ሰላም ወዳጄ እንዴት አደሩልኝ! እሰይ ሰላምዎ ይብዛልኝ አዳርዎም ሆነ ትዳርዎ ሳንካ አይግጠመው!

ዛሬ በጠዋት አንድ ወዳጄ መለዕክት ሰዶልኝ ነበር። መጀመሪያ አንዳንድ ልማታዊ ዜናዎችን ነገረኝ።  ከነዚህም ውስጥ “አንበሳ አውቶቢስ መሻሻሉን፣ ወደ አስር በሚጠጉ “ባሶች” ላይ ተስረቅራቂ ድምፆችን አስገጥሞ ፌርማታዎቹ የሚገኙበትን ቦታ የሚያስከፍለው ክፍያ እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ማቀበል ጀምሯል” የሚለው ይገኝበታል። “የመሳሰሉት መረጃዎች”  የሚለውን ስገምት፤ “ሃገራችን እያስመዘገበች ያለችው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት፣ በፀረ ሰላም ሀይሎች ሟርት እንደማይገታ፣ ለሚሊኒየሙ ግድብ  ከደሞዝ  ማስቆረጥ  የአውቶብስ ትኬት የማስቆረጥ ያህል ቀላል መሆኑን” እና ሌሎችም ልማታዊ መረጃዎች ይመሰሉኛል። በእውነቱ ይሄ የሚበረታታ እድገት ነው።

ይህንን እያደነቅሁ  የወዳጄን መልዕክት ዝቅ ብዬ ተመለከትኩ፤ “ፎርቹን የተባለው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ዘንድሮም ደቡብ ክልል ላይ ረሃብ አደጋ እያደረሰ መሆኑን የሚጠቁም ዜና ይዞ ወጥቷል።” ይላል። እንዴት ነው ነገሩ ከዚህ በኋላ ረሀብ የሚባል ወደ ኢትዮጵያ ምድር ድርሽ እንዳይል አድርገነዋል ተብሎ ሲነገር አልነበረም እንዴ…!? ለነገሩ የመንግስት ኢትዮጵያ እና የእኛ ኢትዮጵያ ለየቅል መሆናቸውን ቀስ በቀስ በቅጡ እየተረዳን ነው!

ጉደኛው ወዳጄ ካስቀመጠልኝ መልዕክቶች ውስጥ ሌላው ደግሞ፤ “ፌስ ቡክ ፕሮፋይልህን እንዳናየው ተከልክለናል!” የሚል ነው። አሁን በጣም ተደነቅሁ…
በእውኑ እኔ ማነኝ? ፌስ ቡኬስ ምንድነው? ስል ጠየቅሁ! እውነቱን ለመናገር ባለስልጣኖቻችን የለየለት “ፉገራ” ጀምረዋል። አረ ጎበዝ ባለስልጣን ስራ እንጂ ፉገራ አያምርበትም! አሁን አሁን ሳስበው ኢንሳ ውስጥ በግል የተጣላኝ ሰው ይኖራል እንጂ፤ መንግስትን ያህል ተቋም በዚህ ደረጃ  እንደ ወገብ ቅማል ጠምዶ ይይዘናል ብዬ  አላስብም።  ለዚህ ግለሰብ፤ “ፍሬንድ” ችግር አለ እንዴ ምነው እንዲህ ጠመድከኝ አረ “አፉ” በለኝ! ብዬ በማን በኩል እንደምልክለት ግራ ገባኝኮ!

ልብ አድርጉልኝ 1፤ ብሎጌ ተዘጋ እሺ ለልማቱ ካልጠቀመ እና መንግስት ካላመነበት ጥርቅም ይበል ብዬ ተደሰትኩ።

ልብ አድርጉልኝ 2፤ በመፅሀፌ ስም የተሰየመው “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” የተባለው የፌስ ቡክ ግሩፕ ተዘጋ “መቼስ ማል ጎደኒ” ብዬ ዝም አልኩ!

