በመጀመሪያም፤

ብስጭቴ

እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)

ዋናው ወሬ፤

የሆነው ሆኖ ትላንት በዋሽንግተኑ ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመጡ ከውጪ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ በመከራ አልፈው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተሰብሳቢው ፊት፤ ከውጪ ያለው ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ እንዲሁም አዲሳባ ያለው ህዝብ ደግሞ በሰላማዊ ዝምታ በሆዱ ምን እያላቸው እንደሆነ ነጥብ ነጥቡን ነግሯቸዋል። እንደው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ “እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ድረስ ነግሯቸዋል!” ብል የበለጠ ይገልፀዋል መሰል!

የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድርጊት ከዚህ በፊት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረው ጋዜጠኛ ጋር የሚቀራረብ ይመስላል። እንደውም በቪዲዮ እንዳየኋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የደረሰው የቅስም ስብራት “በጫማ መመታት በስንት ጣዕሙ!” ያሰኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስፍራው የተገኙት በባራክ ኦባማ ጋባዥነት ከቡድን ስምንት ሀገሮች ጋር ስብሰባ ሊቀመጡ እንደሆነ ባለፈው ግዜ አውርተናል፤ ከቡድን ስምንቱ ስብሰባ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ታድያ  “ግሎባል አግሪካልቸር ኤንድ ፉድ ሴኪዩሪቲ” በተባለው ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው እንደተለመደው ፐርሰንታቸውን እየጠቀሱ ሳለ ድንገት አበበ ገላው፤ “መለስ ዜናዊ…” ብሎ ሲጠራ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን “የደነገጡት መደንገጥ… ከአንድ ታጋይ የሚጠበቅ አይደለም” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ። እኔም እንዳየሁት ጆሯቸውን ማመን አቅቷቸው “የድርጅቴን ብቅል እየፈጨሁ ነው…” ብለው ሊያልፉት የከጀሉ ሁሉ መስሎኝ ነበር።

ብቻ በጣም ክው ማለታቸውን ፊታቸው አሳበቀባቸው። ከዛ እንደምንም ተረጋግተው…“ሰበንቲ….ፐርሰንት” ብለው ንግግራቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድምፅ ከመጀመሪያው ከፍ ብሎ “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር…” ማለቱን ቀጠለ አሁን ትንፋሽም ቃልም አጠራቸው። አስተያየታቸው “ምነው ዛሬ እግሬን በሰበረው!?” የሚሉ ይመስላሉ። ግን እንደምንም ብለው ለመቀጠል ሞከሩ። ድምፃቸውን ከአበበ ድምፅ ከፍ ለማድረግ እየጣሩ “ሰበንቲ…ፐርሰንት” አልቻሉም። “ምን ላይ ነበር ያቆምኩት…?” ለማለት የፈለጉ ይመስላሉ ባልንጀሮቻቸውን ቃኘት ቃኘት አደረጉ። እነርሱቴ “ራስህ ተወጣው!” ሳይሏቸው አይቀሩም… አበበ ቀጥሏል። “መለስ ዜናዊ ኢዝ ኤ ዲክታተር….” አሁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኛ በላይ ድምፅ ላሳር በሚመስል መልኩ ከአበበ በላይ ጮክ ብለው እና ድፍረታቸውን አሰባስበው፤ “ሰበንቲ ፐርሰንት ኦፍ ዘ ፖፕሌሽን ኢን አፍሪካ….” አሉ። ብሽሽቅ ነው የሚመስለው እንጂ የንግግራቸው አካል አይመስልም!

