በዚህ ወሬ ውስጥ ተሜ ባይኖርበትም በሽኝቱ ላይ ተካፋይ ስለነበር፤ ይህንን ፎቶ ለጥፌዋለሁ!

ሰላም ወዳጄ ዛሬ ብዙ ወሬዎች ሳይኖሩኝ አይቀሩም፤ ታድያ  ከየትኛው ልጀምር!? ብዬ ሳስብ ይቺ “ኢጃ በና” ትሁን ብዬ አካፈልኳችሁ። “ኢጃ በና” ማለት ቃሉ ኦሮሚፋ ሲሆን የአይን መክፈቻ! ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ቃሚዎች ዋናውን ጫት “ቂማህ”  ከመጀመራቸው በፊት ትንሽ ነከስ ነከስ የሚያደርጓትን አይን መክፈቻ ወይም ኢጃ በና! ይሏታል።

ተጀመረ፤

ደራሲ በውቀቱ ስዩም ትላንት በጣይቱ ሆቴል አድናቂዎቹ፣ የጥበብ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።

በእውቀቱ እንግሊዝ የሚሄደው በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ግጥም እንዲያቀርብ ተወዳድሮ በማሸነፉ ሲሆን ከእርሱ ጋር በርካታ ስማቸውን የማላስታውሳቸው የአለማችን ታላላቅ ፀሀፍት ስራ ይቀርባል። በተጨማሪም ፅሁፎቹ ታትመው በኢሊኮፍተር ወይም በአንዳች ነገር ከሰማይ ለህዝቡ እንደሚበተኑ ሰምቻለሁ።

ይህ ለበውቀቱ እና ለሁላችንም ታላቅ ውጤት ነው። በተለይ ደግሞ ለሞያ አጋሮቹ እና ለቀድሞ ጓደኞቹ… እልና፤ (ጓደኛው እንደነበርኩ እገልፃለሁ!) እዝች ጋ የሽሙጥ ሳቅ ሲስቁ እየታዩኝነው።

ይልቅስ በሽኝቱ ወቅት እንዲህ ሆነላችሁ፤

የደራሲያን ማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ሆዬ ንግግር ሲያደርጉ…

“ለበእውቀቱ የለንደን ጉዞ መሳካት የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን እና መንግስትን ማመስገን እወዳለሁ…! በእውቀቱ በጉዞህ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ እንድታስተዋውቅም አደራ እልሃለሁ!” ብለው እንደ ደራሲ ሳይሆን እንደ ካድሬ አልተናገሩም መሰልዎ…!? ቆይማ አንድ ጊዜ የአርቲስት እሸቱ ጥሩነህ ንግግርን ደግሞ ልቀንጭብላችሁና ወደ በእውቄ መልስ እናሳልጣለን፤

“ይህ ልጅ ድሮ ሳውቀው ቀጫጫ ነበር አሁን ግን በጣም ወፍሯል… መጀመሪያ ያየሁት ጊዜ ኮት እንደሰጠሁት አስታውሳለሁ…!” ብለው ሌላም ሌላም ጨምሩ ሰዓሊው እሸቱ… ሲያበቁ፤ (ነገረኛ ታዳሚዎች፤   “አሁን ያቺ ኮት ለዚህ ጉዞ ያላት አስተዋፅኦ ምን ይሆን…!?” እያሉ በሆዳቸው ጠየቁ…!)

በእውቀቱም ተራው ደርሶ ዝግጅቱን እና ንግግሩን ሲያቀርብ እንዲህ አለ፤

“በመጀመሪያ አቶ ጌታቸው ባሉት አልስማማም። መንግስትም ሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ምንም አላደረጉልኝምና አላመሰግናቸውም። ትብብር ያደረገለኝ የደራሲያን ማህበር መመስገን ካለበት እርሱን አመሰግናለሁ።

ሌላ… “የሀገሪቱን መልካም ገፅታ ገንባ አደራ” ለተባልኩት፤ ጋሽ እሸቱ እንዳለው እውነትም በፊት በጣም ቀጫጫ ነበርኩ። አሁን ግን ወደ ውጪ ሀገር ስሄድ፤ “እነዚህ ሰዎች ምግብ አይበሉም እንዴ!?” እንዳይሉን በመስጋት ይኸው ወፍሪያለሁ!” (ታዳሚው ሆዬ በሳቅ መሞት… እኔስ ብትሉ…! እርስዎስ ብል…!?)

በውቀቱ ሲቀጥልም፤ “ጋሽ እሸቱ “ኮት ሰትቼዋለሁ” ያሉት እውነታቸውን ነው። ግን አሁንም የምሄደው ብርድ ሀገር ስለሆነ ጃኬት ይሰጡኛል!?” በማለት አርቲስት እሸቱንም ታዳሚውንም እኛ በሩቅ የሰማነውንም በሳቅ አንፈራፍሮናል!

አብዛኛውን ታዳሚ በተለይ የደራሲያን ሊቀመንበሩ አቶ ጌታቸው ካድሪያዊ ንግግር አሸማቋቸው እንደነበር ወሬ አቀባዬ ሹክ ብላኛለች!

በእውቀቱ ስዩም በዛሬው እለት ወደ ለንደን ይበራል የተባለ ሲሆን፤ መልካም ጊዜ እንዲኖረው እመኝለታለሁ!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

9 responses »

  1. Etsegenet says:

    good answer be ewketu and good luck .

