እኔ የምለው ኢህአዴግ ድሮ “ብሶት የወለደው” ነበር የሚባለው። አሁን ደግሞ የሚሰራውን ልብ ብለው ያዩ አንዳንድ ግለሰቦች “ጭንቀት የወለደው እያሉ”  ሲጠሩት እየሰማሁ ነው። ስጠረጥር የሆኑ እጣ ፈንታ ነጋሪ፤ “መጨረሻህ እየደረሰ ነውና ከባድ ጥንቃቄ አድርግ” ብለው አስጨንቀውታል መሰለኝ!  በየቦታው የሚወሰዱ ከእርግጫ የሚስተካከሉ እርምጃዎችን ልብ ብትሉ  የምርም ጭንቀት የወለዳቸው ናቸው!   (እኔን ጭንቅ ይበለኝ!  ወይስ አይበለኝ…?)

እናም ሀገሬው “ጭንቀት የወለደው የኢህአዴግ ሰራዊት በሃያ አንድ አመቱም በርካታ ነገሮችን እየተቆጣጠረ እና እየቆጣጠረ ይገኛል” እያለ እየቦጨቀው ይገኛል።

በየጊዜው የሚወጡት አዎጆች እና ህጎች በሙሉ “አይቻልም” የሚሉ ናቸው። ማንኛውም ታጋይ እና የታጋይን ገድል በየ ግንቦት ሃያው የሰማ ሰው እንደሚያስታውሰው ህውሐት ያኔ ጫካ እያለችም የማትከለክለው ነገር አልነበራትም። እንኳንስ ሌላው ቀርቶ ተፈጥሯዊ የሆነውን የወንድና ሴት ግንኙነት ራሱ በጥብቅ ከልክላ ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ደግሞ “ታጋዮቹ የፈለጉት ነገር ሁሉ ሲፈቀድላቸው እኛ ህዝቦቹ በተራችን ሁሉንም ነገር እየተከለከልን ነው።”  የሚል ሰው ተበራክቷል። እስከ አሁን በይፋ ያልተከለከለው የፍቅር ግንኙነት ብቻ ነው። እርሱም ቢሆን፤ “ተገናኝተን ሻይ ቡና እንኳ ለማለት የሚያስችል አቅም በማጣታችን እንደተከለከለ ቁጠረው!” ያሉኝ ወዳጆች አሉ።

የምር ግን ወዳጄ ዘንድሮ ያልታገደ ነገር ምንድነው? በየነጋው የምንሰማው ሁሉ እንትን ተከለከለ፣ እንትን ታገደ፣ እንትን ተዘጋ፣ የሚል ብቻ ሆኗል። ከዚህ በፊት ኢቲቪ እንደነገረን፤ “የአሁኑ መንግስት ልማታዊ መንግስት ነው።” ጠቅላይ ሚኒስትሩም ልማት እንጂ ለዚህ  ህዝብ ዴሞክራሲ ምንም አያደርግለትም በሚለው ዜማቸው ሲናገሩ እንደሰማነው “ዴሞክራሲ እና ልማት ምንም ግንኙነት የላቸውም።” ብለውናል። አንዳንድ ካድሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሲተረጉሙ ዴሞክራሲ “እንደውም የእድገት ፀር ነው።” ብለው እየተናገሩ ነው።

ታድያ እንደዚህ ከሆነ በአውራው ፓርቲ ስያሜ ኢህአዴግ ውስጥ “ዴ” ምን ልታደርግ ተሰነቀረች? ሰዉ እኮ ፊልም ሲታገድ፣ ስካይፕ ሲታገድ፣ ዌብ ሳይቶች ሲዘጉ፣ ራዲዮ ጣቢያዎች ሲጠረቀሙ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሲታወኩ “እንዴ!” እያለ የሚደነቀው እኮ በስማችን ውስጥ “ዴ” በመኖሯ ሳቢያ ነው።

