ሰሞኑን አቶ በረከት ሰምዖን “ኢሳት ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮጵያ ከሚገባ ቢላ በአንገቴ…” አይነት ንግግር መናገራቸውን ሰምተናል።
እንዴት አደሩ አቶ በረከት…! እኔ የምልዎት ከ “አረብ ሳት” ባለስልጣናት ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ኢሳት ቴሌቪዥን ዘግቦት ተመልክተነው እኮ! እውነት እርሶዎ አፍዎን ሞልተው፤ “የኤርትራ ቴሌቪዥን ከፈለገ ይግባ በኢሳት ጉዳይ ግን አንደራደርም!” ብለው ተናገሩ!?
ምነው አቶ በረከት ለራስዎ ስምዎ ጥሩ አይደለም። አንዳንድ ንግግሮች ላይ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ምን አለበት!? እኔም ምን ጨነቀኝ ለራስዎ ብዬ ነው። ሰዉ፤ “እኒህ ሰውዬ ኤርትራዊ በመሆናቸው ከድሮም ጀምሮ የኤርትራ ጉዳይ እንጂ የኢትዮጵያ ነገር አያስጨንቃቸውም!” እያለ ስምዎን ሲያነሳና ሲጥል ተመልክቻለሁ። ምን ጨነቀኝ እኔ፤ የፍርድ ቀን የደረሰ ጊዜ፤ “ምነው ምላስ ባልኖረኝ ኖሮ…! እኔን ብሎ ተናጋሪ… እኔን ብሎ ኮሚዩኒኬሽን ሚንስቴር… እኔን ብሎ መግለጫ ሰጪ…. እኔን ብሎ ተደራዳሪ…!” ማለት ይመጣል።
ነገር ግን መጪውን አላመላከትዎትምና አልህ ጩቤ ያስውጣል እንዲል የሀገሬ ሰው ጭራሽ ብለው ብለው “የኤርትራ ቴሌቪዥን ላይ ተቃውሞ የለኝም ኢሳት ግን ወደ ኢትዮጵያ ከሚገባ ቢላ በአንገቴ!” ብለው ፎክረዋል አሉ። በርግጥ የሚበጅዎትን የመምረጥ መብትዎን መጋፋት ተገቢ አይደለም። ከኢሳት ቢላ ይሻለኛል። ካሉ እንግዲህ ወደ ጓዳዎ ገባ ብለው የሽንኩርት ወይም የስጋ አማርጠው መጠቀም ይችላሉ። ለምን ክፉ ያናግሩኛል አቶ በረከት!? እንደኔ እንደኔ ግን ከቢላ ኢሳት ይሻልዎታል!
የምር ግን እኛ ለአባይ መገደብያ ብለን በምናዋጣው ገንዘብ ራሳችንን እና እነ ኢሳትን መገደቡን ቀጥሎበታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ነው… ለቀጣይ አርባ አመት ለመኖር ያቀድነው…? አረ ይደብራል!? እንዴት ነው ነገሩ ድርጅታችን ካለመገደብ ስራ የላትም እንዴ!? በኑሮ ውድነት ሳብያ አመጋገባችን ተገደበ ዝም አልን፣ በተለያዩ አዋጆች እና ህጎች ሳቢያ ከሰዎች ጋር ያለን ወዳጅነት ተገደበ ዝም አልን፣ ነጋ ጠባ ሀርድ እየተሰጠን ንግግራችን ተገደበ ዝም አልን፤ አሁን ደግሞ አትሰሙም አታዩም ተብለን እየተገደብን ነው! ተዉ ይሄ ነገር ጥሩ አይመጣም!
እውነቱን ንገረን ካሉኝ መካሪ እያጣችሁ ነው።
ተዉ… ብሶቲቱ ዛሬም ታረግዛለች።
ተዉ… ብሶቲቱ ዛሬም ትወልዳለች።
ተዉ… ዛሬም ጀግና ይፈጠራል
ተዉ… ዛሬም ንጉስ ይከሰሳል
ተዉ… ኋላ ማጣፊያው ይቸግራል
ተዉ… ምክር መስማት ይሻላል።
ተዉ… ተዉ… ተዉ… ዉዉዉ…!
