እኔ የምለው ወዳጄ ቅድም ስለ በእውቀቱ ስዩም ጉዞ ሳወራ አብሬው አነሳዋለሁ ብዬ ስደተኛ እንደመሆኔ መጠን ቀልብ አጥቼ የራሳሁት አንድ ጉዳይ አለ… ምን መሰልዎ…!?

ታዋቂዋ ተዋናይ መሰረት መብራቴ ከሀገር ወጥታ አሜሪካ ጥገኝነት ጠየቀች የተባለው እውነት ነው እንዴ!? መቼም ምን ሆና!? ብሎ መጠየቅ አግባበብ አይደለም። ምክንያቱም “ጉዳችንን” መቼ አጣነውና!

መሰረት መብራቴ በቀጥታ ከፖለቲካው ጋር የሚያገናኛት ነገር ባይኖርም ሁሉን ሰብስበው መያዝ የሚፈልጉ ዋና “የሴራ” ሂደት ባለቤቶች መሰረትንም፤ “የኢህአዴግ ንብረት ነሽ አለበለዛ ወዮልሽ!” አይሏትም ለማለት አያስደፍርም።

እውነቱን ለመናገር በአቶ በረከት ስምዖን የመፅሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝቶ፤ “ከመፅሀፉ የተመረጠ አንድ ክፍል አንብብ” መባል እንኳንስ መሰደድ ጫካ መግባትም ያሰኛል። ሰውየው የኢህአዴግ ባለስልጣን ስለሆኑ አይደለም እንዲህ የምለው… “እህ” ይበሉኝማ፤ ባለፈው ጊዜ በጣም የምናከብረው ፍቃዱ ተክለማሪያምን ጨምሮ ሌሎችም “አርቲቶች” የሁለት ሀውልት ወጎች መፅሐፍ ( ይቅርታ ወዳጄ  የሁለት ምርጫዎች ወግ በሚል ይስተካከልልኝ… ይህንን መፅሐፍ ከዚህም በፊት ስሙን አሳስቼው ሰው ነበር ያረመኝ። አቶ በረከት ርዕስ ሰርቀው እኛንም ግራ አጋቡንኮ!)   እናልዎ…  በምረቃው ላይ ከመፅሀፉ የተወሰነ ክፍል በዕለቱ ለነበረው ታዳሚ እንዲያነቡ ታዘው ነበር። “ትዕዛዝ አይደለም” የሚለኝ ካለ፤ “የጌቶች ልመና ከትዕዛዝ እኩል ነው” የሚለውን የአበው ንግግር አስታውሳለሁ።

ታድያ በዛ ምረቃ ዕለት አንጋፋው ፍቃዱ ተክለማርያም እያነበበ ሳለ አንድ እንኳ በቅጡ የሚሰማው ሰው አልነበረም። ራሳቸው የአቶ በረከት ስምዖን ሳይቀሩ ውስኪያቸውን እየጨለጡ ወሪያቸውን ሲያቀልጡት ነበር። (ካላመኑኝ “ዩቲዩብ” ይመስክር!) ምስኪን ፍቃዱ ተክለማርያም ግን በሞቅታ ውስጥ ላሉት ባለስልጣኖች ንባቡን ቀጥሏል። በእውነቱ እኔ ፍቃዱን ብሆን ኖሮ የአፄ ቴውድሮስን ሽጉጥ የምመኘው ይሄኔ ነበር! ለአንድ ተዋናይ መድረክ ላይ ስራ አቅርብ ተብሎ አለመሰማትን ያህል ውርደት የትም የለም። በእርግጥ ሰዎቻችንም ቢሆኑ አርቲስቶቹን እጃቸውን እየጠመዘዙ አብራችሁን ኳስ ተራገጡ አብራችሁን መሸታ ጠጡ የሚሉት ወደዋቸው እንዳልሆነ ይታወቃል…! እናስ? የተባለ እንደሆነ አርቲሰቶቹ ያላቸውን የተቃባይነት በረከት ለመቋደስ እንደሆነ ግልፅ ነው።

እናም መሰረት መብራቴም እንዲህ አይነት ተደጋጋሚ እጅ መጠምዘዞች አይደርሱባትም ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ፍሬንዶቼ ሰዎቹ እኮ አምርረዋል።  በዚሁ ሰሞኑን ተመስገን ደሳለኝ ላይ የደረሰውን ማንሳት እንችላለን!

እኔ የምለው ትላንት ፍትህ ጋዜጣን በኢንተርኔት ተመልክቻት ነበር። “ፍትህ እና አልሸባብ ምን አገናኛቸው!” በሚል ርዕስ ተመስገን የፃፈውን ተመልክቼ በጣም ነው የተደነቅሁት። እኔ የምለው ሰዎቻችን ይሄንን ያህል ወርደዋል!? ተዋርደዋል እንዴ…!? አረ ሼ…!

