የዛሬ ሳምንት ከደቡብ አፍሪካ ባፋና ባፋናዎች ጋር በሳላዲን ሰይድ ጎል አቻ ተለያይቶ መነጋገሪያ የነበረው ብሄራዊ ቡድናችን ትላንት ደግሞ አሁንም በማይጨበጠው አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ፤ ሁለት ለምንም በሆነ ውጤት መካከለኛው አፍሪካን አሸንፏል። በስታድየም፣ በቴሌቪዥን እና በኢንተርኔት ስንከታተል የነበርን በርካቶችም ፈንድቀናል።
ሳላዲን ሰይድም ከስታድየሙ ታዳሚ “ጥቁር ሰው” የሚል ማዕረግ ተሰጥቶታል። እንደውም አንድ የፌስ ቡክ ወዳጃችን እንዲህ ብሎ ለጥፏል።
“ብራዚል ሊሄድ ሳላዲን ኑ ካለ
አረ አይቀርም በኢትዮጵያ ስለማለ
ታድያ ልጁስ ሲጠራው ምናለ….
ወ….ይ…
ወይ ባለለው ያኔ
አዝናብኝ ነበር ሀገሬ”
እንግዲህ ሀገሩን የሚያኮራ የጀግና ስራ የሚሰራ ሁሉ በአሁኑ ግዜ “ጥቁር ሰው” የሚል ማዕረግ የሚያገኝበት ሁኔታ ነው ያለው! (እንዲህ ነው እንጂ የኔ ኢቲቪ አይሉኝም!)
እዝች ጋ ውድ ቴዲ መለኪያ ሰጥተከናል እና እግዜር ይስጥህ! ብለን ማመስገን ይገባናል። እውነቱን ለመናገር ራስህም “ጥቁር ሰው” ነህ ብዬ ደፍሬ ለመናገር እወዳለሁ። እንዴት…? የሚል ካለ ምንም እንኳ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሚኒሊክ ሲባል ደማቸው ቢንተከተክም የመጣው ይምጣ ብሎ “ጥቁሩን ሰው” አሞካሽቷልና… እደግመዋለሁ ቴዲም “ጥቁር ሰው” ነው!
በነገራችን ላይ ከላይ በርዕሴ ያልጠቀስኳቸው በርካታ “ጥቁር ሰዎች” እንዳሉን ለማስታወስ እወዳለሁ።
ባለፈው ጊዜ እንዳየነው አበበ ገላው ቆሌ ገፋፊውን ጠቅላይ ሚኒስተር ቆሌያቸውን የገፈፈ ጊዜ በበርካቶች ዘንድ “ጥቁር ሰው” የሚል ማዕረግ ተሰጥቶት እንደነበር እናስታውሳለን። አረ እዚህ ጋ ሳይጠቀስ የሚያልፍ ነገር አለ። ትላንት አዲስ አድማስ ጋዜጣን በኢንተርኔት መስኮት ጎብኘት አድርጌው ነበር። “አበበ ገላው በድጋፍ እና ተቃውሞ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል” የሚል አንድ ዘገባ ወጥቶ አየሁ። ፅሁፉን ልብ ብዬ ስመለከት ጠቅላይ ሚኒስትራችንን እና እጅግ ወዳጆቻቸው የሆኑ ግለሰቦችን ከደረሰባቸው የቅስም ስብራት ለማከም የተፃፈ ይመስላል።
አረ እንደውም፤ “አበበ ገለው ዋሽንግተን ዲሲ ያልሄደው የኢህአዴግ ደጋፊዎችን ፈርቶ ነው!” የሚል ነገርም አይቻለሁ። እሰይ አድማሶች እንዲህ ነው እንጂ… ለዚህ አኩሪ ተግባር “ጥቁር ሰው” ባልላችሁም ለጊዜው “አስር አለቃ” ልበላችሁ ይሆን…!? ግን ለምን ይዋሻል…? በአዲስ መስመር እወቅሳችኋለሁ፡
እኔ የምለው ለምን ድርጅታችንን ታሳስቷታላችሁ? በእውነቱ ኢህአዴግ እንኳንስ ከፍቶት በተሰደደው የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ይቅርና በአገርቤቱ ደሴ እንኳ እናንተ እንደምትሉት አይነት ደጋፊ አለውን…? (ዲሲ እና ደሴ ለማመሳሰል ብዬ ደሴን ጠቀኩ እንጂ በመላው ኢትዮጵያ… የኢህአዴግ ደጋፊ ማነው…?) በእውነቱ በመላዋ ኢትዮጵያ ኢህአዴግ ብዙዎችን ራሱ በአበል እየደገፈ ነው እንጂ ህብረተሰቡ ኢህአዴግን ለመደገፈ አቅም አለውን!? በእውነቱ በዲሲ በርካታ ደጋፊዎች ቢኖሩት ኖሮ ባለፈው ጊዜ ባለስልጣኖቻችንን ለአባይ ገንዘብ ስብሰባ በሄዱ ወቅት በተቃውሞ ብዛት ንግግር እንኳ ማደረግ ተስኗቸው ይመለሱ ነበር? ለማንኛውም አድማሶች ድርጅታችን አታሳስቷት…! በተለይ ውጪ ሀገር ከኤንባሲው የጥበቃ ሰራተኞች ውጪ ይሄ ነው የሚባል ደጋፊ እንደሌለን እኛም እናውቀዋለን!