ለማንኛውም ለጠቅላላ እውቀትዎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተማ ያሉ ኮምፒውተር የሚጠቀሙ ወዳጆች የኢሳትን ዜናዎች እና ዝግጅቶች እንደምንም ብለው ለመከታተል እየቻሉ እንደሆነ ሰምቻለሁ። እናንተ በከለከላችሁ ቁጥር ሰዉ የተለያዩ መላዎችን መጠቀም ጀምሯል። ምናልባት ይሄ ክፉ ቀን ሲያልፍ ብልሀቶቹ በሙዚየም ይቀመጡ ይሆናል።
እኔ የምልዎ…
አብዮት አደባባይ የሚገኘው ሙዚየም እስቲ ዛሬ ጎራ ብለው ይጎብኙ። ደርግ በተቃወሙት ላይ ሲያደርግ የነበረውን የሚያሳይ ብዙ ነገር አለልዎት። እውነቱን ለመናገር አብዛኛውን ነገር ዛሬም ድረስ ያለ እንደሆነ ከጉብኝቱ ሲወጡ ራስዎ ይመሰክራሉ።
ለዛሬ ግን በደርግ ግዜ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ ወጣቶች ሃሳባቸውን ለመግለፅ በድብቅ ሲጠቀሙባት የነበረች የማተሚያ ማሽንን ሄድ ብለው እንዲመለከቷት ልጋብዝዎ።
ልክ እርሱን ሲመለከቱ መከልከል መፍትሄ እንደማይሆን ትዝ ይሎታል። ዛሬም በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶች ምን እያደረጉ ይሆን? ብለው ራስዎን ይጠይቁ? እውነት እውነት እለዎታለሁ። የዘጋችሁትን በሙሉ የሚከፍቱ ብልሀተኛ ወጣቶች በሀገሪቱ ሞልተዋል። እናም መገደብ መፍትሄ አይሆንም!
ልክ የተሜን (ተመስገንን)…የጠፋው ትውልድ እና የታህሪር ናፍቆት-፪…እንደጨረስኩ ነው ያንተን ያነበብኩት:: እናም አሁን አሁንስ መጨረሻው የደረሰ ይመስለኛል:: አረ ከተሜ ጽሑፍ በፊት “ከቅዳሜ ማስታወሻ” ያነበብክትን አንድ አስገራሚ ጽሑፍ ላካፍልህ (ካላየኸው)::…እስቲ እናንተ ብዕራችሁ ስለታማ የሆናችሁ በርቱ እኛንም አበርቱ::
http://tgindex.blogspot.be/2012/06/blog-post_18.html
thank you abe…of course…they said ” beseferut kuna mesefer aykerem” it’s all a matter of time but regardless the criminal members of tplf fate will not be diffrent from derg or mubark…therefore regardless how long it will take…..the criminal members of tplf/weyane will be facing justice and hung in public for the crimes that they committed against humanity….
Amara Ahyoch nachu
መጀመሪያ ነው አ.ንጂ መጥኖ መደቆስ
አውን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀሰ
የሚባለውን ተረት አትርሳ ፡፡ ለወያኔ የሚገባ ነው ፡፡ ወይኔ የሚሉበት ጊዜ እሩቅ አይደለም ፡፡
Ant Ahya arfeh tegeza!