አንዴ… ቆይኝማ ደብዳቤውን ላላያችሁት ወዳጆች  እዚሁ ላይ ላምጣምውና እንየው ድጋሚ እስቲ…

“To Ato Temesgen Desalegne

Chief Editor of Fitih magazine

Ethiopia

It has to be remembered that AlShebab has assigned me secretly to make propagation activities in Ethiopia, Somaliland, Kenya and Uganda. To accomplish the task we have agreed with you through your representative Ato Mamush Sentie in Eritrea to publish propaganda articles against the Ethiopian government, against the interest of the Ethiopian people and the American government. It has to be remembered that we have paid US dollar 24,000 for 30 consecutive editions. Now alshebab has made strategic change to accomplish its tasks. Therefore we need the 14 edition charges US dollar 11,200 dollar to alshebab. We believe that you will return back the money to our organization. If this is not fulfilled on time you will bear a cost on your representative Ato Mamush Sentie and your life according to the rule of the organization.

Alshebab wins

Ahmedin Nasir”

ተመስገን በፅሁፉ ላይ እንደነገረን፤ እኔም በበኩሌ የዚህን ደብዳቤ የእጅ አጣጣል  በፍፁም የአልሸባብ ነው ብሎ ማመን ይከብደኛል። ይህ ኢሜል ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነው የተላከው ብዬ ደፍሬ ለመናገር ባልችልም፤ ከኢትዮጵያን ሄራልድ መሆኑ እንደማይቀር ግን 99.6 % እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ!

እስቲ አስቡት ተመስገን ደሳለኝ የኢትዮጵያን መንግስት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እና የአሜሪካንን መንግስት ጥቅም የሚፃረር ፕሮፖጋንዳ ለአልሸባብ ለማተም ሲስማማ…! ምናለበት “የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ” የሚለውን እንኳ ቢያወጡት! ይሄ ግፍ ምናምን የሚባለው ነገር ቀረ እንዴ…!?

ሌላው ይህ “የአልሸባብ” ተወካይ እንደሚለው ከሆነ ተሜ 30 እትሞች ላይ እኛን መንግስታችንን እና አሜሪካንን የሚጎዳ ፕሮፖጋንዳ ሊያወጣ 24 ሺህ ዶላር ተቀብሏል። አንግዲህ አሁን መልስልን የተባለው 11200 ዶላር ነው። ያም ማለት ከግማሽ በላይ ፕሮፖጋንዳውን ተግባራዊ አድርጓል ማለት ነው። እስቲ የትኛው የፍትህ ጋዜጣ ፅሁፍ ነው “አልሸባብዬ የኔ ጌታ አይዞህ በርታ በርታ…!” የሚል ይዘት ያለው!? በበኩሌ ከሀጥያቴ የተነሳም እንደሆነ እንጃ እንዲህ አይነት ፅሁፍ ፍትህ ጋዜጣ ላይ አይቼ አላውቅም! እናንት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ብፁህ የሆናችሁ ትመሩኝ ዘንድ እለምናለሁ!

እርግጥ ነው ፍትህ ጋዜጣ የመንግስትን እንከን ፈልገው ከሚተቹት ጋዜጦች ወገን ናት። እንደውም አውራ ናት ማለት ይቻላል። ይህም የኢትዮጵዩያ ህዝብ ፍላጎት ለመሆኑ ሁላችንም “ቀፈፈኝ” ብለን ስንወጣ፤ እርሱ የመጣው ይምጣ ብሎ በፃፈ ቁጥር የአንባቢው ምላሽ እንዴት እንደሆነ ራሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኤጀንሲን ጠይቆ መረዳት ይቻላል።

ለማንኛውም ባለፈው ጊዜ የሰማናት ጭምጭምታ እውን ልትሆን ይመስላል። ከዛም በተጨማሪ ሰዎቻችን ከበድ ያሉ ጥቃቶችንም ሰንዝረውብን “አልሸባብ አደረገው!” ሊሉን ይችሉም ይሆናል። በእውነቱ ይሄ ምንም ባልታጠቀ ህዝብ ላይ ጣንያን የተጠቀመው የአውሮፕላን ድብደባ ጋር ይመሳሰላል ብል ምንም ማጋነን አይሆንም… ከሆነም ይሁን…(ደሞ ለማጋነን! ይህው መንግስታችን ስንት ነገር ያደርግ የለም እንዴ!?)  እና በፀሎቱም በጥንቃቄውም መትጋት ያስፈልጋል። የሰማሃት ጭምጭምታ ምንድናት? ብሎ የጠየቀ መልሱን በአዲስ መስመር ያገኘዋል።

መንግስት ተጨማሪ ሰዎችን በአሸባሪነት ክስ ሊጠረንፍ አስቧል አሉ። እዚህ ውስጥ ፍትህ ጋዜጣ ነፃነት ጋዜጣ እና አገር ቤት ያሉ ጦማሪያን ሊኖሩበት እንደሚችሉ ጠርጣሮቹ ጠርጥረዋል።  ስለዚህ ነቃ ብሎ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ያለ ሁሉ አረማመዱ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን አደራ ማለት ይገባል። ለቸሩ መድሃኒያለምም አደራ እንላለን!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

13 responses »

  1. Fibus Niggli says:

    የወያኔ ጉድ ተወርቶ አያልቅም…የሚቀጥለው አኬልዳማ እየተዘጋጀ ነው ማለት ነው::

  2. haile says:

    “የሁለት ሀውልት” ወጎች መፅሐፍ Yehulet Mirchawoch bemil yistekakel

  3. yigermal says:

    meche yihon yezich mekeregna hager sikay yemibekaw?zegochuas kesidet yemikerut…?

