ብሎጋችን 3 ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ከመቶ ሃያ ሺህ ግዜ በላይ ተጎብኝታለች። ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላዩ ወደ ሀገር ቤት መግባት ከመከልከሏ በፊት በኢትዮጵያ የተጎበኘችው ነው። በነገራችን ላይ ይህ ቁጥር የአንጋፋይቱ ብሎጋችን ብቻ ነው “የተሰዉ” አስራ አምስቱን አያካትትም። በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያላችሁ ወዳጆቼ “ቢረባም ባይረባም እስቲ እንይለት” ብላችሁ ጨዋታዎቼን የተመለከታችሁልኝ በሙሉ እግዜር ያክብርልኝ።

አንዳንዶች በጨዋታዎቼ ብስጭት እያሉ “አሁንስ የቡና እና የአረቄ ጨዋታ አደረከው” ሲሉ ሊወቅሱኝ ሞክረዋል። እነዚህን ወዳጆቼን እላቸዋለሁ፤ “ፍሬንዶቼ” እኔ እኮ ከበፊቱም የአረቄ እና የቡና ወግ ነው ማውጋት የምፈለገው… እዝችው ላይ አረቄም ሆኑ ቡና “የጨዋ መጫወቻ” እንደሚባሉ ማስታወስ ይገባል።

ከበድ ጠለቅ ያሉ ትንታኔዎችን ፍለጋ ወደዚህ ብሎግ ከመጣችሁ ሰፈር ተሳስታችኋል ልላቸው እወዳለሁ።

እስከ አሁን ድረስ በብሎጋችን ላይ አስተያየት በመስጠት ግንባር ቀደም ቦታውን የያዘው ወዳጃችን በለው ሲሆን በትጋት 31 አስተያያየቶችን ሰጥቷል። በነገራችን ላይ ወዳጃችን በለው አስተያየት ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ግዜ እኔ ያጎደልኩትን ሁሉ ነው የሚያሟላልን። እናም በይፋ ማመስገን ይገባል። ሽብር ሽብር ይላል፣ ቁልጭ እና ዮሴፍ የተበሉ ወዳጆቻችንም በብሎጋችን ላይ እያንዳንዳቸው ስምንት ስምንት ግዜ በአስተያየት ተሳትፎ አድርገዋል። እነሆ ምስጋናችሁን ውሰዱ…! ምርጥ ወርቅ፣ ኢትዮጵያዊ እና ሳሚ አልረሳኋችሁም እባካችሁ በአስተያየታችሁ ግፉበት!

በፌስ ቡክ፣ በኢሜል እና በስልክ “አይዞህ፣ በርታ፣ ከጎንህ ነን” እያላችሁ በርካታ ማበረታቻ፣ ምርቃት እና ውዳሴ ላቀረባችሁልኝ ወዳጆቼ ምስጋና አይበቃችሁም ግን ሌላ ከየት ይምጣ..!?

በመጨረሻም

“የፕሬስ ነፃነት በተከበረባት” ሀገር ከአስራ አምስት ግዜ በላይ በታታሪነት ብሎጌን ለዘጋችሁት “ዘጊዎች” ያደረጋችሁት በሙሉ ከአክብሮት የመጣ ነው ብዬ በማሰብ እግዜር ያክብርልኝ ልላችሁ ፈልጌ ነበር… ሳስበው ይሄ ሊያንሳችሁ ይችላልና ሌላ ምርቃት አፈላልግላችኋለሁ!

ለማንኛው ሰኞ ግንቦት ሃያን በዕለተ ቀኑ በሚዘክረው ጨዋታችን እስክንገናኝ ድረስ መልካም ሰንበት ይሁንልን ብንባባልስ!?

አሜን!

መልካም ሰንበት!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

6 responses »

 1. Addisaba says:

  Lol የፕሬስ ነጻነት በኢትዮዸያ በሳቅ ቅቅቅ ለቅንቅኖች

 2. በለው! says:

  እኛም ዕድሉን በቅርብ አግኝተን ለመሳተፍ በመብቃታችን እናመሰግናለን። ቀድሞም እንሳተፍ ነበር የምንገናኘው በሰው ሠፈር ስለነበር ሰው እየበዛ አልተያየንም። ድሮም ” ደበዳቤ ቢልኩት እንደቃል አይሆንም ….” ብሏል አሁን ዕለት በዕለት …. በቀልድ እያዋዙ፣ በሳቅ የሰው ልብ እያፈረሱ፤ ቁምነገር ማስጨበጥ መልካም ነው። በተለይ የኢህአዴግ ደጋፊ የጠ/ሚ እና የቤተሰባቸው ጆሮ፣ የኢቲቪ ዓይን፤የፓረቲው ደጋፊዎች አማካሪ ሆኖ ከመስራት በቀር የተሻለ ስደት ከየት እናምጣልህ ? ?