ድጋሚ አቋረጡ አበበ ግን የሚያቋርጥ አይመስልም በእንግሊዝ አፍ “እስክንድር ነጋ እና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ምግብ ያለ ነፃነት ዋጋ የለውም! መለስ ዜናዊ አምባ ገነን ነው!” ብሎ እንቅጩን ነገራቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁና ቁና ሲተነፍሱ ኮምፒውተሬን አልፎ ሁሉ ይሰማ ነበር። በሆዴ “ይበልዎት አይሂዱ አላልኮትም ነበር!?” ብልም እውነቱን ለመናገር ግን አንጀቴን በልተውታል።

አቶ መለስ ከትላንትናው የበለጠ  ቅዳሜ ደግሞ ሌላ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸው ጭምጭምታ ሰምቻለሁ። ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የሚገኘው ካምፕ ዴቪድ ድረስ ህዝቡን ለማመላለስ የተሰናዱ አውቶቡሶች መኖራቸውን የደረሰኝ ጭምጭምታ ያስረዳል።

እኔማ የሚሰማኝ አጣሁ እንጂ ቀድሞውኑም ይሄ ስብሰባ ይቅርብዎ ብዬ ነበር። ይሄን ግዜ እርሳቸውም በሆዳቸው “ምነው ምነው ምነው በቀረብኝ” የሚለውን ሙዚቃ ሊያዜሙ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ። ምንም ጠቅላይሚኒስትር ቢሆኑ ሰው አይደሉ እንዴ…!? ምክሬን ባለመስማታቸው መፀፀት ካልቻሉ እውነትም ሰውየው ጠቅላይ ሚኒስትር እንጂ ሰው አይደሉም ማለት ነው!

ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቅስም ስብራት የሰማ አንድ ወዳጄ “ይሄኔ ጥሩ አዝማሪ ቢገኝ ይቺን ግጥም በል እስቲ ተቀበል ብሎ ማቀበል ነበር” ብሎኛል…

“አፄ መለስ ዜና እጅግ ተዋረዱ

ምግብ ብለው መጥተው አንጀት በልተው ሄዱ

አንተ አበበ ገላው እንደምን ቻልካቸው

መለስ ቀለስ ሲሉ ጎንበስ አረካቸው”

(አረ ጎበዝ ዜማ ፈልጉና ይችን ነገር ነጠላ ዜማ አደርገን እንልቀቃት በስንት ግዜ የተገኘ የግጥም አዚምን እንጠቀምበት እንጂ!)

በነገራችን ላይ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ አቶ መለስ አዲሳባ ሲገቡ ወይ በጭፈራ ሞቅ ደመቅ አድርገን ካልተቀበልናቸው ወይ ደግሞ ለጥ ብለን ተኝተን ካልጠበቅናቸው በብስጭት ሊጨርሱን ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም

ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

39 responses »

 1. Fibus says:

  Great article, very funny!!!

 2. …ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)

  እኒያ ፓርላማ ላይ(ይቅርታ የመለስ ሾው)ላይ የሚወናጨፉት እጆቻቸው ተሰብስበው
  ክምትር ብለው ላያቸው አባቱ የተቆጣው ብላቴና ይመስላሉ።ኢቲቪ ምን ብሎ ይዘግብ ይሆን?
  ይብላኝለመሰለና ሄርሜላ ጉባዔው ከታቀደለት በላይ ስኬታማ ሆኖ ተጠናቀቀ ይሉናል !
  መቼም እንደፈረደብን ጋዜጠኛ አበበ ገላውና ኢራቃዊው ሙንታደር አል፡ዘይዲ(Muntadar al-Zeidi)
  አስታወሰኝ ብራቮ አበበ ገላው! ምናለበት መቅረፀ ድምፅህን አሊያም እንደሙንታደር በጫማዎ ፊቱን በመታኸው ኖሮ!

 3. samsson Dechassa says:

  ካካካካ፡ ቱባውን ባንዳ አንዱ አበበ ቀን ሲያሸማቅቀቅ መዋሉ ሳያንስ ሌላው አበበ ደግሞ ማታውን ሲያሳልቅበት አመሸ ዛሬ ፡ ወይ መዓልቲ አሉ አቦይ እገሌ !! የእኛ አቤወች በርቱልን፡ ሁሌም ከጎናችሁነን።

 4. adugenet says:

  abe guade betam nice one

 5. SAMI says:

  Nice Article as usual. I am proud of u abebe.!!!