“ዴ” ማለት ዴሞክራሲ ማለት ነው። እንግዲያስ ከልካዩ መንግስታችን ሁሉን ነገር እየከለከለ አረ የ ”ዴ” ስራ ምንድነው? በሚል ለተቺዎች አጋልጦ ከሚሰጠን አንድ ጊዜ ስያሜውን ቢያስተካክለው ግልግል ይሆናል የሚል አስተያየት አለኝ። ስለዚህም እንደሚከተለው አመለክታለሁ።

እኔ አመልካቹ ግለሰብ በሀገሪቱ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ገደብ የለሽ ክልከላ በሙሉ ልቤ የምደግፍ ስሆን፤ በዴሞክራሲ እና “በልማት መካከል ምንም ግንኙነት የለም” የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሬን ንግግር ወደ መዝሙር ቀይሬ ጠዋት ማታ የማንጎራጉር መሆኔንም ለማሳወቅ እወዳለሁ።

መንግስታችን ሁሉንም ነገር መከልከሉ ለእኛው አስቦ እንዳንበላሽ ሰግቶ እንደሆነም አምናለሁ።   ዴሞክራሲ የሚባለው ነገርም አጉል ቅብጠት መሆኑ ገብቶኛል። በመሆኑም በገዢው ፓርቲ ስያሜ “ኢህአዴግ” ውስጥ ያለችውን “ዴ” እንድትወጣልን በታላቅ አክብሮት እጠይቃለሁ።

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

22 responses »

 1. meretwork says:

  Hi abe!!! Thank you very much !! yes. no matter haw powerful. rich they are we will be free

 2. aberha says:

  abe you are a total smart guy and may god bless you and wishing you many many years.

 3. Abel says:

  መልስ
  ምንም እንኳን ማመልከቻዎ ለእኛ አስበው ቦሆንም፤ ዴ እንዳይወጣ ወስነናል። ለጊዜው በዲሞክራሲያዊ መንገድ የማንለቅ ብንመስልም-የማናመልጠው ነገር አለ። ሕዝቡን ብናስፈራራ፤ብንገድብ፤ አንድ ሃይል ከበላይ አለ። በእየቀኑ የፈቀደልንን ጊዜ እያነሳብን ነው። እናም-መወገዳችን አይቀርም። ተፈጥሯዊ ሞትን ማን ያመልጣታል። እንደ ሌሎቹ መገደብ አትቻል። እኖም ዴ ሳትጠፋ-ተፈጥሮ ስታስወግደን፤ እንወገዳለን። ቦቅቧቃ ከሞላባት አገር፤ከተፈጥሮ ውጭ ማንም እንደ ማያወርደን አረጋግጠናል!!

 4. Eyob says:

  Abe great piece.

 5. Wellabu G. says:

  Every body is writing as Abe is smart. I am so sorry that I lost the info that the definition for the word smart is changed.
  Abe you need a change while you are enjoying life abroad. You idiot man. By now every youth knows what is better to his life. DEDEB!!!

 6. hale says:

  Wellabu ante rasih dedeb malet min malet endehone yetefabih yimesilegnal Abe is our hero

 7. yigermal says:

  ante yehonk wellabu neger.dingay eras neh ende?eski beteshekemkew neger asib.alolo eras.

 8. ያገር ልጅ says:

  አቤ መቼስ “መልክ ጥፉ በስም ይደግፉ” እንደሚባለው ሆኖ ነው እንጂ “ዴ”ማ አገልግሎት መስጠት ካቆመች እኮ ሰነበተች። ባይሆን መተኪያ ቃል ቢፈለግላቸው ጥሩ ይመስለኛል። ለምሳሌ “ናሙና” የሚለውን ቃል በማስገባት ፊደሎቹ ሳይገድሉ ኢህአዴግ መሆኑ ቀርቶ “ኢህናአግ” ቢባልስ?

 9. tameru says:

  its nice to reading Abe

 10. mm says:

  ante wellabu…

  sew dedeb ayibalim…ante gin dedeb neh lol.