  2. Fibus Niggli says:

    በጣም ጥሩ ዜና ነው! እንኳን ተሳክቶለት ወጣ:: ሐሳብን በነጻነት መግልጽ፣ ሐይማኖትን መተቸት በማይቻልበት አገር ከመኖር ስደት ይሻላል…ወደ እስር ቤት እንዳትመለስ በለው…

  3. majesty says:

    መልካም እድል ባለህበት!

  4. Azalech says:

    Abe, what a nice reading to begin my week with
    I wish I am in London….I hope one day I will have a chance to listen to you and Bewketu

    Ene degmo tilobign bitay yihen derek tsihuf aliwodim…Abe yantenna ye Bewkettu tsihufoch beka migib albela yalegn ken hulu maworarejawoche nachew…..
    ene enja bicha endihu melku yaltetsafe tsihuf jemire bicha akomalehu

    Anyways I hope you guys all the best

    Thank you for making us feel at ease in this crappy zemen

  5. በለው! says:

    “ደራሲ በውቀቱ ስዩም ትላንት በጣይቱ ሆቴል አድናቂዎቹ፣ የጥበብ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።(>>>)

    *ወይ አዲስ አበባ ወይ አራዳ ሆይ
    በእውቀቱ ስዩም በአንቺ ጨከነ ወይ ? ?

    “በእውቀቱ እንግሊዝ የሚሄደው በለንደን ኦሎምፒክ ላይ ግጥም እንዲያቀርብ ተወዳድሮ በማሸነፉ ሲሆን ፅሁፎቹ ታትመው በኢሊኮፍተር ወይም በአንዳች ነገር ከሰማይ ለህዝቡ እንደሚበተኑ ሰምቻለሁ።
    ** ተው በለው ! ተገጥሞ የሚበትን ነገር አላማረኝም ቀን እና ሰዓቱ ባልተጠቀሰ ዜና ቆመን አንጠብቀም ይበተን! የጉዞው ነገር ሲነሳ ድሮ በፊልም ላይ ያየሗትን “ባለሶስት እግር የአውቶቡስ ግልገል” ባህር ዳር ላይ እንዴት እንደሳላት ሳይ አሁን የተሳፈረው በእሱ ቢሆን ብዬ …አሳቀኝ እስከ አሁን በአይኔ ባላያትም ትናፍቀኛለች!

    የደራሲያን ማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ሆዬ ንግግር ሲያደርጉ…”በእውቀቱ በጉዞህ የሀገሪቱን መልካም ገፅታ እንድታስተዋውቅም አደራ እልሃለሁ!
    -መንግስትም ሆነ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ምንም አላደረጉልኝምና አላመሰግናቸውም። ትብብር ያደረገለኝ የደራሲያን ማህበር መመስገን ካለበት እርሱን አመሰግናለሁ።ያልዘሩት አይበቅልም!
    ማስታወቂያ ፩…
    “ሀገራችን ዕድገት ጨምሯል ድሮ ኮት የሰጡን የቆዳ ጃኬት መግዛት ስለቻሉ ነው ዛሬ ጃኬት እንስጥህ ያሉን ወርቅ የመግዛት አቅማቸው በመጨመሩ ነው።ለእናንተ ለአለቆቻቸው አይን እድሞላ ጥሩ ልብስ መልበስ እንዳለበኝ የሀገሪቱን ገፅታ እኔን አይቶ ከመመስከር “ልብስ አልባ በቦይ አደር ” ሕፃናትን ሄዳችሁ ጎበኙ አይን ገበያ ነው።ሕንፃ አድጓል ሕፃን ተርቧል!!!

    ”የአርቲስት እሸቱ ጥሩነህ ንግግር ደግሞ ድሮ ኮት እንደሰጠሁት አስታውሳለሁ…!”
    -“ጋሽ እሸቱ “ኮት ሰትቼዋለሁ” ያሉት እውነታቸውን ነው። ግን አሁንም የምሄደው ብርድ ሀገር ስለሆነ ጃኬት ይሰጡኛል!?”
    ማስታወቂያ ፪…
    “የፓውንድ እና የዩሮ ምንዛሪ እኔ እና እኔን የሚያውቁ ጓደኞቼ ሁሉ ተዘርዝረን ብንቆጠር ለእረስዎ ውለታ መክፈያ ስጦታ መግዣ የለኝም አይጠበቁ !።ይህ መልስ ለደራሲው ሊ/መንበር ለአቶ ጌታቸውም የሀገራችንን መልካም የኢኮኖሚ ሆኔታ የሚገልፅ ስለሆነ ከተመለስኩ ልቤን አታድርቁት ሳልሄድ መልሻለሁ!! ለቀባሪው አረዱት አሉ…በለው !

  6. Tobia says:

    ኦሮሚፋ ሳይሆን አፋን ኦሮሞ በሚለው ይስተካከል

  7. Billy says:

    I like 2 people commedian like peope…one is Bewuketu…whenever i see situation that have potential sources to have better commedy i wish I were Bewuketu or Bewuketu were me fo the chance. I know Bewuketu has potential to do alot especially the surprising western and Europian life styles with comparison or whatever way he make it. Good luck Bewuketu!

  8. meretwork says:

    Thank you very much!!! I like it!
    And yet earthling man,though in honor, cannot keep lodging”,He is indeed comparable with the beasts that have been destryed”,This is the way of those who have stupidity”and of those coming after them who take pleasure in their very mouthing”

    DELE LE EWNTE ETHIOPIA !!!!!! Yetelat Aneget yedefa Amen!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s