 6. Basie says:

  I like your blog all the time, it is so interesting

 7. Annonim says:

  arife new abe

 8. Danny says:

  Alehu Alehu malet, …

 9. jambo says:

  abbe hoden aqoselkew…

 10. Etsegenet says:

  አቢ አንትማ አስቀድመህ ነግረህው ነበር የፈራህለት ደረሰ አደል ?

 11. yesu says:

  super!

 12. Andy says:

  Absha,

  You are a genius. Keep up your great work.

 13. Abu Imran says:

  Abe,

  This one is amazing!!!

 14. Sweet says:

  Oopes

 15. kidus says:

  ኦባማ ግን አራዳ መሆናቸው ነው ሰውየውን ጠርተው ልክ ልካቸውን የሚያስነግሯቸው!? የምር ሽምቅቅ አደረጓቸውኮ! (እኔ ልሸማቀቅ… ልላቸው ነበር አሁንማ አንዴ ጀምረውታል… ይወጡት እንግዲህ!)
  Abe best man …..long live for you

 16. marie says:

  abebe gelaw,the hero the year!!! great point has been made.

 17. ahmed says:

  abe ine personaly altelahim ethiopiawy neh inem indante huletachinim sile hagherachin yemenagherim hone yemewded yemetilat mebit alen inam and negher lilih wededikugh ,ante ghin sirah mindin new ?melesin ye metilat mebit aleh ghin inde agher mery litaderighilet yemighebawin akbrotim latresa yighebahal .ante america iyenorick were silawerah min yemitlewit yimesilihal ?inante america yetekemetachihu tekhamay bayoch kurt sigha iyebelachu teshikerkary weneber lay iyetekemetachu bewer 100 dollar silemittlulet agher ina beteseb mawrat zim bilo ye ghan mebrat mehon yimesileghal .and negher linigherih ante bewere melesin lematifat yemitasibewn yahil ke meles ghar ikul lememot yeminifeligh millionoch menorachini atresa atiterater tilacha tilachan yiwelidal inghy lewt ayametam !!!

  • Tikure sew says:

   To Amed, As you said u don’t have any personal problem with Abe, I am sure Abe also don’t have any personal problem with any one but our wrong politics. we all love our country. ppl who live in America and other country even if they send $100 still they are helping their family so u shouldn’t have to mention it as a reason to criticize diaspora and support Ato Melse. it is not a good compare and contrast try something else, O ya…most of diaspora they didn’t sit in a good chair as u wish for them..just saying…on top of this our political philosophy couldn’t be the same accept it Abe N other ” 2million” ppl need a better Ethiopia and asking for freedom, equality, human right, fairness, respect and dignity this is our main needs…if u r not okay with that good luck with what ever kind of life u have…

 18. Tezebet says:

  To ahmed:

  I see your full of BS, at least Abe did not kill any one, Abe did not sold his land, Abe did not put a thousand innocent people in prison, Abe did not chase-out Ethiopian journalists from the country they love, Abe did not make Ethiopian people miserable… Ethiopian today can’t say what they want to say or write about their own country, they country they love.
  Abe did one thing he tell us the life of our people and expose the hierocracy of Melese and his clone such as you. You said there are a million ready to die with him? My friend when the days come people like you run as fast as cheetah… have see Libya, have you see Iraq. Good luck but can’t wait to see the day that Melese will face justice and can’t wait to see the million people who want to die with him

 19. Ethiopiawi says:

  Ahmed= Dog= A tamed animal that barks where it gets its daily subsitance.

  You are a puppy hatched at Dengay mamrecha. You stupid highscool dropout who can’t think oneself outof and has not have any hope without this corrupt system and its tyranical dictator, you tried to look smart and fool others. You boasted as millions, where else you are millions???????…trash lairs. A lair group based on a lie propaganda.
  Just lying, lying..