ወደ ዋናው መስመር ስንመለስ… ሀገራችን በተለያየ ቦታ የተለያዩ “ጥቁር ሰዎች” እያፈራች ትገኛለች። ልብ አድርጉልኝ እነዚህ ጥቁር ሰዎች ባንዲራዋን ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ናቸው እንጂ ባንዲራዋን የሚዘቀዝቁ አይደሉም። በድፍረት የሚናገሩ ናቸው እንጂ በአፍረት አንገት የሚደፉ አይደሉም። ሀቅን የሚለብሱ ናቸው እንጂ ውሸት የሚቀዱ አይደሉም።
ሳላዲን ሰይድ ኢትዮጵያ ለአለም ዋንጫ ለማለፍ ባደረገችው ማጣሪያ እስከ አሁን ያስቆጠረቻቸውን አምስት ጎሎች በሙሉ አስቆጥሯል! በዚህም ባንዲራችን ከፍ ብሎ ተውለብልቧል እኛም ሳላዲንን ብለነዋል “ጥቁር ሰው” ይህንን ማዕረግ መላው የብሄራዊ ቡድኑ አባላትም ይጋራሉ!
አበበ ገላው እና እስክንድር ነጋ ሁለቱም የሚወክሏቸው ህዝቦች አሏቸው አበበ በውጪ ሆነው ደከመኝ ሳይሉ ለሀገራቸው መልካም እንዲመጣ አበሳቸውን የሚያዩ ሰዎችን፣ እስክንድር ደግሞ “ሀሰት ለመናገር አትሻም ምላሴ ለእውነት እሞታለሁ አልሳሳም ለነብሴ” ብለው በየ እስር ቤቱ መከራቸውን የሚያዩ የኢትዮጵያ ልጆችን ይወክላሉ። ወክለውም የ “ጥቁር ሰው” ማዕረግን ያገኛሉ።
“ጥቁር ሰው! ያብዛልን እኛንም “ጥቁር ሰው” ያድርገን አሜን በሉ!
Ameen Abe!!!
amen
አንተ’ማ(እናንተ’ማ) አቤ ወይ እንደ ሰው ታርክ አትሰራ ወይ ታርክ አትጽፍ እንቶፍንቶህን ወሬ ለቃቅም ግድ አይዞህ ያኔ መጨረሻ ስትሰናብት መቃብርህ ላይ ”በተወለደ በ 0 አመቱ አረፈ” ተብሎ ይጻፍልሀል ምክንያቱም ምም እየኖርክ አይደለማ በዚ ምደር
what about u josi … i call u black A$$
Yehe kebade alemetadel new yosef. Keshem atehun. endet melese sew yanoral
አንተስ ማን ትባል ዮሴፍ: በ21ኛው ክ/ዘመን በጎሳ የጋርዮሽ አስተሳሰብ ፓርቲ የምትደግፍ?
