ትላንትና ከስንት ጊዜ በኋላ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርዬን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አየኋቸው። ያኔ አበበ ገላው በዋሽንግተን ዲሲ ቆሌያቸውን ከገፈፋቸው በኋላ በቴሌቪዥን መስኮት ስናያቸው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። (በቅንፍ፤ እንደ ድሮ ጎረቤት ብንሆን ኖሮ በቴሌቪዥን መስኮት ሲጠፉብን በሳሎናቸው መስኮት ለማየት ሙከራ እናደርግ ነበር። ዛሬ ግን ሩቅ ሆንና ናፍቆታቸው ሲያስቸግረን ሰነበተ! ብዬ ሀሳቢነቴን ለመግለፅ እወዳለሁ።)

አረ እዝች ጋ ሳይረሳ ባለፈው ጊዜ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሰዎች “አበበ ገላው ዋሽንግተን ዲሲ ያልሄደው በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ስላሉ እነርሱን ፈርቶ ነው!” ብላችሁን ነበረ። ረስቼላችሁ፤ ሰውየው እኮ አንገታቸውን የደፉት በዋሽንግተን ዲሲ ነው።

ታድያ የዛን ጊዜ ያ ሁሉ የአንገት እና የቅስም ስብራት ያጋጠማቸው የጋዜጠኛ አበበ ገላው ንግግር ብቻ መስሏችሁ ከሆነ ተሸወዳችሁ።

ከውጪ የነበሩት የአካባቢው ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ጩኸትም “ምነው እግሬን በሰበረው!” አስብሏቸው ነበር። ውስጥ ደግሞ አበበ ትንታግ ሲጨመርበት…!  እና ታድያ አዲስ አድማሶች ይሄ ሁሉ ነገር በዋሽንግተን ዲሲ ሲከናወን ደጋፊዎቻቸው የት ሄደው ይመስላችኋል? “በልማታዊ ስራ ተወጥረው ነበር!” ብላችሁ ሳቄን እስቲ አብዙልኝ! “ምን አይነት አዲስ አድማስ መጣ ደሞ ባካችሁ!?”

በነገራችን ላይ አሁንም እርሳቸው እርም የላቸውም የቡድን ሃያ አገራት ስብሰባ ላይ ደግሞ ሊገኙ ሲሄዱ ነው ያየኋቸው። እንደኔ እንደኔ ይሄ ቡድን ምናምን የሚባል ነገር ቢቀርባቸው ይሻላል። በርግጥ ስብሰባ ሊናፍቃቸው አንደሚችል ጠረጥራለሁ።  ምን ችግር አለው ታድየ በፈለጉ ጊዜ የሚሰበስቡት በፈለጉ ጊዜ የሚበትኑት ፓርላማ አላቸው አይደል እንዴ…!?  እዛው እንደሚሆኑ ቢሆኑ ይሻላቸዋል እንጂ፤ ገና ለገና የፈረንጆቹ “ቡድን” አያልቅም እና እርሳቸው “በድን” እየሆኑ የሚመጡበት ምክንያት ምንድነው!?

የሆነ ሆኖ “ታንክ ተደግፈው መፅሀፍ የሚያነቡት ጀግናው ጠቅላይ ሚኒስትራችን” በአበበ ገላው ንግግር የተነሳ ለአንድ ወር ያህል ተሸማቀው እና ተሸምቀው ሲያበቁ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለዋል።

ታድያልዎ፤ ትላንት ሳያቸው ክስት ብለዋል። ምን ሆኑ!? እንዴ ጠንከር ይበሉ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ! ቀጣዩ ጩኸት እኮ እየባሰ ነው የሚመጣው! ታድያ ጠንከር ጠንከር ማለት አይሻልም ይላሉ? ቁጣ እና ጩኸት ይህንን ያህል የሚረብሽዎት ከሆነ ግን ዘዴውን ልንገርዎት…!? እሺ አይሉኝም እንጂ ዛሬውኑ ስልጣንዎን ልቅቅ አድርገው አዲስ አገራዊ መግባባት፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ማከናወን! አቤት ያኔ ጤናዎ ላይ ራሱ ምን አይነት መሻሻል አንደሚመጣ ያዩት ነበር።

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

15 responses »

 1. majesty says:

  አቤ ከምኔው አደረስካት ባክህ? ሰውየው በጣም የተቸገሩ ይመስላሉ፡፡ እግዜሩ በመጨረሻው ፍርድ ሊሰጥ ተቃርቧል፡፡

 2. muna says:

  Abe mut mata be TV sayachew enem endantew kw nw yalkut. Ere sewyew lichru nw mesel angetachew bcha eko nw yekerew! Ende betam kestewal eko. Be Abebe gelaw chuhet endih kedenegetuma hzbu mechoh sijemr mn lihonu nw? Nigus yemikeses ken mn lihonu nw? Melsun lesachew titenewal.