 20. meretwork says:

  ABE! ABE! !!!!! you are our hero!!!!!!! you are the most of Great lij!! ya ETHIOPIAWY neh you did Marvelous History for our Voicles people!!and I am proud of you all Ethiopia
  proud of you !!!gen Abe! I respect you but Abe!! betm tetenqaq!!! buchloch endaybeluoh!!! Ant a Voice for the oppressed AMHARA Ethiopia neh!!you are best for our Mother land !!!!
  EGZABER YETEBKEHE!!!!!!!

 21. ME says:

  Abebe you make my day you are amazing i am proud of you man.From now on please watch your back their is a lot of stupid people out their hunting a good people like you !!!!!!

 22. ME says:

  To ahmed
  ante yematereba aheya keza kagerehe hezebe eyalekes ante tedesakuralahe desekuram enga yemenefalegaw ende abebe ayenat sawe nawe ende ante ayenatu ema agerachen eyasalefe nawe yamesate la sudan le eretera le east indian lemehonu televsion tayalahe seria,lybia yehonawen ayetehal ande kane egezabar bale geza yehe melese yametelaw gemash ereterawie ethiopian erakutewan asekerat endate ayenatun bemeyaz ,afar dame yasebelahe getaye yematereba ena banete afareku hodam behodu adare.

 23. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

  አቤ እየሰማ የገባን እያየ ቅበረው የሚባለውን ተረት አልሰማህም ? በቃ ነገሩ እንደዛ ነው ፡ ሰውየው እየተነገረው አይደል የሄደው ? ታዲያ የምን ማዘን ነው ይበለው ፡፡

 24. Amte says:

  entofento alech enate…ende ante ayinet ye Buna atachi woregna new ye selechen…Mendere neger neh..esty Beweketu Seyoumn sima…enkef…ante ke melesim ke qey shibertegnaw mengistum atishalim..ebet

  • MYESAW KASA says:

   አመት ነው ማነው ስምህ….? እንከፍ አንተ ነህ! አቤ ሆነ በውቀየ፡የየራሳቸው መለያ እና ወዳጅ አድናቂ አላቸው። የአቤ ወሬ ካልተመቸህ እዚህ ምን ልታደርግ መጣህ!? ቂቂቂ….. ወሬኛ ነገር ነህ!

  • Ashkero says:

   Amet?? Ante yihe neger ligebah ayichilim silezih tegebi bota ayidelem yemetahew yihe tilalik sewoch hasabachewin yemigeltsubet bota new..

 25. Wegen says:

  “Ye weyanew Selato
  Mehal Adarash Tegento
  Tenesa belut Minew
  yih hulu alemafer new“

 26. eva says:

  Abebe Melesen belaw ……!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
  Besowenema sinit amet bela

 27. eva says:

  Abebe Melesen belaw !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
  Besowenema sinit amet bela…………..

 28. Tuztuzu says:

  “አፄ መለስ ዜና እጅግ ተዋረዱ

  ምግብ ብለው መጥተው አንጀት በልተው ሄዱ

  አንተ አበበ ገላው እንደምን ቻልካቸው

  መለስ ቀለስ ሲሉ ጎንበስ አረካቸው”

 29. Tadiwos says:

  አምባገነኑ መለስ ለንቦጩን ጣለ !!!! አበበ ተባረክ !!!!

 30. በለው! says:

  “አንዳንድ ጋጠ ወጥ ጋዜጠኞች በኩራት ቀና ብለው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲናገሩ የሰው ምክር የማይሰሙት የአብዮታዊ ዴሚከራሲ መሪ አይናቸው አይቶ አላመነም በጆሮአቸው ገበቶ አንገታቸውን አሰደፋቸው።

  “አባይን መድፈር ይቻላል ኢትዮጵን ማንቋሸሽ ኢትዮጵያዊያንን መዳፈር አደጋ አለው።” !!!!!!!!!
  “የሚሰማን ቢኖር እኛ ስንናገር
  በአጭር አማርንእኛ ዘንድሮ አለ ነገር!”