  4. በለው! says:

    “ታዋቂዋ ተዋናይ መሰረት መብራቴ ከሀገር ወጥታ አሜሪካ ጥገኝነት ጠየቀች የተባለው እውነት ነው እንዴ!?ሁሉን ሰብስበው መያዝ የሚፈልጉ ዋና “የሴራ” ሂደት የሰራዊቱ ባለቤቶች መሰረትንም፤ “የኢህአዴግ ንብረት ነሽ አለበለዛ ወዮልሽ!”ብለዋት ይሆን? ድሮም ይቺ ማንቆለጳጰስ ስትበዛ ሊበሏት ያሰቧትን… እያልኩ ሁልጊዜም አስባለሁ።!
    “በሚሊኒየሙ ግስጋሴ በሕዳሴው ተምሳሌት በችግር ደህና ሰንብት ዕለት በብር ሙሉ ቀሚስ የተሰፋላት ናት ??”

    “የአለፈውን የአራት ሺህ ብር ቦንድ አልወድኳትም ያልኩት ለዚሁ ነበር” !!

    Chief Editor of Fitih magazine
    representative Ato Mamush Sentie in Eritrea
    Ahmedin Nasir”
    “To Ato Temesgen Desalegne

    “AlShebab has assigned me secretly to make propagation activities in Ethiopia
    to publish propaganda articles against the Ethiopian government,”
    ፩) የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለውን ተቃውሞ በራሱ ፹፫ የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ መናገር መፃፍ አይችልም ? ሕገ መንግስታዊ ጥበቃው ዕኩልነቱ ማንነቱ የሚረጋገጠው (ተረግጦ) ነው ማለት ነው ? እውነትም ሼ..
    ፪) ህዝብ መልካም አስተዳደር, የተደላደለ ኑሮ, ብዙ ጋዜጦች, የመናገር, የመሰብሰብ, የመወያት, መብት ካለው የግድ የፍትህ ጋዜጣ የምፈልገውን ፃፈ ተናገረ አመላከተ ብሎ ተመስገን ደስ አለኝ ብሎ ባልመሰከረ ነበር።!! ፫) ፍትህ ማመዛዘንን ማስተዋልን የሚያሳይ እንጂ ከምስራቅ አፍሪካ ሆኖ አሜሪካንን የማተራመስ የመለካት አቅም ካለው የጂ-፰ , የጂ-፳ እና የሄግ (ICC) ተመስገን ብለው ኢትዮጵያ ለመኖር እጃቸውን ሊሰጡ እንደሆነ ያመላክትል። ፬) “የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ” ፃፈ የሚለው ተመስገን የሚባል አልሸባብ እስከ አሁን አልተመዘገበም ግን ያየሁ የሰማሁትን ሳላሸልብ አናገራለሁ አልሸበብም ካለ “ሸብ” አርገው ካሉ …አሁን ከሼምም ሼም ሽንታም በለው!

    ” It has to be remembered that we have paid US dollar 24,000 for 30 consecutive editions.”
    ፩) ክፍት የሥራ ቦታ ለጠ/ሚ ፮፼፪፻ የኢት/ብር ተሸብረው ከሚያሸበሩና ከሚዋርዱ በአንድ ጊዜ ዶላሩን ነክሰው ቢወርዱ! ፪) የፍትህ ጋዜጣ ግማሽ ሂሳብ ተቀብሎ ማሸበሩን በ፴ ዕትም አቁሞ ተሸማቆ ላጤ ቢል ኢህአዴግ ተመስገን ደስአለኝ ብሎ መስቀል አደባባይ ላይ ከበሮ ሊያስደልቅብን ነው ማለት ነው? ? እህል ሲጠፋ ዶላር ይረክሳል እንዴ ? ? ፫) እናንት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ብፁህ የሆናችሁ ትመሩኝ ዘንድ እለምናለሁ!አንግዲህ አሁን መልስልን የተባለው 11200 ዶላር ነው። ከኢህአዴግ ካድሬ እና የደንባራው ይቅርታ ቸኩዬ ነው (ዲያስፖራው) ኢንቨስተር በቀር በባንክ ውሰጥም ይሁን በቦርሳቸው እንዲሁም በመቀነታቸው የመሪዎች ሁሉ ድሃ ታጋይ ቀዳማዊት አዜብ መስፍን እንኳ አላቸውን ? ? መንግስት ተጨማሪ ሰዎችን በአሸባሪነት ክስ ሊጠረንፍ አስቧል አሉ።የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል ያለ ሁሉ አረማመዱ ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን አደራ ማለት ይገባል። ለቸሩ መድሃኒያለምም አደራ እንላለን! ዳር ዳሩንም እንሄዳለን !
    ፬) አልሸባብም ሰበብ ከሚሆንብን እራሱን አደራጅቶ ፓርቲ መስርቶ ከምርጫ ቦርድ ገንዘብ እየተቀበለ የአውራው ፓረቲ አቻ ሆኖ ፕሮግራሙን በነፃ እና በሕጋዊ መንገድ በግልፅ ዓላማውን ለምን አያራምድም ? ? ኢህአዴግ አነተ ሁሉን ታውቃለህ እና አማልደን… ተመሳጥረህ አታስጠፍርነን ነፃነት! ነፃነት! ግልፅነት ተጠያቂነት ፍትህ ያብብ እንላለን !! እስር ቤቱ ከሰል ቤት ይሁን አሜን በሉ.. ተመስገን ደስአለኝ ዶላር ጨበጠልኝ !! አቤ…ት..እንቁልልጭ…እንቁልልጭ!!