  ባለህበት እያደነቅህ፤እያመሰገንክ ኑር፤ሽንብራ በጠፋ ቁጥር ሆዳቸው የሚረበሽ እነ ሽበሩ የእነ አሸብር ሠፈር ልጆችን ሰላም በልልን።ሰሞኑን አጎታቸው ሁሴን ኦባማ አንድ የላኩትን መልዕክት ለመጻፍ ፈልጌ” መረረን ኢህአዴግ የምትሉ እጃችሁን አውጡ ! ብለህ ምላሳችን ሳይቀር አውጥተን ብንመጣ አንተም የሐሳብ መስጫ ውል ‘ከጭለማና ሽብር ማተሚያ ቤት’ ኮረጅህ መሰለኝ አሳብ መስጫው ተዘግቷል ይላል! ይቺ ናት የአቤ ኩረጃው ብለን በሳቅ……..

  መቼም ወዳጅህ አቶ መለስን የሚነካብህ አትወድም እኔም ቅርበት የለኝ የምኖረው ከሰማይ ጥግ ነው።ለመሆኑ ደውለህ ፅፈህ ወይንም በሌላ በመትገናኙበት ዘዴ ስለጤንነታቸው አረጋገጥህ ? ሰውዬው አሁንም ያሉበትን አላወቁም አሉ የጨበጣቸውን ሁሉ ሰባ ፐርሰንት ይላሉ አሉ። ካሜራ የያዘ ጎብኝ ነጭ ዜጋ ባዩ ቁጥር ይታሰር ይላሉ አሉ።

  እሱ ነገረኝ እነዳትል አንድ በጆሮህ ሚስጠር ልንገርህ … ወዳጅህ አቶ መልስ ፈሪ ናቸው ሲሉ ከብዙ የጥንት የበረሃ ጓደኞቻቸው አንዱ አቶ ገብረመድህን አርዓያ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። አ/አ በሚሚ ስብሐቱ ሬዲዮ የአንድ ኢትዮጵያ ሬዲዮ አዘጋጅ ከዋሽነግተን ዲሲ ዮሴፍ የሚባል እና የቀድሞው የሞንትሪያል ሚግል ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ተማሪ የዛሬው የወያኔ መንገደኛው ጋዜጠኛ ካናዳ ሥራ ማግኘት አልቻለም አሜሪካ እነዲሁ በእየ ምግብ ቤቱ ያንዛርጥ የነበረ ሲቀደዱ የነበረውን በሰንበት አድምጠው……
  ” ጠ/ሚ መልስ ዜናዊ ደነገጡ ያሉት የሚገርም ነው አንድ ሰው አዳራሹ ውስጥ አደናቅፎት ሊወድቅ ሲል የጠራቸው መስሎአቸው ነው።….. ሰውዬው መድፍ ሲያገላበጡ እንደኖሩ አያውቁም እንዴ?” ይላል ቢኒያም ከበደ
  እርግጠኛ ነኝ ካናዳ እና ደደቢት በረሃ ቅርብ አደሉም ቢሆን እኔም እሄድ ነበር።ግን ይህ ሚስጥር ከአንተ እና ከወዳጅህ ተመስገን ደስ አለኝ አያመልጥም እና ለምን ደበቃችሁን ብዬ በጣም ታዘብኳችሁ አልተቀየምኩም ይሁን…ለነፍሳችሁ።?

  የወዳጃችሁን ብሎግ የዘጋችሁ ጆሮአችሁን እንደዘጋችሁ ይቆጠራል መስማት የማይችል ደንቆሮ ነውና ተከፈቱ እንላለን!!

  መልካም ሰንበት በቸር ይግጠመን!

 3. quicha says:

  አቤ ትፈራለህ እንዴ?! አይዞህ ምናምን ስላላችሁኝ አመሰግናለሁ ስትል እኮ… ይቅርታ ያለሰፈሯ የመታች ዉሻ እንዳታደርገኝ

 4. quicha says:

  በናትህ አቤ አስጎብኚ ድርጅት ካለህ የኔንም ብሎግ አስግብኝልኝ?! አንተ ሰው ጠፋ እኮ! 120 ሺ!! ሆኦኦኦ…

 5. Taddy Wedi says:

  it is funny.aba እግዜር ያክብርልኝ! (አቤ ቶኪቻው)anetenem.

  • ጦቢያ says:

   በሳል ወግ ወድጀዋለሁ :: በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ወግ ማግኘት መታደል ነው ::በርታ ወንድማችን ::

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s