ሰሞኑን ሰለሞን ተካ “ፅናት” በተባለ የሬድዮ ጣቢያው ላይ ጮክ ብሎ ሙስሊም ወንድሞቻችንን በሚመለከት አንድ መግለጫ ሰጥቷል። ሰለሞን የቱ…? ብሎ የጠየቀ ካለ ሰለሞን ዜሮ ዞሮው በሚል አብራራለሁ። መጨመር ካስፈለገም ምን ነካው? የማይባለው ሰለሞን ተካ! ብንለውም ይሆናል።

የሚገርመኝ ነገር 1

ይሄ “ፅናት” የተባለው ራዲዮ ጣቢያ አዘጋጁ ራሱ ሰለሞን ተካ ነው። ስጠረጥር ባለቤቱም እርሱ ይመስለኛል። ታድያ እዚህ ላይ ግርም ያለኝ ነገር፤ ሰለሞን እንዴት ይሄንን ስም ተሸክሞ ቆሞ መሄድ እንደቻለ ነው። በእውነቱ ይሄ ተዓምር ነው። ሰለሞን ተካ ዜሮ ዜሮ፤ ፅናት የሚል ስም በላዩ ላይ ተጭኖት በአደባባይ ሲንከላወስ ማየት አይጥ አንበሳ አዝላ ስትዞር ከማየት ጋር እኩል ያስደንቃል።

የሚገርመኝ ነገር 2

እኔ የምለው ሰለሞን ተካ እንዴት ነው ነገሩ አነጋገረህ እኮ እንደ መንግስት ነው። መቼ ነው የነገስከው የኔ ጌታ። አለግባኝም “ጨለፍ” አደረግህ እንዴ? እውነቴን ነው የምለው ከቤተሰብ እና ዘመድ ጋር ተቆራርጠሃል ማለት ነው? እንጂማ በአደባባይ እንደዚህ ስትናገር በቀጥታ የአዕምሮ ህክምና ቦታ ወይም ደግሞ ፀበል… ወይም ዱዓ ለሚያደርግ ቃልቻ ወስዶ መስጠት ይገባ ነበር።

የሚገርመኝ ነገር 3

የኢህአዴግ ሰዎች እንዴት ዝም አሉ? የምሬን ነው። በዚህ አነጋገሩ እና በዚህ ለዛው ስለሞን ተካን ኢህአዴግን የሚወክል ጋዜጠኛ ማድረግ የሚያመለክተው ትልቅ የሆነ የሰው ሃይል ችግር መኖሩን ነው። እውነቴን ነው የምላችሁ ውድ የኢህአዴግ ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች ሆይ ሰለሞን ተካ እንኳንስ በጋዜጠኝነት እና በዘፈኑም ቢሆን ለሚያደርገው “አስተዋፅኦ” ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ባለፈው ግዜ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን “ቅንድቡ ያማረው” ብሎ ዘፍኖላቸው ስንቱ ነው በሌላ የጠረጠራቸው? እሱ የራሱ ጉዳይ እርሳቸው ግን በምን እዳቸው እንዲህ አይነት ጥርጣሬ ውስጥ ይወድቃሉ። ምንም ቢሆን ባለትዳር ናቸውኮ!

እውነቱን ለመናገር ሰለሞን ተካ ለኢህአዴግ በጋዜጠኝነት እሰራለሁ ማለቱን ማንኛውም ለድርጅቱ አሳቢ የሆነ ግለሰብ ሊያስቆመው ይገባል። የምሬን ነው የምለው ድርጅቱ ስንት የሚተችበት ጉዳዮች እያሉት በማንም ሰርጎ ገብ የሚብጠለጠልበት ምክንያት አለ ብዬ አላስብም።