አቤ እኔ ኤርትራዊ አድናቂህ ነኝ ጽሁፎችህ ሁሌ አያዋዙና እያሳቁ ስለያስተምሩኝ ይመቹኛል.. የዛሬ ግን እንጃ… አንተ እንደምትለው ሁሌ..”እኔ የምለው ”
በረከት በትውልዱ ኤርትራዊ ዩሁን እንጂ ስለ ኤርትራና ህዝብዋ ቅንጣት ታክል ደንታ እንደለለው የታወቀ እያለ ስለ ኤርትራ እንደሚቆርቆር አድርጎ ማቅረቡ .. በኔ አስትእያየት ለኢትዮጲያም ህነ ለ ኤርትራም የሚቢጅ አይመስለኝም.. እንዳው በዘር እንቁጠር ከተባለ እኔ እርግጠኛ ነኝ አብዛኛው የኤርትራ ደም የሌለው የኢትዮጲያ ህዚብ ከበረከት በላይ ስለ ኤርትራ በጎ እንደሚያስብና እንደሚጨነቅ እርግጠኛ ነኝ .. በኤርትራ በኩልም እንዲሁ.. እንደበርከት አይነቱ እንደሆነ ከሁሉም ህዝብ ዘር ሳይለዩ እንደሚፈጠሩና እንደሚፈሩ ያው ይወያኔ ዘመን ብዙ አያሳየን ስለሆነ ምስክር መጥራት አያስፈልገውም::
ታድያ ነገሩ እንዲህ ሆኖ እያለ በረከት ከኢትዮጲያ ይልቅ ስለ ኤርትራ ጥቅም ነው የሚያስበውና የሚጨነቀው እንበል ካልን ተራ ወሬና በሬ ወለደ አይነት ሊሆንብን ነው:: ምክንያቱም በረከት ኢሳትን ፈራ ከተባለና ኤርትራ ደሞ ኢሳትን እየለቀቅች ለበርከት ይግር እሳት ከሆነች …በምን ቀመር በረከት ኤርትራን እንደሚወድ ሎጂኩም አልገባህ ብሎኛል::
እዚህ ላይ አንድ እወነት ማስቀመጥ እወዳለሁ..ኢቲዮጲያ ውስጥ ስር ነቀል ለውጥ የሚመጣ ከሆነ በህዝቡ ብሶት ነው ኢሳት ደሞ የህዝቡን የድምጽ ብሶት በጭሆት እያሰማች ያለች ብርቅ የህዝብ ጀሮና አይን ሆናለች ብንል ቡዙም ክ እውነት አላራቅንም.. የ ኤርትራ ቲቭም እንድሁ በተገኘው አጋጣሚና እድል በራሷም አፍ ይሁን በኢሳት አፍ የኢትዮጲያን ህዝብ ብሶት እማጋለጥ አልቦዘነችምና ለበረከት ሁለቱም ኢሳትና ኤሪ ቲቭኢ የራስ ምታት እንደሆኑት የታወቀ ነገር ነው … ታድያ በረክት ችግሩ ከኢሳት እንጂ ከ ቲቭኢ ኤሪ እንዳልሆነ ለማስመል ያደረገው ሙከራ.. ከ አራብ ሳት ስራ አስካያጆች ያደረገው ድርድር ስለከሸፈበትና እርቃኑ ስለወጣ ብቻ ነው…. ስለዚህ ጉዳይ የኤርትራ መንግንስት ምላሽ በሰፊው ኢሳት ላይ ስለተዘገበ እዚህ ብዙ ማለት አልፈልግም..
ኣቤ እንግባባ ይሆናል ብየ እገምታለሁኝ .. በተርፈ ግን ቀጥልበት አስተምረን አስቀን ፈካ ፈካ አርገን… ሰሰናዩ ካብ ኤርትርዋያን የሕዋትካ.. ንፈትወካን ነክብረካን ኢና .. አምላኽ ምሳኻ ዩኹን .. አብ ቀጻሊ …ሰላም ንዓኻ ይኹን ክቡር ሓው…ciao a’prossima..