ልብ አድርጉልኝ 3፤ የገዛ ፌስ ቡኬ ከወዳጆቼ ጋር የማወጋበት፤ ሰዎች ጎራ ብለው “ፕሮፋይሌን” ማየት እንዳይችሉ ተደረገ። እንግዲህ ምን ልበል…? የገዛ ጓዳዬ ቁልፍ በመንግስት እጅ ከሆነ ምን ይባላል!?

ግን የምር እኔ ማን መስያቸው ነው? “ፍሬንዶቼ” እኔኮ ያ ወገኛው ሰውዬ ነኝ! ምነው እንኳ “ቀፈፈኝ” ብዬ ከሀገር የወጣሁ ግዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ “አንድ የደህንነት ሰው አስፈራራኝ ብሎ እንዴት ከሀገር ይወጣል? አቤ ወይ ጅል ነው ወይ ደግሞ ልጅ ነው! ማለት ነው” ብላችሁ  የፎተታችሁኝ! እ… እሱ እኮ ነኝ። ታድያ ለኔ ለምስኪኑ ይሄ ሁሉ ዱላ ተገቢ ነው?

ደሞስ ምን አጠፋሁ!? በመከርኩ…? በዘከርኩ…? የምሬን ነው የምለው ወዳጄ ሌላ ሰው መስያቸው ነው እንጂ እኔን እንደዚህ አይጨክኑብኝም “የወገን ጦር ነንኮ!” አለ ዘላለም ማልኮም ክብረት! “እኛም አልተባልን!” አልኩኝ እኔ!

ለማንኛውም ዛሬ ፎቶዬንም አብሬ ለጥፌዋለሁ! ውድ “ዘጊዎች” ስታዩኝ “እ… አንተማ የኛው ነህ!” ብለችሁ የተዘጉ በሮቼን እንደምትከፍቱልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አለበለዛ በአካል መጥቼ ለማመልከት እገደዳለሁ! (አትሳቁ የምሬን ነው!)

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

27 responses »

 1. የባንክ አካውንትህንም ጠንቀቅ ብለህ ያዘው [ካለህ]፥ አሁን አሁንማ ኢሜል ስትልክ እንኳ እኛ እናድርስልህ ሳይሉ አይቀርም:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምረው ያልጨረሱት የ “ሰበንቲ ፐርሰንት …” ወሬ ስለ ብሎጎች አፈና ነበር እንዴ፥ አልሰማኋቸውም እኮ?

 2. mati says:

  any one can open blocked blogs by adding https://……….; for example, https://abetokichaw.wordpress.com

 3. abdi says:

  hahhahhahahaha every points which u made are all funny but also real.

 4. aberha says:

  abe nefes neger…god bless you and wishing you all the best in your life…you are a true son of Ethiopia

 5. Kulich says:

  Here is a quote from Internet Sans Frontières:
  “ For instance Abe Tokichaw year exiled Amharic satirist WAS Forced to open new blogs for more Than 15 times by Changing domain names history of blogs. He looks like playing hide and seek with Ethio-Telecom. ”

 6. nafkot says:

  አይዞን ላያስችል አይስጥም አይደል አበው የሚሉት

 7. betu says:

  mechise maleGodeney

 8. Wellabu G. says:

  ውሸታም! ዕድሜክን ሙሉ በዚህ ትችት በመፃፍ ልትቋጨው፡፡ ደህና ነገር አትሰራም እንዴ፤ ወይም እንደ አለቆችህ እዛ ውጭ አገር የፅዳት ስራ ሰርተህ እንኳ ብር ብታገኝ አይሻልህም፡፡ Crazy!!