ቀጥሎ ያለው አንቀፅ ለኢህአዴግ ከልብ በመቆርቆር የተሰነዘረ ነው።

እንደኔ እምነት ሰለሞን ተካ በቅፅል ስሙ “ብሪቱ” እልም ካለው የተቃውሞ ጎራ ወደ ኢህአዴግ ደጃፍ መምጣቱ ለኢህአዴግ ጥሩ ነው። ነገር ግን “ደርሶ ከኔ በላይ ኢህአዴግ ላሳር” ማለቱ እና በየአደባባዩ ድርጅቱን የሚወክል ወሬ ማውራቱ ለኢህአዴግም መልካም ገፅታ አይበጅም። አረ በድንብ ስሙት ጎበዝ ሰውየው እኮ እሳት ይቀረዋል። ስለ እውነት እላችኋለሁ አልበሰለም። ታድያ በሳል ሰው ከየት እናምጣ? ካላችሁ ድርጅቱ ራሱ ተሀድሶ ያስፈልገዋል ማለት ነው። አለበለዛ ግን “ሃይ” ባይ ሰው ያስፈልጋል። ልክ ተቃዋሚዎች “መለስ በቃ” እንደሚሉት አይነት የኢህአዴግ ሰዎች ይበልጡኑም ለድርጅቱ አሳቢ የሆኑቱ “ሰለሞን በቃ” ብለው ሊያስቆሙት ይገባል። ከልቤ ነው የምላችሁ። (ከፈለጋችሁ ንግግሬ ላብራቶሪ “ቼክ” ይደረግ)

ለማንኛውም ሰለሞን ተካ ሰሞኑን ራሱን መንግስት አድርጎ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም “መጅሊስ ይውረድ መንግስት በእምነታችን ጣልቃ አይግባ” ሲሉ ፍፁም ሰላማዊ የሆነ ተቃውሞ እያሰሙ ያሉ ሙስሊም ወዳጆቻችንን “የአልቃኢዳ ቅጥረኞች” ብሏቸዋል። ሰለሞን ይህንን ነገር ከየት አመጣው ያልን እንደሆነ ባለፈው ግዜ ጠቅላይ ሚንስትራችን “በአርሲ እና ጅማ አካባቢ የአልቃይዳ ሴል ተገኝቷል” በማለት የተናገሩትን ለመኮረጅ ሞክሮ ነው። ሰሌ በእብደቱ ተዓምር በየ ጁምዓው ተቃውሞ የሚያሰሙ ሙስሊሞችን በሙሉ “የአልቃይዳ ቅጥረኛ” ብሏቸዋል። አላህ ምህረቱን ያውርድልህ እንጂ ይሄ የጤና አይደለም። “ፍሬንዴ” የአልቃይዳ ቅጥረኛ ቢሆኑማ በአንድ ቦንብ “እምጷ” ያደርጉህ ነበር።

በመጨረሻም

አንድ ጥያቄ

እኔ የምልህ ሰለሞን ተካ ባለፈው ግዜ እኮ “ከዚህ ቀጥሎ ቤተሰቤን ይዤ መጥቼ አዲሳባ መኖር እጀምራለሁ” ብለህ የአዲሳባ ህዝብ በጉጉት እየጠበቀህ ነው። እኔ የምልህ ያንግዜ ካዛንቺስ አካባቢ የጎሻሸሙህ ነገር አናትህን ነክቶት ይሆን እንዴ!? ያልከውንም አስረሱህ የምትናገረውንም አቀዣበሩብህ እኮ!

ሌላ ደግሞ ራስህን “አርቲስት” እያልክ ስተጠራ ሰምቼ ለዚህ ጨዋታ የሚሆን ፎቶ ፍለጋ “ጎግል ኢሜጅ” ውስጥ ገባሁልህና “አርቲስት ሰለሞን ተካን” አፋልገኝ ብለው ብሰራው አንዴ አበበ ተካን ሲያመጣልኝ፤ አንዴ ሰለሞን ቦጋለን ሲያመጣልኝ ስሰማ ተሳስቼ ይሆናል ብዬ ደመደምኩ። ይቅርታ ትደግምልኛለህ…  ምን “…ቲስት”  ነኝ ያልከው?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

5 responses »

 1. yiba says:

  “AR” newa yawum weframu !!!