ተረዋእ
ወገኖቼ-ኢትሳትን በአረብ ሳት ሳይሆን፣ እኛው ይዘነው እንገባለን። እውነት መሰማት የተሳነው፤ የራሱን እርምጃ መውሰድ ይችላል። የውሸት ፕሮፓጋንዳ በነገሰበት ዘመን ቦለቲከኛ የሆነ፤ እውነት ያመዋል። ለድርድር አይቀርብም ያለ ለዚሁ ነው። እድሜ ለቴክኖሎጂ፤ ውሸት እየከሰመች እውነት ደግሞ እያበበች ትገኛለች። ኢትዬጵያ ውሸት አይመቻትም። ታሪካዊ አመጣጧም ይሄን ይመሰክራል። ለምድ ለብሰው ሲገቡባት ቦታ ብትሰጥም እንዳልሆነ አድርጋ ታስወግዳቸዋለች። እነ በረከት ብርክ ብርክ እንዳላቸው ያሳብቅባቸዋል። ሁሉን ነገር ጠርቅመው ዘግተው በሙቀት ታፍነው እያለቁ ነው። ላባቸው ይታየኛል! የለውጥ ሙቀቱን አበበ ካጦቸው ወዲህ፤ በእንፋሎት እጋዩ ይገኗሉ። መጥኔ ለእነ በረከት!!!!!!!!!!! ኢሳትን፤ አሁን በቅብብል እታች ቀበሌ ድረስ እያደረስነው ነው። ዋናውን ስቱዲዬ-ሸገር የሚዸግበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም!
ante weyane yetebalikew dedeb ahya ante neh ishy amaran lemesadeb man abah fekedelih wisha ante neh ahya dedeb bawkih adih neber indante aynetu koshahsa new eprdf inditela yemiyareghew dedeb
አሁን አንተን የመሠለ ጸሐፊ ከማይታወቁት የወያኔ የእሥር ጉሮኖዎች በአንዱ ቢወሽቁህ ኖሮ ወይም ይብስ ብለው ‘ከምድረ -ገፅ ‘ ቢያጠፉህ ኖሮ (ብቻ ሁሉንም የአንተን ክፉ አለቃቸው ሣጥናኤል አይስማው ) እኛ አንባቢዎችህ በምን እንዝናና ነበር? ብቻ አቤ ዕድሜና ጤና ይስጥህ ::
እኝህ ድንቀኛ የተሻለ ፎቶ የላቸውም ? እሳቸውም እንደ አቶ መለስ መድፍ ተደግፈው ሲያነቡ ኖረው በዚያው ትከሻቸው ተንጋዶ ቀረ ? የኢህአዴግ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ፣የአቶ መልስ አማካሪ፤ለኤርትራ ነፃነት ቆስያለሁ ለሚደፍራት አሰቀድሜ እሞታለሁ የሚሉት፤ የብአዴን (እዚህም’ዴ’ አለ?) አማራ ማድቤት ተበድለው ላደጉ ሊ/መንበር፣የብሔር ብሔረሰቦች የክርስትና አባት(…)
“ኢሳት ከሚገባ እሳት ልግባ አሉ” አርጎት ነው ! አቶ መለስ አታዝጎምጁን ! ነበር ያላችሁት ? “ምነው አቶ በረከት ለራስዎ ስምዎ ጥሩ አይደለም። አንዳንድ ንግግሮች ላይ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ምን አለበት!?