  ይህ የመናገርና ሀሳብን የመግለጽ መብት እነደእረስዎ እና ደጋፊዎችዎ ፍሽካታ ሳይሆን ቦታ እና ጊዜ አለው።
  ለማስታወሻ ይሆንዎ ዘንድ…

  *በኤች አር ፳፻፯(2007) ወረራ ጊዜ አንድ የራስዎ እንደራሴ ለቱልቱላ የጥቅም ደጋፊዎችዎ፡ ካድሬዎችዎ፡ ደደብ ምሁራኖችዎ እነዲህ ብሎ ነበር” አሜሪካ ውስጥ ከማናቸውም ሀገር የመንግስት እንደራሴ እኩል አንዳንዴም በበለጠ መልኩ በአሜሪካ ግብር ከፋዩ ዜጋ የሀገሩ ሙሉ ዲፕሎማት(አምባሳደር) ተደርጎ ይቆጠራል።”ይህ ትርጉም ያልገባቸው ደጋፊዎችዎ ግን ወይኔ እኔ በነበርኩ…እንገልሃለን ሲሉ ተደምጠዋል።ለሌላው ጊዜ ይህ ቃል በምስክር(ማስርጃ) ከተረጋገጠ እዚያው እሰኪጣራ እርስዎም አብረው እንደሚቆዩ ያውቃሉን ? ?

  **ሌላው ያ ከታታላቅ ሀገሮች እንዳለ የኮረጁት ሕግ የአሸባሪው “በአሸባሪነት ከተፈረጀ ቡድን ወይም ግለሰብ አብሮ የተሰበሰበ ሻይ ቡና ያለ…ይቀጣል ታዲያ አበበ ገላው የኢሳት አባል የሆነ ኢሳት የግንቦት ሰባት ከሆነ እርስዎ አብረው ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከነበሩ ሌሎቹንም ጨምሮ በአሸባሪነት ወንጀለኛ እንደሆናችሁ ለፍርድ እንደምትቀርቡ ያውቃሉን ? ?

  *** በቅንድብ ፍቅረኛዎ (ከዳልኝ) ያለ ማቋረጥ ለአራት ሰዓት ወጧ ኢንዳማረላት …ሲሞናደል ዋለ! አልሰሜ ? ?
  “መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ኩራት ዲያስፖራው ለልማት… የህዳሴው ግድብ በዲያስፖራው ይገነባል” ሲል ዋለና …

  ዲያስፖራውን እንዲህ ይላል” በቁጥር ሃምሳ የሚሆኑ
  (፩)የሻቢያ ቅጥረኞች የኦነግ እና ኦብነግ አባሎች (፪)ጥገኝነት በመጠየቅ ላይ ያሉ በጠበቆቻቸው ተገፍተው የተላኩ
  (፫) ቤት የሌላቸው፤ ምግብ በመንግስት የሚቸሩ፣ቦዘኔ፤ወሮበሎች፤ዱርዬዎች ናቸው። በቅርብ ጊዜ ይጠፋሉ ይላል ” ይህንን ያሉት አቶ መልስ በሗላም ‘ሀገር ፍቅር’ የሚባል ሬዲዮ ዶ/ር በላይ ሀ/እየሱስ እና ንጉሴ ወልደማርያም ከዋሽንግተን ዲሲ እነ ጋዜጠኛ ፀሐዬ፣ብርሃኑ አባ መላ የመሳሰሉ አውርቶ በሎች የሚሞላፈጡበት መሆኑ ነው።

