ከዛሬ ስድስት ወር በፊት ወፍራሙ መንግስታችን ተጭኗት “ህልፈተ ህይወት አደረገች” ብለን አዝነን ለቅሶ ተቀምጠንላት የነበረችው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ “እጅ መስጠት የለም ብላ” (ትንሽ እናጋነው ካልድ ደግሞ መቃብሯን ፈንቅላ) በዌብ ሳይት በኩል መምጣቷን ትላት ይፋ አደረገች።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “መንግስታችን እኔ ብቻ ላውራ እናንት ዝም በሉ” በሚል እንድተዘጋ ያደረጋት፤ ተወዳጇ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ዘወትር ቅዳሜ ነግሳ ትውል ነበር። ጋዜጣዋ ከመዘጋቷ ከአመት በፊት ማኔጂንግ ኤዲተሯ ዳዊት ከበደ ሲፒጄ ከተባለው ለጋዜጠኞች የቆመ ድርጅት “እሰይ አበጀህ የኛ ልጅ” ተብሎ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የመጣው ይምጣ ብለው ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚሰጠውን ሽልማት ተበርክቶለት ነበር።

ትላትን በዋሽንግተን ዲሲ (የሆቴሉን ስም ረሳሁት) ብቻ በአንድ ሆቴል በተደረገው የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ በርካታ እንግዶች በመድረኩ ላይ የተገኙ ሲሆን በቪዲዮ እና በስካይፒም የሲፒጂ አፍሪካ አስተባባሪ መሃመድ ኬታ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ እና ሌሎችም ግለሰቦች ስለ አውራምባ ታይምስ ዌብሳት መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልጠዋል። (በቅንፍ አንዳንድ ግለሰቦች የተባልኩት እኔ መሆኔን አሳብቃለሁ!)

አውራምባ ታይምስ በአገርቤት ዘጋቢዎቿ እየታገዘች ስለ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዘገባዎችን ለማቅረብ ቆርጣ የተነሳች መሆኗን ዳዊት ከበደ ነግሮኛል።

አውራምባ ታይምስን ለመጎብኘት ተነሳሽነት ያላችሁ ግለሰቦች እና ድርጅቶች http://www.awrambatimes.com/ ብላችሁ እንደምታገኟት ዜናን በጨዋታችን ሊነግራችሁ ይወዳል!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

One response »

  1. […] ይህችን ጠቅ በማድረግ ያንብቡት:: ስለ ርእዮት ከተጻፉት ደግሞ የአቤ ቶኪቻውን ያዙልኝ አቤ ዜናውም ትንተናውም እንግዲህ በጫወታ መልክ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s