  • ውላቡ ምኑ ነው ውሸት? ትቀልዳለህ ወይስ የምርህን ነው? እናንተ አይደለም የአቤን ፌስ ቡክ እና ብሎግ ቀርቶ የፈረነረጀረ ፊልም “ዲክታተርን” ገና ለገና እኛን ይመስላል ብላችሁ የምታግዱ ሰዎች ኤኢደላችሁ እንዴ? ምንድነው ኢህ ሰው የዋሸው! ዘላለምህን ትችት ከምትጥፍ የፅዳት ስራ ሰርተህ ኑር ትላለህ እንዴ/ ታድያ አሁን ምን እየሰራ ይመስልሃል? የእናንተን ቆሻሻ እኮ እያጠዳ ነው! ችግሩ እናንተ አትጠሩም! ቆሻሻ አደራዎ!

 9. Abebe Gellaw says:

  ለበጎ ነው እዚጋ ግን ሳልናገር ማላላፈው ነገር የ ኢትዮጵያ ለውጥ በቅርብ እንደሆነ ነው

 10. Hundanol says:

  The so called ‘Wellabu’:
  In the first place you cant trade with this name-simply you do not belong to the community.
  Second, what lie have you seen from this innocent man struggling for survival, better tomorrow, and freedom? The lair is you who betrayed your soul,! You your self—who lost his moral to fill his porous stomach!
  Demo tsidatihin atsda… Dedeb! Ante aleh adel inde yemitakoshish. Matsdat iko sira new. Yawum tiru kifiya yalew!

  You are simply SUPER SUPER IDIOT!

 11. Abel says:

  እናንተ አበበ እምትባሉ ግለሰቦች ምን አለ ለቀቅ ብታደርጉን። የጎን ውጋት ሆናችሁን እኮ። አሁንማ ከጠቅላይ ሚንሰትራችን ፊት አዲስ አበባ ብሎ መጥራት አይቻልም። አበባ የሚለው ቃል አበበን ስሚያስታውሳቸው፤ ጂኒአቸው ይነሳና ይወድቃሉ። አንተ ደግሞ ሌላው የራስ ምታት ሆንክ። እባክህ ተዋቸው።

 12. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  አነሆ አንዲ ሆነ ፡ ኢትዮጵያ በምትባል ምድር ከባለፈው ሃያ አንድ አመት ጀምሮ ፡ በአገሪቱ ያሉት ጋዜጠኞች እና ጻህፍት በጠቅላላ ወዶ ገቦች ሆኑ እና ፡ አንድም ሰለ እውነት የሚጽፍ ፣ የሚናገር ሰው በጠፋ ጊዜ ፡ የምሬት ሰቃይ የወለደው አንድ ሽሙጠኛ ፡ በብዕሩ ወንጭፍ ይዞ መጣ የእውነት ወንጭፍ ፡፡ አሳዳጁን ጎሊያድን ዳዊት በወንጭፍ እንደጣለው ሁሉ ማለት ነው ፡፡ ይህም በብዕሩ ወንጭፍ የያዘው አንተ ነህ ፡፡ ፌስ ቡክ እና ብሎግህም ፡ ከእቶን እሳት በላይ የሚፋጁ ፣ እንደጥይት የሚበታትኑ ፣ ቃላቶች የሚመሸጉበት ምሽግ ፡፡ ለዚህም ነው ሁሌም ወያኔ የሚያመው ፡፡ ታዲያ አንተም ቃሉ ይፈጸም ዘንድ መጻፍህን ቀጥል እንጂ ከቶም ግራ አትጋባ ፡፡

 13. በለው! says:

  በሰላም ያደራችሁ…እናድር ይሆን ብላችሁ ያሰባችሁ…አድረናል እንዴ ብላችሁ እራሳችሁን የጠየቃችሁ ሁሉ… ማረጋገጫው በቀን አንድ ልማታዊ ዕድገትን ባባዶ ሆዳችሁ መከስከስ ነው።
  ከነዚህም ውስጥ “አንበሳ አውቶቢስ መሻሻሉን፣ ወደ አስር በሚጠጉ “ባሶች” ላይ ተስረቅራቂ ድምፆችን አስገጥሞ ፌርማታዎቹ የሚገኙበትን ቦታ የሚያስከፍለው ክፍያ እና የመሳሰሉትን መረጃዎች ማቀበል ጀምሯል” እልል…እልል…….. ይህ ድሮ የነበረ ነው የዛሬዎቹ የልማት መሪዎች ድሮ “የጥፋት አርበኞች” ስለነበሩ እያወለቁ ለልዋጭ…ልዋጭ…
  አጭሰውት ነው ። አሁን ፌርማታዎችን በመንገር የጀመረው ልማታዊ አሰራር ነገ “ዘመኑ የኤፍ ኤም” ነው እንዳለው
  የታክሲ እረዳት “አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ንቃት በአውቶቡስ” ይሰጣል ማስታወሻ ደብተራችሁን አትርሱ።!!!