  **** የአቶ መልስ ደጋፊዎች እንዴት ደጋፊ ጋዜጠኛ በአዳራሹ እንዳልነበር ተገርመዋል ማን ሰው አለሽ እና አሉ…
  ለመሆኑ ቢኖር ምን ሊያደርግ ይችላል? አብሮ ቅሌትን ከመከናነብ በቀር! ሰውዬው 70 ከመቶ ብለው ሳይጨርሱ አቶ አበበ ገላው 21-27 ሴኮንድ ውስጥ “ፉድ ሴኩሪቲ” ሳይሆን “ሊበረቲ” ቀጥ ብሎ የድምፅ ማጉሊያውን በጥሶ በወጣ መልዕክት ቢወረድበት እሳቸው 45 ዲግሪ ወደታች ተደፉ። ግሎባል አግሪካልቸር ወይስ ግሎባል መኮማተር ??
  *****************************
  ብልግናዎን ደብቀው ለልመና ቢቀመጡ
  ተቅለሠለሱም ያልሞት ባይ ተቁነጠነጡ
  መቃምዎን ኢንጃ ይመስላሉ የጠጡ
  እዚያም ቤት እሳት አለ አላመለጡ
  ድንገት ቀልብዎን ገፈፈው
  ሁሌም የማይረሱት መልከኛው
  የልቡን ተናግሯል እረካ አበበ ገላው ።
  ******************************
  በሌላ ጊዜ የበለጠው ይግጠመን !

 31. አቤ እናመሰግናለን:: በተለይ ግጥሟን ወድጃት ስዘልቃት እውላለሁ:: ለወደፊቱ ትውልድ ሽሙጥነቷ ተረስቶ ከርዕስ ውጪ ተተርጉማ አንጀታችንን በልተው ያሳዘኑን እንዳትመስል በሚል ሳትሽሟጠጥ ስለ ታሪክ ብዬ እንዲህ ብያታለሁ፦

  አፄ ፈላጭ ቆራጭ ዲሲ ተዋረዱ፣
  ብር ብለው መጥተው ጨው ተነፍተው ሄዲ፣
  ባስሰደዲት አሕዛብ በአበበ ገላቸው፣
  መለስ ቀለስ ሲሉ ጊንበስ አረጋቸው:: እንደምታፀድቃት ተስፋ አለኝ:: በርታልን::

 32. ዮሴፍ says:

  ለአህያ ማር አይጥማትም ምንትስ የሚባል ተረት አለ ልበል መርሳት ጀምርያሎ መሰለኝ ከሌለም እርማት በሉኝ ለማንኛውም የሰው ልጅ ሀ ብሎ ትምርት ቤት ስሄድ አስተማሪ የመጀመረያ ትምህርቱ ማስተማር ሲጀምር ” የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት” ብሎ ይጀምርና ”ምግብ መጠልያ ልብስ” ብሎ ያስተምራል አሁን እነዚህ 3 መሰረታዊ ነገሮች ” በነጻነት ድሞክራሲ ፍትህ”ተተክተዋል መሰለኝ አበበ በለው (ይቅርታ ”ገላው” ልል ነው ለነገሩ እሱም የሱ ቢጤ ነው)ምግብ አንፈልግም ነጻነት ብቻ ስጠን ስል እንደ ውሻ ስጮህ ሰማሁት በነገራችን ላይ እሱና ታማኝ በየነ የውሻ ዘር አላቸው ልበል(ልብ በሉ የአህያ አላልኩም)ግድ የላቹሁም ዘር እንኳን ባይኖራቸው እርግጠኛ ነኝ ደማቸው በ DNA ቢመረመር የውሻ cell ይኖራቸዋል እንደው ግን አቤ መች ይሆን እንደ ወንድ እጃችሁን የምትሰነዘሩት ውይይይይይይይ ምላስ ጭሆት ምላስ አሁንም ጭሆት 21 አመት ሙሉ ምላስ አሁን እናንተም የኛ ……ተውኩት መጥፎ ልታናግሩኝ ነው

 33. saba says:

  to Ahmed
  sidb atahulih sidboch hulu yansubhal hodam asama neh sew aydelehim!

 34. saba says:

  to yosef
  wishas ante kimalam ye weyane kit lash.

 35. Eden says:

  Now it is time to do our best!

 36. this is the big history for ETHIOPIA no one repet this history because abeb already he did, thanks abeb!!! he is one of our hero!!! beka kengdy yemenamenew sew agegnen moralachen wedko neber ahun esat sew tefter bezu esatochen yefeteralu kahun wedeya!! thanks abeb!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s