 3. hahulelu says:

  Guys! It’s all what you think. Abe; Don’t you know the history of Meles. You must be crazy. Don’t you know that the man has kicked your fathers and grandfathers? No one will expect you to have a positive ideology; as you are ……

  You left your country ’cause you are unable to make difference. You write and expect the youth to be revolutionarist. Then after to come and …… Foolish!!! By now everyone knows what to do and what not. We are so dissatisfied after the election of 97.

  • G.G says:

   What history are you talking about, is that Meles was PM b/c of his GOD CIA of USA or there is some unknown history of this shameful PM. He is the only leader of Ethiopia w/o history

 4. Spiceup says:

  ende Gazetegna be ETV tewat mata endalaselechun, semonun tinish erfet argen neber.

  • Spiceup says:

   ጠዋት ማታ በኢቲቪ ሲመላለስ “ይሄ ሰውዬ ጋዜጠኛ ሆነ እንዴ?” እንዳላልን ይሄው ሰሞኑን አረፍ ብለን ነበር::

 5. Addisaba says:

  ትላንት ሳያቸው ክስት ብለዋል። ምን ሆኑ!? እንዴ ጠንከር ይበሉ እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትርዬ! ቀጣዩ ጩኸት እኮ እየባሰ ነው የሚመጣው! ታድያ ጠንከር ጠንከር ማለት አይሻልም ይላሉ? ቁጣ እና ጩኸት ይህንን ያህል የሚረብሽዎት ከሆነ ግን ዘዴውን ልንገርዎት…!? እሺ አይሉኝም እንጂ ዛሬውኑ ስልጣንዎን ልቅቅ አድርገው አዲስ አገራዊ መግባባት፣ አዲስ አገራዊ ምርጫ ማከናወን! አቤት ያኔ ጤናዎ ላይ ራሱ ምን አይነት መሻሻል አንደሚመጣ ያዩት ነበር። ካልሆነም ደግሞ ከእኛ ደሆች ላብ ላይ ሰርቀው የሰሩት ቤቶች ስላሎት ሽር ብለው ወደ ቤልጂየሞት ወይም ቻይናዎ ቢብስቦ ወደ አመቻቹት ቻይናዊነት ለውጠው ውልቅ ካልሆነም የከርቸሌ አለቅነት እንሾሞታለን ለጊዜው ግን ሰውነቶን ያደልቡት እሺ ዱላ እና ወደ ቻይ እንዲሆን

 6. henock says:

  my favorite part is
  “budin bilew hedew bedin honew yimetalu” kkkkkkkkkkk
  thank u abe

 7. Besu says:

  Ato meles megebe alekemete belwachewal endalachewe eyalachewe newe yemisemawe beka
  yegebawe hula yemelesale alu …

 8. Fissh says:

  የአንድ ወንድ ሊጅ ጩሀት እንዲህ ካከሳቸውማ የሰማንያ ሚልዮን ጩሀት ሲሰሙማ ሚዛናቸው የላባን ያህል ወርዶ አንደ ገለባ ሰማየ ሳማዩ ሊንሳፈፉብን ነው….

 9. […] በመቀጠልም ከዚህ ቀደም በአዲስ አድማስ በወጣ ፅሁፍ “አበበ ገላው ዋሽንግተን ዲሲያል ሄደው በርካታ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ስላሉ እነርሱን ፈርቶ ነው!” ብላችሁን ነበረ። ሰውየው እኮ አንገታቸውን የደፉት በዋሽንግተን ዲሲ ነው። በማለት ‹‹ምን አይነት አዲስ አድማሰ መጣ ደግሞ ባካችሁ!?›› ሲል ጥያቄ ጥሎ አልፋል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡ […]

 10. fibus says:

  በጣም ደስ የሚል አቀራረብ ነው!!! በደንብ አድርገህ ሰራህላችሀው ጠቅላይ ሚኒስቴራችህንን…Thank you Abe!!!