  *የመንግስት ኢትዮጵያ እና የእኛ ኢትዮጵያ ለየቅል መሆናቸውን ቀስ በቀስ በቅጡ እየተረዳን ነው!
  “ፎርቹን የተባለው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ዘንድሮም ደቡብ ክልል ላይ ረሃብ አደጋ እያደረሰ መሆኑን የሚጠቁም ዜና ይዞ ወጥቷል።”
  **እኔ እንደሚገባኝ “የርሃብ አደጋ” በደቡብ ቋንቋ ሲተረጎም “የዕድገት አደጋ” ሊሆን ይችላል፤ በሗላም በጋዜጠኛው፣
  በጠ/ ሚኒስትሩ፤ በካድሬው፤ በክልሉ መስተዳደር ሲተረጎም ደሞ አዳምጣችሁ እራሳችሁን ታዘቡ… ለማስረጃ ፕ/ት ሁሴን ኦባማ …
  “የኢትዮጵያ ገበሬ በተሰጠው ብድር የራሱን ህይወትና የልጆቹን ትምህርት አሻሽሏል” የትኛው ? ማነው ? የት ክልል ?
  የት አነጋገሩት ? አንድ ገበሬ ፹፭ ከመቶ የሀገሪቱን ድሃ ገበሬ ይወክላል? ብላችሁ አትጠየቁኝ ግን አስቡ!
  በጣም የገረመኝ የኢህአዴግ ጋዜጠኛ ትርጉም ነው” ፕ/ት ሆሴን ኦባማ ኢትዮጵያ በእድገት ጎዳና በምግብ እራስን በመቻል ለተሰብሳቢው በአርዓያነት ያቀረቡት የገበሬውን የኑሮ መለወጥ ነበር።” ገበሬው በተደረገለት የመንግሰት ድጋፍ የራሱን እና የቤተሰቡን ኑሮ ለውጧል” ጥያቄው ገበሬው ተበድሮ ነው? ወይንስ ድጋፍ (የማይመለስ) ችሮታ ተደርጎለት? ገበሬ ነቃ !!
  ምን አልባት እነኝህ ነጮች ደገፍን(ዕረዳን) የሚሉት አበድረውን ነው ማለት ነው ? የአፍሪካን የእርዳታ ፳፭ ከመቶ ድርሻ ነጣቂዎቹ እኛ ስለሆንን ቀመሩ ከአሁን ይስራ። ዕረዳን ብለው ብድር ነውና ክፈሉ ካሉን ሸለቁን በለው! <<<<<<

 14. SAMI says:

  thanks for sharing us abe as usual!!

 15. በለው! says:

  >>>>>ልብ አድርጉልኝ 1-3 (…)ለማንኛውም ዛሬ ፎቶዬንም አብሬ ለጥፌዋለሁ! ውድ “ዘጊዎች” ስታዩኝ “እ… አንተማ የኛው ነህ!” ብለችሁ የተዘጉ በሮቼን እንደምትከፍቱልኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አለበለዛ በአካል መጥቼ ለማመልከት እገደዳለሁ! (አትሳቁ የምሬን ነው!) እንኳንም ሄደህ አለህበትም ሆነህ በዙ ክፍት አፎች አሉ ይበቃል ተው! ተው!