*አዎን እርስዎም ታጋይ አዜብ ጎላ እና መላኩ ተፈራም ከጎነደር እንደሆናችሁ ሕዝብ ያውቃል። ባለፈው ዓመት የ፳ኛው በዓላችሁን ስታከብሩ የጎጃምን ህዝብ ሰብስበው ያሉትን ያስታውሱ !! መቼም እርስዎ ከሚመሩት ኢቲቪ የኤርትራው የአማርኛ አገልግሎት ዝግጅት ይበልጣል እና ቢያንስ እነ ሚሚ ስብሐቱን፤ሰለሞን ተካልኝን ልከው ቢያሰለጥኗቸው ይሻላል አለበለዚያ ከባድ ችግር አለ።
**ክፉን ያርቅ የጠላት ጆሮ ይደፈን እና እናንተንና ደጋፊዎቻችሁን የሰማ ያመነ በቁሙ የመነመነ ነው።ባለፈው በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና በአንዱዓለም አራጌ የክስ መዝገብ የሰፈረውን መፈክርና ኢትዮጵያና ኤርትራ በጦርነት ውስጥ ሆነው ግንኙነት አድርገዋል የሚሰለጥኑ ወጣቶች መልምለዋል መርተዋል ብላችሁ የፃፋችሁት ክስ በጣም አስገራሚ የተዋጣለት ቅጥፈት ይገርማል… ከሀገር ውጭ በኢትዮጵያውያን የሚተዳደረው ኢሳት ቴሌቪዥን ግን የግለሰቦቹን ማንነት የየትኛውም የውጭ የፖለቲካ ድርጅት አባል ላለመሆናቸው ዘግቧል። በነገራችን ላይ ኤርትራ ውስጥ ፲፰ ኪሎ ሜ
ጥሰን ገባን ብላችሁ የአርብቶ አደሩን የፀሐይ መጠለያ ጎጆ አፈረሳችሁ አቃጠላችሁ።
የተማረከም የገደላችሁትንም ወንበዴ አላሳያችሁም ? ደግማችሁ ሄዳችሁ ድል አደረግን አላችሁ ወይ መሬቱ ወይ ሕዘቡ ከኢትዮጵያ አልሆነ ድሃ ለማስፈጀት ሕዝብን ለማሸበር ጥሩ ዘዴ ሆኖላችሗል። ምን አልባት የእነሱን ድንበር ለመጠበቅ ነፃ አገልግሎት ትሰጡ እንደሆነ ተናገሩ አትደብቁን።!!
**እንዲህ ‘ ኢሳት ‘ የቁም ‘እሳት’ ሆኖባችሁ የራሳችሁን ጣቢያ ሳይቀር ካስጠፋችሁ እውነተኛ ተፎካካሪ መሆኑን አመናችሁ! ሀገር አማን ነው ጠግበን እንደፋለን ትላላችሁ?፣ ተርበው የሚደፉ ያሳያሉ!፣ ዕድገታችሁን በፐርሰንት ትቆልላላችሁ? እነሱ በዴሲማል ማሽቆልቆሉን ያሳያሉ!፣የሕዝብ ፍቅር ፺፮.፮ አድጓል ትላላችሁ? “ህዝቡ ሳንፈልጋቸው ሃያ ዓመታቸው” ! ይላል…የአምስት ዓመት ኮንትራት አለን ትላላችሁ !ሕዝቡ “በቃ !” ይላል! ሕዝብ ከመሬቱ አልተፈናቀለም “መኢአድ” ጽ/ቤት(እዚህ ዴ የለም?) ለስብሰባ መጥተው ነው ትላላችሁ? ሕፃናት ሲያለቀሱ እመጫት ስታነባ ገበሬ ሲማረር በዜግነቱ ሲያፍር አቀርቡ! አዎ አቶ በረከት አውቀውበታል “እሳት ካልገባ እሳት ግቡ” በአመዱ ታሪካችሁ ይፃፍ በለው!
ካሉ እንግዲህ ወደ ጓዳዎ ገባ ብለው የሽንኩርት ወይም የስጋ አማርጠው መጠቀም ይችላሉ። ለምን ክፉ ያናግሩኛል አቶ በረከት!? እንደኔ እንደኔ ግን ከቢላ ኢሳት
የሚገርመው ነገር አሁንም የኢሳትና ሌሎችም የታገዱ ሚድያዎች ድምጽ በሚገባ እየተከታተልናቸው መሆኑ ነው፡፡ አምባገነኖች እንደሚያስቡት ወጣቱ ደደብ እና አላዋቂ አይደለም፡፡ ዜናዎች በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሱ ነው፡፡ በባሌም በቦሌም፡፡ እናንተ ፃፉ እንጂ አንባቢ አይታጣም፡፡
what goes around comes around (a matter of time)
[…] በዜማ አለቃቅሷል፡፡ ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፡፡መልካም […]
አቤ እንግዲህ ምክርሕን ሰጥተሃችዋል ካልሰሙ የስራቸውን ይስጣቸው ማለት ነው…