  5. mm says:

    Not የሁለት ሀውልት ወጎች መፅሐፍ ምረቃ ——–> But የሁለት …. ወጎች መፅሐፍ ምረቃ

  6. Tobia says:

    The stupidity of the email sender once again confirmed by another mistake. The sender is made a complete spelling mistake when he wrote AlShebab. The correct spelling is ‘ Al Shabaab’

  7. majesty says:

    አሸብር ጌትነት የፃፈው ማስፈራሪያ ይመስላል፡፡ በነገራችን ላይ አሸብር በተራው መቼ ነው ጥገኝነት የሚጠይቀው

  8. በለው! says:

    “እኔ የምለው ትላንት ፍትህ ጋዜጣን በኢንተርኔት ተመልክቻት ነበር። “ፍትህ እና አልሸባብ ምን አገናኛቸው!” በሚል ርዕስ ተመስገን የፃፈውን ተመልክቼ በጣም ነው የተደነቅሁት። እኔ የምለው ሰዎቻችን ይሄንን ያህል ወርደዋል!? ተዋርደዋል እንዴ…!? አረ ሼ…!

    አንዴ… ቆይኝማ ደብዳቤውን ላላያችሁት ወዳጆች እዚሁ ላይ ላምጣምውና እንየው ድጋሚ እስቲ…”
    *********************************
    እናመሰግናለን አቤ..ተመስገን ደስአለኝ ደብዳቤውን “ዘ ሀበሻ” የሚባል ድረ ገፅ ላይ አነበብኩት እነኝህ ትችት የሚያቀርቡበትን ግለሰቦች ፅሑፍ ሁሉንም አንብቤአቸዋለሁ አብዛኛዎቹ ሀተታዎች ከአንዳንድ ባለሥልጣናት አፍ
    የወዳደቀች ተለጣጥፋ የምትፃፍ ነች(…) ፅሁፉ የሚረበሸው የራሳቸውን ሐሳብ ሲያስገቡበት ይጣረሳል…ያስቃል..
    *የሚያስቀው ክፍል ቀድመን ያደመጥነው የተቸነውን ተራ ወሬ እነሱ ብቻ ያወቁት የመንግስት ሚስጥር አድርገው ይቀበጣጥራሉ ። ሌላው የጨረባ ተስካር የሚሆነው የመንግስት ደጋፊ ድረ ገፅ እና የመንግስት ጋዜጣ ላይ የሚቀሳፍቱት ሰዎች…በካድሬነት ፣በጆሮ ጠቢነት ወይም ከእነኝህ ሰዎች ጋር ወሬ በማቀበልም ይሁን በመቀበል ቅርብ ግንኙነት ያላቸው ናቸው። በአብዛኛው ያለ አዋቂ ሳሚ የመነግስትን ሚስጥር ተሻምተው ያወጣሉ !!
    **ችግሩ ያለው አልኩ ባይነት (እኔ ቀድሜ ተናግሬአለሁ) (ቀድሜ አውቄ ነበር ) (እኔ ቀድሜ ፅፌ ነበር) የሚሉ ይመስላል የሚታሰረውን,በዓይነ ቁራኛ የሚጠበቀውን,ሀገር ጥሎ የሚጠፋውን,አልፈውም የሚከሰሰውን,የክስ ጭብጡን እንዲሁም የዓቃቢ ህጉን ማስረጃ, ሊሰጥ የሚችለውን ውሳኔ ይፅፋሉ።”እውነትም የተሰውት ጎድለው የሚሰውት ሞልተዋል!!”

