዱዓለም አራጌ የሚመራው ቡድን እንዳለ ነገረው፤ ***አነዱዓለም አራጌን እና ናትናኤልን አገኗቸው ቦታውን ግን አየቁትም፤
***ሕጉ እስረኛን ማስመስከር ሲከለክል ዘመኑ ሞላን ከእስር ፈቶ አስጠንቶ እና አሰልጥነው መስካሪ እንዲሆን አደረጉ፤ ***’የፉት ቦል ክለብ በሚል ሽፋን’ በቦሌ እና በቄርቆስ አባላት ተመለመሉ እንዴት ከግነቡት ፯ ጋር እንደሚገናኝ አያቁም፤ ***፳፰ኛው ምስክር አቶ አበበ ታፈሰ መደበኛ ሥራቸው የታክሲ ሹፌር, የሽጉጥና የቦንብ ስልጠና ወስደዋል, ኮምፒውትር ት/ርት ወስደዋል, እቤታቸው ኮምፒተር የለም እንዴት እንደሚከፈት አያውቁም የአዋሳቸውን ሰው አያውቁም፣ ተደብቀው ስለ ግንቦት ፯ ዓላማ ስለ ኤርትራ የጉዞ ካርታ ሲያጠኑ ነበር ፤ከጎንደር ኤርትራ ሌላው መስካሪ ፯ ነበርን ሲል እሳቸው ሁለት ብቻ ነበርን ሲሉ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ? እኛም የቤታችን ጉድ ብለን ተገረምን…ምነው ሸዋ ! !ሰው ጠፋ በአገሩ ? ? ? ውጤቱ ምንም አጓጚ አደለም አውቀነዋል በለው! በተመስገን ደሳለኝ የሁለት ሺህ ቦንድ መግዛትም ያላገጥንባችሁ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከሀገር እንዲወጣ ወይንም በሌላ ወንጀል አቅርባችሁት ይህንን የገንዘብ ቅጣት ተንተርሳችሁ እነደሁለተኛ ጥፋት ልትጠቀሙበት ማሰባችሁን ድሮውንም አውቀነዋል።አላጭበረበራችሁም ተጭበርብሮባችሗል ተረጋጉ ሕዝብ ካለፈው ተምሯል! ተማሯል! ተሞርሙሯል! ፍትሕ ይከበር! ይህ ሕዝብ ሰላም ኖሮት ተመስገን ብሎ ይኑር ተውት!! ^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^