  የዚህ የፎቶ ነገር ሲነሳ አቶ መልስ በዲክታተር ማዕረጋቸው ከተነሱት ፎቶ ጋር ሲነፃፀር እሳቸው የሶላቶ መልክ ሲኖራቸው ያንተ ጥቁር፤ በጣም ጥቁር፤የደመክ ጥቁር ሰው መሆንህን አይቼ…በጣም ገረመኝ…! ጥቁር ሰዎች ባሉበት ሁሉ ድል ነው። ፃፈው እንደ አቤ ቶኪቻው…
  ግብ ማስቆጠርን እንደ ሳላዲን ሁሴን…
  ንገረው እንደ አበበ ገላው…
  ማጎንበስ እንደ አቶ መለስ…. “(ሲመክረኝ ሰምቼ ቢሆን ያኔ… አላቀረቅርም ነበር ይሄኔ !)” >>>> ይከፈትለት !!!!!!

 16. Wellabu G. says:

  Hundanol!

  You idiot man. GALA. You have to thank EPRDF for giving you a liberty in which others restricted to you.

  If you are cleaner, go ahead and collect money and you will go to hell. Nothing else. You crazy, idiot, the bullshit GALA people.

 17. Wellabu G. says:

  Hundanol;

  “………….who lost his moral to fill his porous stomach”. You must be kidding. You are the one still serving racists for the sake of your stomach. hahahahha………………………..
  ………………………… You do not have any moral to respond. ‘ cause the white people is fucking your ass. FUCK!!!!

  • Hundanol says:

   hahaha… let it be!
   In the first place i am not a servant of the idiots like you!
   Second I have never mentioned any thing racial.What is the need to blast all such racially? Just to prove your supper idiot nature! I thought you can at least think as a human being (though as an idiot one) But I now see that you are even less! You donkey!

 18. yosef says:

  አይ አቤ ትልቅ የመሆን ህልምህ አሁንም አልቀቀህም ”ትልቅ አምባሻ እንጂ ትልቅ ሰው የለም” ሲባል አልሰማህም ይህ አባባል ግን መለስን include አያደርግም እናማ እባክህን ይህን ለዛ የሌለው ፉገራህ ሰበብ በማደረግ እዩኝ እዩኝ አትበል ሰንት የሚታይ እያለ

  • MYESAW KASA says:

   ወይ ዮሴፍ…. ልጁን እኮ አለቆችህ ናቸው ያከበሩት! እሱም ይህንኑ ተናግሯል። ለአንድ ፎጋሪ ይሄንን ያህል ክትትል ነውር አይደለም እንዴ! ዛሬ ግን ምነው አስተያየት ለመስጠት ዘገየህ!? አበል አሳነሱብህ እንዴ…!? ሃሃሃ… የምር ዮሲ ለኢህአዴግ ያለህን ተቆርቋሪነት አደንቃለሁ። ግን ከመለስ ጋር ዘመድ ናችሁ!? ወይስ ራሱ መለስ ነህ…? የሰው ትልቅ የለውም የአንባሻ እንጂ ያልከው ተመችቶኛል። ግን ይሄ የሚሰራው እንደውም ለመለስ ነው!!!!

 19. Wellabu G. says:

  Hundanol!

  Try to think twice PLEASE! Who is donkey? Me or YOU. Unable to stop my laugh. You poor man. Don’t you know that until the early of the decade – you and your parents were not considered as a human being in Ethiopia? Don’t you have what the so called Minilik said? Please, try to know who you are. Poor!!!!

 20. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  እባክ ፡ ዮሲ ትልቅ አምባሻ የት እንዳለ ብትነግረኝ ? ትልቅ አምባሻም ሆነ ዳቦ እኮ ተረት ተረት ሆኖአል ፡፡ ነገሩ አንተ የት ታውቃለ ፡፡ በአበል እየኖርክ ፡፡

 21. Muktar Msurur says:

  Abe bertalign Allah kante gar yihun……….agerachininim selam yadirgilin…………bereketunim yisten(egnihignawun bereket aydelem tadiya)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s