 11. fano tesemara says:

  gobze abe

 12. ጩቤው says:

  ተጋዳላይ አቤ ማመልከቻህን በመርህ ደረጃ ተቀብለነዋል፡፡ ሆኖም ኅብረተሰቡን በስፋት ካሳተፍንበት ልማት መር ተግባር አኳያ ፋይዳው ያነሰ ሆኖ ስላገኘነው ውድቅ አድርገነዋል፡፡ እንዲያውም ይህ የቦናፓርቲስቶችና የኒዎሊበራሎች የገማ እደግመዋለሁ የገማ አስተሳሰብ ስለሆነ እነርሱ ያግማሙትን እንኳን ለመቀበል ቀርቶ ለማንበብም ጊዜ የለንም፡፡ ይልቁንም በዚህ ብሎግህ ላይ ከሚወጣው ማስታወቂያ ትርፍ ተቆራጭ የሚሆን ለሕዳሴው ግድብ በራስህ አነሳሽነት እንድትሰጥ ሌሎችንም እንድታነሳሳ አዘንሃል፡፡ የማትታዘዝ ከሆነ ማስታወቂያውንም እንዘጋብሃለን (አራት ነጥብ)፡፡

 13. Hundanol says:

  Abe min nekah! LoL ‘De’ yemil fdel iko ayinebebim! It is soundless and even Meles never read it. After now never read that letter. It serves just like letter ‘b’ in the inglish word ‘debt’.

 14. Gn says:

  GN
  abe continue telling them technically.

 15. Yedersee lemewodke abe tekochawo Adnkhe neigne Geta Yebarke!

 16. Demelash says:

  Well another Era of Derg regime. May be this is part of the transformation package not to allow the people to use new technologies’ but we can sense that Woyane is under pressure. They do not know what they are doing. Like the final days of Derg.
  they wan to make more profit from this sector (telecommunication). we know that the sector is controlled by higher officials of woyane, their is a fake privatized transformation.
  they never realize that many of investors in Ethiopia use SKYPE for business meeting especially the international ones, so Mr. Shimels or Mr. Breket have you noticed this before the issue of this law? Actually it do not matter for you guys, you are ass hole, you do not have time to think in this way. Shame on you.
  .

 17. majesty says:

  Hello Abe. I like everything you touch. I want to tell you one thing. EPRDF is scheduling an evaluation meeting in the coming weeks about teachers performance. It is believed that the ruling party will fire teachers after the evaluation.

 18. በለው! says:

  “ዴ” ማለት ዴሞክራሲ ማለት ነው። እንግዲያስ ከልካዩ መንግስታችን ሁሉን ነገር እየከለከለ አረ የ ”ዴ” ስራ ምንድነው? ፊልም ሲታገድ፣ ስካይፕ ሲታገድ፣ ዌብ ሳይቶች ሲዘጉ፣ ራዲዮ ጣቢያዎች ሲጠረቀሙ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሲታወኩ “እንዴ!” እያለ የሚደነቀው እኮ በስማችን ውስጥ “ዴ” በመኖሯ ሳቢያ ነው።”
  ኢ – ኢሰብዓዊ…
  ህ- ህልም(ራዕየ) ቢስ…
  አ- አወናባጅ …
  ዴ- ዴዴብ…
  ግ- ግም (የበሰበሰ)…
  *ይህ “ብሶት የወለደው ” ሳይሆን “ብሶበት የተወለደ ብስብስ” ነው ብለን ደምድመናል!!!
  ** “ጭንቀት የወለደው” ? ሲፀነስ-በጭንቀት ፤ ሲወለድ-በጭንቅ ፤ ሲዳክር -ተጨንቆ ፤ ሲቆም-በጭንቅንቅ ፤ ሲራመድ-ተጨናቂ ፤ ሲኖር-አጨናናቂ ፤ ሲወድቅም-ጭንቅ ወልዶ ልጆቹ….ሽብር፣አመፅ፣ብጥብጥ፣ነውጥ፣ሁከት፣ ማፋጀት፣ማባላት፣ማናቆር፣ማበታተን ይሆናሉ።(ፆታቸውና መልካቸው በጭንቀቱ መጠን ይለያያል!)