 11. በለው! says:

  *ምሁሩና ደፋሪው መሪ ይህ ሱፍ የት እንደተሰፋ? ማን እንደሰፋው አይታወቅም? ካለፈው ይህኛው ያምርብዎታል። ለመሆኑ ያገር ውስጥ ምርት ነው?
  -ከቻይና ለናሙና የእህት ፓርቲያችን የላከችልኝ ፤
  ደሞ ምን ጎደለ ? – ሽክ ብለዋል ብዬ ነው
  – ምንም አልጎደለ አሁን ፸ ከመቶ ሽክ ብለዋል ብዬ ነው ።
  ” አልፈራም…አልደነግጥም ! በከፍተኛ ደረጃ ተጠናክረናል ! ደጋፊዎቼን፤ካድሬዎቼን፤አምባሳደሮቼን ገምግመናል ካሉ በሗላ…. ይህንንም ሄደህ ከአቤ ጋር አሽሟጡኝ ….ኢሳት ላይ ለጥፉኝ አብዮታችን አይቀለበስም !

  አቤ,, የቱ ? ልላቸው ስል ለፎቶ ገጭ ሚ/ር ችንግ ከች አሉ…
  ምነው ነገር ነገር አለዎ ? ማድነቀም አሸባሪነት ነው? ሳልላቸው… የአራት ኪሎ አድባር ይከትልዎ ሕዝብ በእስካየብ እነዲከታተልዎ ቁልፉን ትተው ይሂዱ ልላቸው ስል …ያለፈው ጂ -፰ “ፈጣን ተቃውሞ” በ፳፩ ሴኮንድ ሳቄ ና !ና!

  “ታንክ ተደግፈው መፅሀፍ የሚያነቡት ጀግናው ጠቅላይ ሚኒስትራችን” በአበበ ገላው ንግግር የተነሳ ለአንድ ወር ያህል ተሸማቀው እና ተሸምቀው ሲያበቁ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለዋል።
  ** አድናቂ እና ተደናቂው ከጂ ፰ -ጂ ፳ ቀለጠ በለው!ሌላው ደጋፊ ሲቀሳፍት “አቶ መልስ በወቅቱ ያቀረቀሩት የመድረክ መቆጣጠር ልምዳቸውን አስመስከሩ…
  አቶ አበበ ገላው ተናግሮ ሁኔታዎች እስኪረጋጉ አቀርቅረው ማስታወሻቸውን እያነበቡ ነበር” እባካችሁ አዋጡ እና እንሳቅ(ቦንድ ግዙ)!

 12. Henok G says:

  abe so loved you, so addicted to your articles.pls, keep on posting.

 13. gibdaw says:

  “መለስ አንጀቴን በሉት” (ነበልባሉ አቤ ቶኪቻዉ ) ባለፈው ወር ኢትዮጵያ እናት ሃገራችን ካፈራቻቸው ጥቂት የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ጋዜጠኛ አበበ ገላዉ ምናልባትም አቶ መለስ በህይወታቸው ከደነገጡት ድንጋጤ ሁሉ የበለጠ ድንጋጤንና ሽብርን በመላ ሰዉነታቸው ከለቀቀባቸው በኋላ ጥፍት ብለው ከርመው ነበር።
  አብዛኞቻችን አቶ መለስ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ራሳቸውን ያጠፋሉ የሚል ግምት ነበረን። እውነታዉ ግን በጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላዉ የመብረቅ ድምጽ ክፉኛ ተመትተው ሽንፈት የገጠማቸው መሪ ከቁስላቸው ማገገም ተስኗቸው የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ ዉጭ ሃገር መጓዛቸዉን ሰማን ኣጀብ ተሰኘን ።
  ከዚያም ለበርካታ ሳምንታት ጥፍት ብለዉ ከርመው በሜክሲኮዋ የቅንጦት ከተማ ፊታቸው አብጦና ገርጥቶ እንዲሁም ቆዳቸው ልክ ጥቃጥቄ እንዳወጣ ሙዝ ተዥጎርጉረው ብቅ ሲሉ አበበ ገላዉ አንጀታቸውን ብቻ ሳይሆን ቆዳቸውንም ጭምር አንዳቃጠላቸዉ ገባኝ። ታዲያ በዚያን ወቅት መለስ ምትበላዉ ያጣች አራስ ድመት መስለዉ ሲመጡ ባለፈው የአቤን አንጀት እንደበሉ የኔንም አንጀት በሉት፡፡
  ግን ብስጭቴን የባለፈዉን ሁሉ ድንጋጤ ረስተዉት ወደ ጅ20 እንዴት ሊመጡ ቻሉ ? በእውነትም እኒህ ጠቅላይ ሚንስትር እንጂ ሰው አይደሉም በየ ከአቤ ጋር ተስማማሁ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s