 2. Kulich says:

  Abe
  I don’t know why you write about this moron. I think you are doing him a big favor by writing about him or repeating what he says in his radio show.

 3. በለው! says:

  ለመሆኑ “የፅናት” ትርጉሙ “ወላዋይ” ሆነ እንዴ? ? ባለፈው አንድ ዘፈን ለጽናቱ የቅልቅል መሆኑ ነው ዘፈነ አሉ ….. *****************
  ይቀጥል… ይቀጥል ያው ባለሙያው
  መዋሸት ማሰር መግደል የተካነው
  ከሌባ እጅ ጉርሻ አልጠገብንም እና አሁንም ምረጡት ያብላን እንደገና በጥሩ ቅጥፈቱ በዓለም ተወድሷል ትናንት ብቻ አደለም ነገም ይፈረጃል
  እርምጃው አደጋ ብዙ ውጥን አለው
  ለሆድ አደር ካድሬ ጥሩ መሪአችን ነው
  ምሁርን አጥላልቶ ሰበስቦ ደንቆሮ
  አፈላልጎ አገኘን ግራ ቀኙን ዞሮ ።
  ****
  ውሸት ከአይኑ ሽፋን የፈለቀለት
  ዕውቀቱን መሃይም ያሞካሸለት
  ንግግሩ መራር ጋጠ-ወጥ አንደበት
  ስብዕና የሌለው የሌባ ተምሳሌት
  በጥፋት ጎዳና ጉዞን ያሰጀመረን
  ነገም እንዳትነኩት የሚሰጠን አለን !
  ለራዕይ እና ጉዞው ለዓላማ እና ግቡ
  ባንዳ ጭልጥ ብሎ ገባ እነ ሥግብግቡ
  ሲናግር ይውላል ትምኪት በታጀበ
  ዲሞከራሲ ይላል ጦር እያነገበ
  ጎሳ ብሔር መረጦ ከሀገር አንድነት
  በጭለማ አኖረው መብራትን በማጥፋት
  በልባዊ ዓላማው መበተን ጽናቱ
  እውነትም ብልህ ነው ሆዳም በማብዛቱ
  ይህን ሁሉ አጋሥሥ ቀድሞ በመምራቱ
  ታይቷል በአደባባይ ንብረት ማካበቱ
  ብሩህ ተስፋ ጠፋ ዘመነኛ ብቻ ሲበላ ሲያውካካ
  ያ ‘ድሃ ሕዝብ በተስፋ በድራጎት ሲመካ
  አንዴ ጋግሮ ሳይበላ ሁሌም እንደቦካ
  *****
  ለዘረኞች ለሆዳሞች ስኬት ሰልፉን እየመራ
  ምን መርገምት ይሆን ይህ ሁሉ ቡጠራ
  መለስ ብለን ስናይ አነሳሳችንን
  ገንዘብ እና መሬት ብለን ተማጸንን
  እንኳንም ደግ አረግን ሌባ መምረጣችን
  መንገድ ስላሳየን አባልቶ መብላትን
  ድርሻህን አንነካም ስጠን ፍርፋሪህን
  መላጣው ቅንድቡ ያማረው መሪያችን።
  ********************************
  ደራሲ ተካ ብሪቱ($$$$)

 4. Tinbit says:

  አቤ ውይ እንዲህ ልክ ልኩን ንገርልኝ እንጂ አንጀቴን ነው ቅቤ ያጠጣኽው ይብላኝለት ይሄን የ_ቲስት ጭንቅላቱን ለተሸከመው አገቱ ታሪክ እንደሆነ ራሱን መድገሙ አይቀርም የካዛንቺሱ ጉሸማ በሌሎች ክፍለከተማ መደገሙ አይቀሬ ነው።

 5. Anani zefasiledes says:

  Besinitu enikatel er newu allu yeteweledewu atarut Abo ehen melitie ehadigimko werada bilotal, enen yemikochegn ene kitaw ejigu yeteweledubet bota newu allu yeteweledewu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s