ከዚህ በፊት አህመድ አብዱራህማን የተባለ ወዳጃችን በፌስቡክ ግድግዳው ላይ ይህንን መረጃ አድርሶን  ነበር።

“(BLOCKED FACEBOOK GROUPS IN ETHIOPIA) Anti Ahbash- New Group, YE ABE TOKICHAW SHEMUTOCH, ETHIIO ISLAMIC ART AND DAWAA GROUP, Ethiopian Muslim Writers Group, Freedom of Religion foe All Ethiopians, The Whole Ethiopian Muslims Union and Revolutin Against Mejlis.”

ይህ ወዳጃችን ዜናውን እንዳደረሰን እርግጠኛ ለመሆን ብዬ አዲሳባ ወዳጆቼ “YE ABETOKICHAW SHEMUTOCH” የተሰኘችውን የፌስ ቡክ ግሩፓችንን ይሞክሯት ዘንድ ጠይቄ ነበር። እውነትም ብዙዎቹ ወዳጆቼ “ግሩፓችንን” መክፈት ተሰኗቸዋል። እኔም በልቤ በዚህ ደረጃ መንግስቴ “እያንዳንዷን ንግግር ያፍናል” ብሎ ለማመን እየተቸገርኩ ችግሩ ከ”ኔትዎርክ” ይሆናል። ብዬ ጠርጥሬ ነበር። ነገር ግን ጥርጣሬዬ አለቅጥ ለኢህአዴግ ከማድላት የመጣ እንደሆነ በርካታ ወዳጆቼ አረጋግጠውልኛል። አዎን… የእኛይቱን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” ግሩፕ ጨምሮ ሌሎችም ስለ ዴሞክራሲ፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚሰብኩ የፌስ ቡክ ግሩፖች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ ተከርችመዋል!

ምንድነው ጉዱ…!?

አረ ተዉ ጎበዝ መዝጋት ማፈን መፍትሄ አይደለም። እንዴ  አለቆቻችንም ቢሆኑ እኮ  ከአንድ ለአምስት አደረጃጀት ውጪ የሆነው ህብረተሰቡ ምን እያለ እንደሆነ መስማት አለባቸው!  አረ ግዴየላችሁ “እረኛ ምን አለ?” ብላችሁ ጠይቁ! ተዉ ይህ አይነቱ በጉልበት የሚገኝ ዝምታ ወርቅ አይደለም…! ተዉ ተዉ ተዉ…!

ተያይዞ በደረሰኝ ዜና አዲሱን የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅን ተከትሎ በአዲሳባ ኢንተርኔት ካፌዎች በስካይፕ አገልግሎት እንዳይሰጡ መከልከላቸውን ሰምቻለሁ።

ምክር ቤቱ ያፀደቀው አዲሱ አዋጅ፤ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ወይም የፋክስ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውንም ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ 3 ዓመት እስከ ስምንት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በስልክ ጥሪዎቹ ሊያገኝ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን ገቢ አምስት እጥፍ በሚሆን መቀጫ ይቀጣል፡፡”

የሚል ሲሆን በስካይፕ ማስደወልን በይፋ አይከለክልም። ታድያ ኢንተርኔት ካፌዎቹ ለምን ተከለከሉ ብለን ስንጠይቅ…የሚከተለውን ጥርጣሬ እናገኛለን

በስካይፕ የሚደረግ ግንኙነት የቴሌ ሰዎች ሳያዳምጡት ወይም “ሰርቨር” ላይ ሳይደርስ በደዋይ እና ተቀባይ ብቻ የሚደረግ ውይይት ነው። በርግጥ በአንድ ወቅት ይህንን የነገርኩት ወዳጄ “እኛ እንኳንስ በስካይፕ የምናደርገው ጨዋታ ይቅርና፤ ለእግዜሩ የምናደርሰውንም ፀሎት ሊጠለፍ ይችላል ብለን እንጠራጠራለን!” ቢለኝም። እውቀቱ አለን የሚሉ ሰዎች ግን ስካይፕ ከጠለፋ ውጪ ነው። ብለውናል። (በርግጥ ይህንን ብለን መንግስታችንን ክፉኛ አናማም) ከዚህ በፊት እንዳየነው መንግስት ነብሴ እያንዳንዷን የጓዳ ሚስጥር ቁጭ ብሎ ለመስማት ፍላጎት ያለው መሆኑ ይታወቃል። እናም ስካይፕ የተከለከለው ለዚህ ይሆን? ስንል እንጠርጥራለን!   ከዛም ይቅር በለን እንላለን!

ውድ ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች አረ ይሄንን ነገር አጣሩ… በስንቱ ነገር ስማችን ይጠፋል!?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

2 responses »

  1. yetezegan site or facebook group http:// yemelewene https:// bemaderege mekefete yechelalu menegeset yehinin mekefete ayechelem b/c it is encrypted or filter madrege ayechelume

  2. Haron says:

    አይዞን አቤ በስሚ ስሚም ቢሆን እኛው እናደርሳለን!!! የ proud to be ethiopian ምክር ብትሞክረዉ አሪፍ ይመስለኛል:: We are always with U Abie!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s