እስኪ መጀመሪያ ፊደል ተማር
ha ha ha ha……GA GA GA GA GA GA…….Lella yeleheme Agazi weyane Yosef !!! lol
ዮሴፍ አንድ ነገር አትዋሽ የአቤ ጥሁፎች ሱስ ሰለባ ሆነሃል! ወይም ደግሞ በትክክል ለአቤ ተመደብከው ደህንነት አንተ ነበርክ ማለት ነው። ወይ ታሪክ አትሰራ ወይ ታሪክ አትጥፍ ብለህ ለመተቸት ሞክረሃል። አቤ እስከ አሁን ሁለት መጣፎችን አበርክቶልናል። እነርሱም የየወቅታቸውን ታሪክ የሚዘክሩ እንደሆኑ በርካቶች ይስማሙበታል። አሁንም አቤ በየቀኑ እየመዘገበ የሚያስቀምጥልን ታሪክ ቀላል የሚባል አይደለም። በበኩሌ ትጋቱን አደንቃለሁ። ትጋቱን ብቻ ሳይሆን አቤ እንደሌሎች በውጪ ሀገር እንደሚኖሩ ጋዜጠኞች ጥንፈኛ አለመሆኑንም አይቻለሁ። በዚህም ሊደነቌ፡ይገባዋል እላለሁ። ለነገሩ አንተም የሚያመላልስህ አድናቆት ነው!
koy ene emlew ye aben shimut ento fento yalkew yante yehe asteyayet min libal new? wendim yosef yalhone entofento tsfe yesewn agenda askeyralehu bileh kehone tebanobetal lela neger mokir.
ዮሱፍ አቤንማ እንዲኖር አላረጋችሁትም በ እርግጥ እትብቱ ከተቀበረባት እናት ምድሩ እንዳይኖር ስላረጋችሁት እንደሞተ ይቆጠራል;; ለሞሞት ያብቃው አንጅ እስከሞሞት አንተንና መሰሎችህን በተሳለ የብእር ሰይፉ እውነትን እየተናገረ ባንዳ ካህዲዎችን እኩይ ምግባራቸሁን ከ እግር እግር እየተከተለ አንጀታችሀን እያቀጠለ የበሸታው ስሙ የማይታወቅ የጭንቅላት እጢ ሁሉ እያስበቀለ፤ እኛን እንደሳላሀዲን ጨዋታ አንጀታችን እያረሰ እሰከሚሞት ይኖራል ; ሲሞትም በመቃብሩ ላይ የሸሙጦች አይነት በ አይነቱ በ አማረ የቁም ፁሁፍ ይቀመጣል እኔን ደሰ የሚለኝ የናንተ የካድሬወች የፍቅር ደብዳቤ ጎልቶ ቢቀመጥ ደስ ይለኛል አቤ ጥቁር ሰው;
Ezi degmo mn alkesekesachu yeweyane frfari albeka alachu ezi yenesanet erehabtegna enji hodamoch ayasfelgunm ks ks ks abe tikur sew!
Abe, antem ´´tikur sew´´ yemilewun mareg deserve tadergaleh!
the so called yoseph, you are a black dog (tikur wusha), even the crazy one!
ዮሲፍ ” ብኩን ሰው”
አቤ ጥቁር ሰው አሜን አሜን አሜን
ዮሴፍ አታፍርም እንዴ አቤንማ በደንብ ታውቀዋለህ:: አቤ ጥቁር ሰው:
በሥራ ከሆነ፣ የዘመናችን ‘ጥቁር ሰው’ መለስ ዜናዊ ብቻ ነው።
Yosef ante mechem tiru tamagn hodam baria neh
Abe – Tikur Sew! You must be man. ’cause you are racist. The one who is your legend – the Tikur Sew – is the Black Hitlor. Don’t you know this.
FUCK AMHARA!!!
ለ ዉድ Wellabu G. አንዴ አማራን አንዴ ኦሮሞን ትሳደባለህ ፤ በምን ያክል እንደዘቀጥክ (ወደታች እንደወረድክ) ለማሰብ ቀላል ነዉ።
እባክህን እራስህን እየጎዳህ ነዉ። እንዲህ በከፋ የጎሳ ጥላቻ ተሞልተህ አብሮህ የሚኖረዉን መልካም ሰዉ ሁሉ እንደማታምን እርግጠኛ ነኝ፤ አምላክ ይርዳህ።
ስለፅሁፉ ብቻ አስተያየት ለመስጠት ብትሞክር ሰላምህን እንደምታገኝ አልጠራጠርም፤ ካለበለዚያ በቅርብ ቀን የምታብድ ይመስለኛል !!! (ስላሳዘንከኝ ነዉ ወንድም)
Amen Belenal Hulachenm Le Ethiopiachen Tikur Sew Yadergen.