ዛሬ ግንቦት ሰባትን አስመልክቶ አንዳንድ የተለቃቀሙ ጨዋታዎችን ለማቅረብ ዕቅድ ነበረኝ ነገር ግን በ”ሙድ” እጦት ጨዋታው ሳያልቅልኝ ቀኑ አለቀብኝ። ስለዚህ ለዛሬ ቢያንስ እንኳን አደረሳችሁ እንባባል። እና ለነገ በሀገርቤቱም በዲያስፖራውም ብሎጋችን “ሙድ ያፈራውን” የግንቦት ሰባት ወሬ እንቃመሳለን። (ማስታወቂያ መሆኑ ነው እንግዲህ) ኢቲቪም “በነገው ዕለት” አያለ የፕሮግራም ማስታወቂያ ይሰራ የለ እንዴ…? ማን ከማን ያንሳል!
በነገራችን ላይ ለኢትዮጵያ ብለን የከፈትነው 15ኛው ብሎጋችን እስከ አሁን ባለመዘጋቱ የተሰማኝን መደነቅ ሳልገልፅ አላልፍም። አሁንም በነገራችን ላይ ዋናው ብሎጋችን እስከ አሁን ደረስ ከመቶ ሺህ ግዜ በላይ የተጎበኘ ሲሆን ሌሎቹ አስራ አራቱ ብሎጋ ብሎጎችም ከ ሃያ ሺህ እስከ አራት ሺህ ግዜ ድረስ ተጎብኝተው “የተሰዉ” ናቸው። “እንደምታነቡኝ ባወቅሁ ግዜ ደስ አለኝ” የሚባለው ይሄኔ ነው! የነገ ሰው ይበለን!