  ***ስለዚህም” ጠቅላይ ሚኒስትሩም ልማት እንጂ ለዚህ ህዝብ ዴሞክራሲ ምንም አያደርግለትም በሚለው ዜማቸው ሲናገሩ እንደሰማነው “ዴሞክራሲ እና ልማት ምንም ግንኙነት የላቸውም።” ብለውናል። አንዳንድ ካድሪዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሲተረጉሙ ዴሞክራሲ “እንደውም የእድገት ፀር ነው።” ብለው እየተናገሩ ነው። እኛም ጠ/ሚኒስትሩም፣አብዮታዊ ዶማ-ክራሲም፣ ካድሬውም ፤አሽቃባጭና አሽቋላጭ ደጋፊም ለዚያ ድሃ የዋህ ሕዘብ የቃላት ጋጋታ ለልጆቹ ቁራሽ ዳቦ አይሆንም !

  ****ቢያንስ ነፃነትን፣ እኩልነትን፣መሠረታዊ የሰው ልጅ አስፈላጊ መብቱ ፣በማናቸውም መንገድ ተሸራርፎ ወይንም ተነፍጎ በጭንቀት መኖር የለበትም ! አስጨናቂው በእንቢኝታ ሙሉ በሙሉ መወገድ አለበት በለው!በቸር ይግጠመን>>>

 19. ወንዱ says:

  ይህ ጨለምተኛ አመለካከት የወለደው አስተሳሰብ ነው ብለን እንሄድበታለን። ሁዝቡ እስካመነብን ድረስ ዴሞክራሲያዊ መሆናችንን ተቀብሎ ከመሄድ ሌላ አማራጭ ያለው አካሄድ አይደለም። ዴሞክራሲ ሂደት እንደሆነ ሁዝቡ አምኖ ተቀብሏል:: ሂደት ደግሞ የሚደረስበት ሳይሆን አካሄድ፧ መሄጃ ነው። ይህን እዉነታ መካድ ልማታዊነትን ማደናቀፍና ፀረ ሰላማዊነት የሰፈነበት ፅንፈኝነት በመሆኑ ሊመረመር ይገባል። በሌላ ጎኑ ደግሞ ከኢህአዴግ ኋላ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ዴሞክራሲን እንደአቅጣጫ ጠቋሚነቱ እየተንቀሳቀሰበት መሆኑን ለቅንጣት ታክል የሚዘነጋ፧ እሱ ወራዳ፧ ዉሻ ነው:: ይህ ግልፅ መሆን ያለበት ይመስለኛል። እነዚህን ሁሉ ያገናዘበ የተሟላ ምላሽ እስኪሰጥህ ድረስ ማረፊያ ቤት እንድትቆይ ይደረጋል።

  ሌ ላ?

 20. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  አቤ ማመልከቻው እኮ ዘገየ ፡፡ ህዝቡ እራሱ ሰሚ አጥቶ እንጂ ዴ የሚለው ቃል አ.ና ዴሞክራሲ ለልማታችን ጸር ነው ብሎ ፡ ለጋሽዬ ነግሮአቸዋል ፡፡ አንተ አገሩውስጥ ሰለሌለ ሰላልሰማ ነው ፡፡

 21. Buta madingo says:

  Democracy is good only on paper not for people,people don’t need democracy because we TPLF are standing for development so development and democracy to gather is not necessary for Ethiopia so don’t ask to take out one alphabet from the logo if you do that next time you will be in jell to serve your time.

 22. Samson says:

  Thank you so much Abe! I think the name Abebe is becoming more famous as a name of heroes. We can mention from the earliest like Ras Abebe Aregay and Abebe Bikila and from now we can mention heroes like Abebe Gellaw and Abe Tokichaw. WOW! For all Abebes Thank you for what you have done for us and God Bless You and God Bless Our Country Ethiopia. Let God Emancipate Ethiopia from Sickness of TPLF poison!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s