    ይህ ሲታይ ያ…የወታደር መንግስት ምንም ጨካኝ ቢሆን የሰሉ እና የበሰሉም ሀገር ወዳዶችም ይዞ ነበር ማለት ያስደፍራል። በዚህም እስካሁን በተፎካካሪው ጎራ በታሪክ, በሥነ ፅሑፍ, በሃይማኖት,በኢኮኖሚው,በሕጉ ዘርፍ የተመጣጠነ በቂ አሰላለፍ አለ። እስከ አሁን ከውስጥም ከውጭም ያልተሳካለት አሰራር ቢኖር ይህንን በቂ እና ቆራጥ ሀይል አሰላለፉን አጠናክሮ ከፖለቲካው ጋር ማዛመድ ያልተቻለበት ምክንያት በጣም ያሳዝናል? ? ?
    ለእንደነዚህ ያሉ ጋጠ ወጦች እነኳ ተቀናጅቶ በወቅቱ በቂ ምላሽ የሚሰጥ እነኳ አላነበብኩም!! ይህ አሰራር መለመድ መቻል አለበት በዚህ አቤ ቶኪቻው በፅሑፍ የታማኝ በየነ በመድረክ በምስለ ቅርፅ ያላቸው አካሄድና አሰላለፍ መልካም ነው።

    ***ወያኔ እነኝህን የመሳሰሉ ኮራጅ አመዳምና አድመኞች ይዞ ለሃያ ዓመት ቢያተራምስም በቂ ተቃዋሚ ባለማግኘቱ እነጂ በዕውቀት የተሻለ ሆኖ አደለም! ጎበዝ ቢሆን ኖሮ በአነድ ቀን ቁጣ አያቀረቀርም ! ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ በ፫፼፯፻ ብር አዲስ አበባን ስታሸበር፣ አቶ ለገሠ(መለሰ) በ፮፼፪፻ ብር ኢትዮጵያን እና የፍሪካ ቀንድ የቀጠናው አሸባሪ፣ ተመስገን በ፳፬፼ የአሜሪካ ዶላር ኢትኦጵያንና አሜሪካን ? ? የኢህአዴግ አባላት ያን ሁሉ ገንዘብ ያሸሹት ማንን ሊያሸብሩበት ነው? ምን አልባት እነሱም የሽንበራ እርሻ መሬት ሊገዙበት ይሆን? ኸረ በባንዲራው እንዳልል ዘጠኝ ሆነ ብዬ ነው!!
    ዘጠኝ ሞት ቢመጣ አንዱን ግባ በለው እንል ነበር። በቸር ይግጠመን>>>

  9. I am unique! says:

  10. በለው! says:

    ክቡር ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ እንደምን ሰንብተዋል “አፍ ሥራ ሲፈታ ወዳጁን ያማል”አሉ ቀደም ባለ ጽሁፍዎ አንድ ጥያቄ ነበረዎ”የወያኔ ምሁራን ሹማምንትና ካድሬዎች የት እንደተማሩና ምን መጽሐፍ እንዳነበቡ ቢነግሩን?” ያሉት አስገርሞኝ ጽሁፍዎ በእኛ ቤት ምሑራን እንዴት ይታያል (ይተገበራል) ብዬ ለማመሳከር መቼም ከእነኝህ ሰዎች ጋር ተጻፅፎም ይሁን ተቀራርቦ ለመረዳዳት ያስቸግራልና በዚያው ድረ-ገፃቸው የተሻለ ትምህርት ለመቅሰም ጎራ አልኩ አይጋ ፎረም “የዜሮ ድምር ፖለቲካ ደግሞ የመሬት ሽሚያ በሊዝ አዋጅ ሽፋን” ሙሉጌታ ከጋምቤላ 2/14/15 ይህ ቀኑ ይሁን የካድሬነቱ መታወቂያ ቁጥር ይሁን አላውቅም ጸሐፊው እንደእርስዎ አስራ አንድ ገጽ ጽፏል ምሁር ለመሆኑ ማስረጃ እንዲሆነው 1)ሊ/ጠ መስፍን ወ/ማ 2)ሊ/ጠ በየነ ጴጥሮስን 3)የጋዜጣ አምደኛውን ተመስገን ደስአለኝን 4)የዓለም የሰብዓዊ መብት ጠባቂ ተቋምን በተከታታይ ስምንት ገጽ ሲዘልፍ ይዘልቃል ከዘጠነኛው ገጽ በኋላ ግን የእርስዎ ጥያቄ ተመልሷል ጊዜ አግኝተው ሲያነቡ ወንበርዎ ተሽከርካሪ ከሆነ ይጠንቀቁ!ምን አልባት መነጽር የሚያዘወትሩ ከሆነ ገመድ ያዘጋጁለት ተስፈንጥሮ ቢወድቅ ሃላፊ አደለሁም! “የጋምቤላ ክልል ግብርና ቢሮ ዓመታዊ ዕቅድ” በአምስት ወራት የተከናወነው ሥራ አደለም ጋምቤላ አሜሪካና ጃፓን በሕብረት በሙሉ በዘመናዊ መሳሪያ ቢሰማሩ ሊጠናቀቅ ሳይሆን ንድፉን ወረቀት ላይ ለማስፈር ብዙ ጊዜ ይወስድባቸዋል::ለመሆኑ ጋምቤላ በአምስት ወር እንዲህ የተሳካ ለውጥ ካመጣ ሃያ አንድ ዓመት ይህ ህዝብ እንዴት ለዳቦ ሰልፍ ያዘ??
    አስደናቂው ዘገባ 52.850 አርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ 10 ቀናት ትምህርት ተሰጥቷቸዋል:: 58.370.30 ሄክታር መሬት ለምቶ1125.219 ኩንታል ለመሰብሰብ በተጣለው ግብ49.923.07ሄክታር መሬት በዘር መመሸፈን 571.874.25ኩንታል ምርት ተሰብስቧል::በዚህኛው ጽሑፍዎ እንደገለጹት ግለሰቡ በተፈጥሮ ሳይንስ የተመረቀ መሆን አለበት ቀሪውን የቁጥር ብዛት አንብበው ይዝናኑበት::
    ለመሆኑ የሚሊኒየሙ ተመራጭ ምግብ እሩዝ እንደሆነ ያውቁ ነበር??ማንቸውም መንግስት በሚያወጣቸው ሕጎች ደንብ አዋጆች ሕዝቡን በውሃ ቀጠነ መሰብሰብና ማወያየት የሞራልም የህግም ድጋፍ እንደሌለው ያውቃሉ??በሀገራችን አርሶ አደሩ በክክልል እና በቀጠና ስለመስኖ ልማት በሦስት ቀናት ስልጠና ወደ ተግባር እንደሚገባ ያውቃሉ??ከ15.000አባ ወራና/እማ ወራ 14.367 በመንደር ለመሰባሰብ በፍቃደኝነት ሆ !ብለው መመዝገባቸውን ያውቁ ነበር?? 418.4ሄክታር በመንግስት እና በግል ይዞታ ላይ የዛፍና የፍራፍሬ ችግኝ ተተክሎ 85%መጽደቁንስ አይተዋል የት ሀገር ?? ጋምቤላ ክልል ብቻ እውነትም ይህ ትምህርት እና መጽሐፍ ትምህርት ቤቱን ጨምሮ ማፈላለግ አለብን ::ምን አልባት ዘ ሰን ይህንን ዘገባ ተርጉሞ ይሆን ኢትይጵያ ከእንግሊዝ ጋር ስትወዳደር 10 ዕጥፍ ትበልጣለች ያለው ወይንስ 38.7% ወደ 29.6% ድህነት ቀነሰ የሚሉት 9.1%ድሆችን ፈጅተው ቀንሰዋል
    “እንደ እኔ እማ ቢሆን እንደ ልቦናዬ ንጉስ ባሌ ሆኖ ዳልጌ ውሽማዬ አለች አሉ አራዳይቷ” እኛ እንዲህ ሁሉ አልጋ በአልጋ የሆነ ኑሮ ሕዝባችን ቢገጥመው መች ጠላን በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
    ‘አቡጊዳ’ ድረ ገፅ April 02 2021 በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
    “የአቶ መልስ መንግስት ልማታዊ ወይንስ አጥፊ አገዛዝ?” በሚል ርዕስ እነኝህን የመንግስት ቡችሎች በድሃው ህዘብ ላይ አላጋጮች የሚቀሳፍቱትን በምሳሌነት ማቅረቤ ትዝ ይለኛል ቀጣዩንም ክፍል በዚያው ላይ ያንብቡ…. አመሰግናለሁ።

  11. በለው! says:

    ኮለኔል ተወልደ ሀብቴ ነጋሽ ማነው?
    በፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ላይ ተደጋጋሚ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰ እንደሆነ ደጋግመን ገልፀናል፡፡ የዛሬ አስራ አምስት
    ቀን በታተመው ፍትህ ላይም ‹‹የአልሸባብ›› ተወካይ ነኝ ያለ ሰው በፍትህ ኢሜል አድራሻ ማስፈራሪያ መላኩም እንዲሁ ተገልፆአል፡፡ ሆኖም ይህ አይነቱ ዛቻ እንደቀጠለ ሲሆን በዚህ ሳምንት መጀመሪያም ‹‹ኮለኔል ተወልድ ሀብቴ ነጋሽ›› ነኝ
    ያለ ግለሰብ ከዚህ በታች ያለውን የማስፈራሪያ ደብዳቤ በዛው የፍትህ የኢሜል አድራሻ በመላክ ዘመቻው ቀጣይነት እንዳለው አመላክቷል፡፡ እናም አንባቢያን እንዲያውቁት እና መንግስት ‹‹እጄ የለበትም›› የሚል ከሆነ ጉዳዩን ተከታትሎ እኛን በዜግነታችን የመጠበቅ ያለበትን ግዴታ ይወጣ ዘንድ ለማሳሰብ አትመነዋል፡፡
    Hi temesgen!
    It is adivisable for you not to open a conflict with the agents of shebab. If
    there is unsettled problem you should leave it to be solved with the concerned body. What you are expected to do as always is to continue the wage over the Ethiopian regime and its economy. You are expected to hammer more the protest propaganda.
    To be fruitful and resultful in your mission you always consult you collegue fassil yenialem for the design and planning of the propaganda. we have learned that some time you work your self egnoring fassil. This is not good and acceptable.with regards
    Tewolde habte Negash(colonel)
    ሰላም ተመስገን
    ከአልሸባብ ልዑክ ጋር ችግር ውስጥ ባትገባ የተሻለ ነው ። ምን አልባት ያልተፈታ ችግር ካለ ለሚመለከተው ክፍል ብትተወው ይሻላል። ካንተ የሚጠበቀው በኢትዮጵያ መንግሥት እና ኢኮኖሚው ላይ የከፈትከውን የማጥላላት ዘመቻ መቀጠል ብቻ ነው። ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ መልኩ በደንብ አድርገህ እንድትቀጠቅጠው ያስፈልጋል፡፡
    ለጀመርከው ፕሮፓጋንዳ እቅድና ዲዛይኑን በማውጣት እንዲተባበርህና ውጤታማ እንድትሆን አጋርህን ፋሲል የኔአለም ልታማክረው ይገባል። አንዳንድ ጊዜ ፋሲልን ሳታማክር በራስህ የምትሰራቸው ስራዎች አንዳንድ ጊዜ ፋሲልን ሳታማክር
    በራስህ የምትሰራቸው ስራዎች እንዳሉ ተረድተናል። ይሄ መልካምና የሚደገፍ ሆኖ አላገኘነውም።
    ከአክብሮት ጋር
    ተወልደ ኃብቴ ነጋሽ (ኮሎኔል)
    **************************************************************************************************
    እኛም የተዘጋጃችሁበትን የክስ መዝገብ ደርሰንበታል “ውሾች ሲጮሁ ግለሰቡ በመተኛቱ ተመስገን ደስአለኝ በለው!

  12. በለው! says:

    ‘ጎራዴው ቢዘም ባይዘም’(…) “የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ እና አምደኞቿን የክስ መዝገብ በጨረፍታ!!”
    ************************************************************************************************* ፩)በፍትህ ጋዜጣ የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ ነገረኛው ብረሃኑ ደቦጭ፣ወስን ሰገድ ገ/ኪዳን፣ ዶ/ር ነጋሱ ጊዳዳ፣ ሊ/ጠ መስፍን ወ/ማርያም፣ሊ/ጠ ጴጥሮስ በየነ ፣ሀሳባቸውን ያለገደብ እንዲፅፋ ኢህአዴግን እንዲተቹ መብት ሰጥቷል። ፪)ይድረስ ለአጉራ ዘለል ካድሬ!”ዛሬ እንዲህ የምትፎክርበትን ሗላ ኪስህ ያለው የድርጅትህ መታወቂያ ነገ መወንጀያህ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር አለብህ ብሎ የኢህአዴግ ካድሬን አሸበሯል (አስፈራርቷል)። ፫)”እኛም ኢትዮጵያዊ ነን !”ኢትዮጰያዊ ጀግንነትን ለብቻህ አታድርግ ብሎ ጀግና ለመሆን ቃጥቶታል ቢያንስ እንደ አቡነ ጴጥሮስ እውነትን ተናግረን ለሀቅ እንሞታለን ብሎ ሁከት ለመፍጠር ተነሳስቷል። ፬)በሀገራዊ ጉዳዮች “ኢትዮጵያዊው ማነው ?ሲል( ኤፍ.ቢ.አይ)የሰጠውን የሽብርተኝነት ትርጓሜ አጣጥሏል በሽብርተኝነት ተጠርጥረው የጥፋተኝነት ውሳኔ የተሰጣቸውን ጓደኞቹን ለመታደግ ሞክሯል። ፭)ተመስገንና መዋቅሩ (አምደኞቹ)”ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ እየተጓዘ ነው !”በማለት የኢህአዴግን የሚስጠር ሥራ በጋዜጣ ለሕዘብ አዳርሰዋል (አሳምፀዋል)። ፮)በሰኔ ፳፱/፪፼፬ ዕትሙ “ይቅርታ ኢህአዴግ ቃጭል ወይንስ?”በሚል የቅንጅት እንጀራ ልጅ ለሆነው አንድነት ልሳን ሆኖ አገልግሏል።ግን የማንም የፖለቲካ ድርጅት አባል እንዳልሆነ የክህደት ቃል ሰጥቷል። ፯)የሽብርተኛ አዋጁን ላይ ተጠቀሰውን “ከሽብርተኛ ጋር መወዳጀት ” የሚለውን ተላልፎ ከአብይ ተክለማርያም ጋር በመገናኘት ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳንም እቢሮዋ ድረስ ሄዶ አነጋግሯል።
    ፰)”መለስ ዜናዊ ከመይ ቀኒዮም” በማለት ጋዜጠኞች እና የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ከሽብርተኝነት ወንጀል ነፃ ናቸው የሚል መጣጠፍ ፅፏል።
    ፱)የብሔር ብሔረሰቦችን ሕገ መንግስታዊ መብት “የጭፈራ እና የዳንስ መብት!”ሲል ጭር ያለውን መንደር ለማቃጠል መፈለጉ ታውቋል።
    ፲)የግብር ሥርዓቱን “ነጠቃ” ነው ብሎ ሕዝቡን አሳዛኗል።
    ፲፩)ለዘመናት ሲናፍቀን እና ስንፈራው,የቁጭት ክራር ስንከረክርለት እና ግጥም ስንደርድርለት,ሸራ ስንወጥርለት ለኖርነው አባይ ግድብ ዕውን መሆን “በአባይ ጉዳይ የሚያፈገፍግ ካለ ኢትዮጰያዊነቱ ተሰርዟል” ያሉትን ዶ/ር አባ ጳውሎስ ቃል በእጅጉ ተሳልቆበታል ብዙ ምሕመናንም ከቤተ ክርስቲያን ቀርተዋል ህዝቡም ለዜግነቱ መነጠቅ ተቆጥቷል።
    ፲፪)ሀገር እየሰለለ እና እያሰለለ የሚገኘው ‘የፍትህ አምደኞች መንደር’ “ቀያፋም -ሄሮድስም “ናቸው።
    ፲፫)”የሀውልቱ ሥር ፖለቲካ”የጄኔራል ሳሞራ የኑስን ጄኔራልነት አድንቀው እና አዳንቀው አልፃፉም።የድሮውን ናፋቂ!፲፬)”የተከበሩ እና የቀለሉ መሪዎች” በማለት ከቅንነት ነው ርዕሰ ጉዳዩን የመረጥኩት ብሎ “ቅንነቴን ቅንቅን አድርጎ የሚያስብ ካለ” ማለቱ ኢህአዴግ ቅን የማያስብ ቅንቅናም እንደሆነ ለሕዝብ ማሳወቁን በማስረጃ ተደርሶበታል። ፲፭)የአወልያው ኮሚቴ አባላትን መብታችሁን ጠይቁ ብሎ አላስተባበረም “በብጥብጡ አጋጣሚውን በመጠቀም መንግስትን መንግሉ!አመፃውን ከዳር ዕዳር አዝምቱ! አለ።ሙስሊሙ አፉን ሸብቦ እጁን አውለበለበ በፖሊስ አስደበደበ!
    ፲፮)የዋልድባ መነኮሳትን ገዳሙን ሰላም ስበኩበት ሳይሆን ተዋጉበት አለ። (አቧራው ጨሰ!)
    ፲፯)የጉራፈርዳ የአማራ ብሔር ተፈናቃዮችን “በደቡቡ ሕዝብ ላይ ዝመቱበት!” አለ ሕፃናትን ለአመፅ አስለቀሰ። ፲፰) መብት ነጥቋል ተብሎ የሚታማውን ኢህአዴግንና ካድሬውን “የወረደድሽ ዕለት ወዮውልሸ እያለ ዝቷል። ፲፱)”ልጆቻችሁ ቻይና ምን እየሰሩ ነው ?”ሲል የኢህአዴግን የሥልጣን መተካካት በቤተስብ እንደሆነ ዘመድ አዝማዶቻቸውን አስተማሩ ሌላው የሚበላው የለውም ሲል ወጣቱን ለተቃውሞ አነቃቅቷል።
    ፳)ኢህአዴግ መሠረታዊ ሥህተት እስካልፈፀመ ድረስ በመሳሪያ,በገንዘብ ሀይል እና በሰው ሀይል ስለተጠናከረ ከዚህ በሗላ ለረጅም ዓመት ይገዛል ሲል ተነበየ።
    ፳፩)ለሕዘቡ የማይቀርብ ከሕዘብ የማይገናኝ ዜጎቹን የማያበረታታ የማይሸልም “መሪ ሳይሆን መሰሪ ነው” ሲል በአንድ በሉ! አምዱና ርዕሰ አንቀፁ ጽፏል። ለማበረታቻ የተሰጠን ገንዘብ ‘መደለያ’ ሲለው ሲያጣጥለው ተገኝቷል። ፳፪)”እራሳቸውን የመገንባት አምልኮ” መለስ ይናገራሉ እንጂ በጥያቄ አይፋጠጡም!ሲል ሊቁን መሪ አቃሎ ጽፏል። ፳፫)ቤቱን የማይሰራ.. ዕድር እንደማይመራው ሁሉ ሀገሩን በሚገባ ያላስተዳደረ መሪ የአህጉር መገለጫ መሆን ከቶ እንዴትስ ይቻለው ይሆን?? ሲል በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ እና አመራሩን ነቅፏል።
    ‹‹ዘምሟል ጎራዴው››? ይላል ይቀጥላል በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ በለው!>>>>>>>>>>>>>>>>>>
    (የዋናው ብሎግ ሐሳብ መስጫ አልቀበል ስላለ በዚህ ተሞከረ)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s