ሰላም ወዳጄ ትላንት ሳንገናኝ ዋልን አይደል!? (ትንሽ ቀጠን ያለች ጉዳይ አጋጥማኝ ነበር!)
በቀድሞ ግዜ ሸማቂ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሰሞኑን “ሲሸማቀቁ” ያየን በርካታ ወዳጆቻቸው አብረናቸው ተሸማቀቅንና ሌላ ጨዋታ መጫወትም አልቻልንም እኮ!
ቀጥሎ ያሉት “ገረመኞች” “ገጠመኞች ካሉህ…” እንዲል ጋዜጠኛ፤ ሰሞኑን ያጋጠሙኝ ናቸው። ነገሩ እንኳ እኔን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ነው ያጋጠሙት። ሁሉም በጉዳዩ ላይ ሀሳቡን ሰንዝሮም ይሆናል። ታድያ እኔስ ለምን ይቅርብኝ…
ገረመኝ 1
በአባይ ወንዝ ላይ “አደገኛ” የሆነ ግድብ እየተሰራ እንደሆነ ይታወቃል። “አደገኛ” የተባለው አንድም ገንዘቡን ለመጠቆም ሌላም ደግሞ ያለ በቂ ጥናት በድንገት መጀመሩን ሶሰተኛም ደግሞ ከተሳካልን አለ የሚባል ግድብ እንደሚሆን ለመግለፅ ነው።
ታድያ በቅርቡ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና ስሰማ ግድቡ በሱዳን እና በግብፅ ላይ “አንዳችም” ጉዳት የማያስከትል መሆኑን” የሚያረጋግጠው አለማቀፍ ኮሚቴ የግድቡን ግንባታ ስራ ጎበኘ” የሚል ሰማሁ። እናም ሰጨነቅ እና ስገረም አደርኩ። ምን ጨነቀህ አይሉኝም…? እኔ የምለው የሰይጣን ጆሮ አይስማና ይሄ ገምጋሚ ቡድን ከግምገማው በኋላ “ግድቡ ሱዳን እና ግብፅ ላይ የሚያመጣው አንዳች ጉዳት አለ!” የሚል ድምዳሜ ላይ ቢደርስ ምንድነው የሚደረገው? (በቅንፍ እሱማ ግልግል የተዋጣው ገንዘብ ወደ ድርጅታችን ካዝና ገብቶ እንግዲህ ምን እናድርግ ችግር ያስከትላል አሉን ልንባል እንችላለን ሲሉ አንዳንድ አሽሟጣጮች እንደሚናገሩ እንጠረጥራለን።)
የምር ግን ወዳጄ ይሄ ነገር እኮ በጣም አሳሳቢ ነው ባለፈው ግዜ “ባድመ እርግጠኛ ነን የኛ ነች” ተብለን ደሞዝ፣ ገብስ እና ነብስ አዋጥተን ሻቢያ በአካባቢው ዝር እንዳይል ከገደብነው በኋላ በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ሲጣራ የተዋደቅንላት ባድመ የኤርትራ ነች ተባለ። እናስ ከደምወዛችን የተቆረጠውንም ሆነ የጠፋውን ነብሳችንን የመለሰልን አካል አለ? የለም።
ህዳሴው ግድብ በሱዳን እና ግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያስከትል የሚያረጋግጠው አለማቀፍ የባለሞያዎች ቡድን…. አይበለውና “ግድቡ በግብፅ እና ሱዳን ላይ አሉታዊ ችግር የሚያስከትል ነው” ቢለን ምን ይደረጋል? ይሄንን ተረት በቅርቡ ተርተነዋል ልበል? ካልተረትነውም ከተረትነውም እነሆ፤ “አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን ባሰብሽ”
ገረመኝ 2
መቼለታ፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያልክ ፅ/ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃና መምሪያ ለማህበረ ቅዱሳን የላከውን አንድ ደብዳቤ አይቼ ነበር።
ደብዳቤው “ማህበረ ቅዱሳን የሚያሳትማቸው ታዋቂ ጋዜጣ እና መፅሄት (ስምዓ ፅድቅ እና ሐመር) በዋልድባ ገዳም ላይ የሚሰራውን የስኳር ፋብሪካ አስመልክቶ ምንም ዘገባ አለማውጣታቸውን የሚኮንን ነው። “ስንቱ የመንግስት እና የግል ሚዲያ ወሬውን ተሻምቶ ሲያወጣ የቤተክርስቲያኒቱ ልሳን የሆኑት ጋዜጣና መፅሄት ግን ምንም ዘገባ ያላወጡበት ምክንያት በደብዳቤ እንድታሳውቁን” ይላል ደብዳቤው።
ይበል። እንግዲህ ቤተሰብ ለቤተሰብ ይሄ ለምን እንዲህ ሆነ? ይሄ ለምን እንዲህ አልሆነም? ብሎ መወቃቀስ የቆየ ባህላችን ነው። ነገር ግን በደብዳቤው ላይ ግልባጭ የተፃፈለቻውን ድርጅቶች ስናይ ድንግጥ ያደርጋል። ለብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ ይላል።
እንደ አለመታደል ሆኖ እኛ ሀገር ፖሊስ እና ደህንነት መስሪያ ቤታችንን የምንመካበት ሳይሆን የምንሸማቀቅባቸው ተቋማት ናቸው። ለአንድ አሜሪካዊ የፖሊስ እና የሲአይኤ ተቋማት ትምክቱ ናቸው። እኛ ደግሞ ስጋታችን ናቸው። ከልጅነታችንም ጀምሮ “ጆሮ ቆራጭ እና ፖሊስ መጣልህ” የምንባለው ለማስፈራራት እንጂ አይዞህ ለማለት አልነበረም።
ዛሬም የፓትሪያልኩ ፅ/ቤት ይህንን ደብዳቤ ለራሱ ሰዎች ሲፅፍ ለፖሊስ እና ለደህንነት መስሪያ ቤት ግልባጭ ያደረገው፤ ያው “እምቢ ካላችሁ ጆሮ ቆራጭ እንዳልጠራላችሁ!” ብሎ ለማስፈራራት እንደሆነ ግልፅ ነው።
የምር ግን የቤተስኪያኒቷ ሰዎች ምን ነካቸው? ድሮ ድሮ “የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ” ብለው እንዳላስተማሩን አሁን እራሳቸው በደህንነት እና ፌደራል ፖሊስ መመካታቸው ከእግዜሩ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት አቋርጠው ነው ማለት ይሆን!? ልቦና ይስጥልና!
ገረመኝ 3
ባለፈው አርብ በአንዋር መስጊድ የተደረገውን ሰላማዊ ተቃውሞ አያችሁልኝ!? በዝምታ አፍን አሽጎ እና እጅ ለእጅ ተያይዞ ተቃውሞን ያለ አንዳች ሁከት ማሳየት። ይሄ አያስደንቅም ትላላችሁ!? በእውነት የኢህአዴግ ወዳጆች ግን እኔን ጨምሮ በጣም ጨካኞች ነን! ይሄ አሁን ምኑ ነው ከአልቃይዳ ጋር የሚመሳሰለው!? እንዲህ አይነቱ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ ባይሆን ከማህተመ ጋንዲ የትግል ስልት ጋር ነው የሚመሳሰለው። ይህንን ለማረጋገጠ የማህተመ ጋንዲን ፊልም ማየት በቂ ነው።
ሙስሊም ወንድሞቻችን በየግዜው እያሳዩ ያሉት ጨዋነት የተሞላበት ፍፁም ሰላማዊ እና ተለዋዋጭ የተቃውሞ ስልት የምርም አስገራሚ ነው። ባለፈው ግዜ አንድ ሰው ይሄ ለሁሉም ሰው ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው። ብሎ ሲናገር ሰምቼዋለሁ። ልክ ብሏል። ያለ ድምፅ ጩህትን ማሰማት እንደምን ያለው ጥበብ ነው? አላህ የሀሳባችሁ ይሙላላችሁ! ብሎ መመረቅ ይገባል።
በመጨረሻም
የአበበ ገላው እና የአቶ መለስ ነገር መነጋገሪያነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። እርሱን አስመልከቶ በፌስ ቡክ ከተለጠፉት ያስገረመኝ ታድያ “አበበ ገላው መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር” ብሎ ሲናገር አቶ መለስ ደግሞ “70%” ይሉ ነበር እርስዎስ ምን ይላሉ?” ብሎ አንዱ ወዳጃችን የጠየቅው ጥያቄ ነው። ታድያ ሌላ መላሽ ምን ብሎ መለሰ መሰልዎ “99.6 % ዲክታተር (ሎል)” ብሎ መለሰ። እኛም (ሎል) ብለናል። ሳቅ በሳቅ ማለት ነው!
hi abe. it is a great article again. i really appreciate your works. I would like you to make a correction ….it is “abebe gelaw” not “abebe belew”.
i am always your fan.
from Germany
THANKS FOR SHARING US.!
I appreciate your articles. It’s good keep it up. Aye Abe min meseleh sewochu bete kihnet ras lay yetekemetut joro liyaskortu sayhon likortu asibew new.
Good explanation Abe!!
THANKS ABE
ወዳጄ አቤ …..ቀንህ ይባረክ አቦ !!!
ethiopia wi jagna!!
ስላነበብኩህ ደስ አለኝ!!!!!!!!!
THANKS aby endy new enjy
መጣጥፎችህ ሁሌም ኦሪጅናል ናቸው!! ከዓይን፣ ከሽቦ፣ ከኤሌክትሪክ፣ ከፖሊስ፣ ከመቀስ፣ ከአደገኛ ክስ ይሰውርህ። አሚን!!
አልሓምዱሊላህ ኑርልን አቦ!!
really you Muslim i appreciate your stand
አዬ አለመታደል አይን ያወጣ ውሸት በetv