abetokichaw@gmail.com

ውድ የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆቼ እንዴት አላችሁልኝ? “እኔስ አለሁ አለሁ አለሁ እንደምንም እግዜር ያመጣውን ሰው አልችል አይልም” የሚል ዘፈን የሚዘፍንልን ሁነኛ ሞዛቂ አጣን አይደል…? ለማንኛወም አንተ እንዴት ነህ ብለው የጠየቁኝ እንደሆነ እኔው ራሴ አዜማታለሁ!

ይህ ደብዳቤ ለቀዳማዊት አዜብ መስፍን በታላቅ ትህትና እና አክብሮት የተፃፈ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ለቤተመንስግስቱ ቤተሰቦች ያነኝን የላቀ ፍቅር እና አክብሮት እንዲሁም ታማኝነት የሚያሳብቅ በመሆኑ ይህንን ሀሳብ የምትቃወሙ ወዳጆችን ከወዲሁ ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ነው።

ጀመርኩ፤

ክብርት ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንዴት ሰነባበቱልኝ? ባለፈው ግዜ ይድረስዎ አይድረስዎ እንጃ አንድ መልዕክት ሰድጄልዎ ነበር። እርግጥ ነው ደብዳቤዬን በዌብ ሳይቶች ላይ እንዲታተም አደረግሁ እንጂ በአድራሻዎ አላኩልዎም። ታድያ እነዚህ ድረ ገፆች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው በመሆናቸው፤ ምናልባት ለገበያ፣ ወይም ቤተሰብ ጥየቃ፣ ወይም ደግሞ አንዱን ቅዳሜና እሁድ ንፋስ ለመቀበል ዱባይ ወይ ቻይና ወይም እንግሊዝና አሜሪካ ብቅ ካላሉ በስተቀር አራት ኪሎ ቁጭ ብለው በድረ ገፅ የታተመ ደብዳቤዬ ላይደርሶት ይችል ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ።

አሁን አሁንማ ያው እንደሚያውቁት “ኢንሳ” የተባለው ዌብሳይቶችን በመዝጋት የሚተዳደረው ዘጊ መስሪያቤት እንኳንስ የተጠናከሩ ዌብ ሳይቶችን ይቅርና እንደኔ ያለን ምስኪኖች ወግ ይድረሰን እና ወግ እናወጋ ብለን የከፈትናቸውን ሚጢጢ ብሎጎች ሁሉ እየዘጋ ከምንወደውና ከሚወደን መንግስታችንም ሆነ ህዝባችን የማለያየት ስራ እየተሰራብን ይገኛል።

የምሬን ነው የምልዎ ይሄ ክፋት ነው። ለምን ከመንግስታቸው ጋር ተግባቡ… ለምን ደብዳቤ ተላላኩ ለምን ተስማሙ የሚል ምቀኝነት። እኔ በበኩሌ ዘወትር እርስዎን እና ጠቅላይ ሚኒስትሬን ጨምሮ መላው የኢህአዴግ አባላት በስራ የዛለ አዕምሯችሁን ዘና ለማድረግ እንደተጋሁ ነው። (እዝች ጋ ታይፕ አልገደፍኩም አይደል…? እባክዎ ይቺ የታይፕ ግድፈት ከብዙ ሰው አያቀያየመችኝ ነው። በተለይ ስራ እኔ ሴራ እየተመሳሰሉብኝ ስቸገር ባዩኝ…! የኛ ሰው ደግሞ ቶሎ ነው የሚከፋው። …አይ አሁን ግን ልክ ነኝ። ሴራ አላልኩም ስራ ነው ያልኩት።) እናልዎ በስራ የዛለ አዕምሯችሁን ትንሽ ዘና እንዲል የማላደርገው ጥረት የለም።

ታድያ ይገርምዎታል የእኔ ብሎግ እንኳ ሳይቀር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገበ ተከልክልዎሎታል። እኔማ የለም ተሳስተው ነው የእኔ ባይመስላቸው ነው… ብዬ ድጋሚ ስከፍት፤ አሁንም ሲዘጉት፣ አሁንም ስሞክር፤ አሁንም ሲዘጉት ቢያምኑኝም ባያምኑኝም አስራ አንድ ግዜ ተዘግቶብኛል። ከዚህ በላይ ከሄድኩኝ ከሀገሪቱ የእድገት ቁጥር ጋር መፎካከር ነው ብዬ ለግዜው ብሎግ ከፈታውን ተወት አድርጌዋለሁ።

እሜትዬ እኛ ኢቲቪ የፈለገውን ሲያቀርብ “ብሎክ” ማድረጊያ ሪሞቱ አጠገባችን እያለ ይሁን ለኛው ብሎ ነው በሚል ቅን አመለካከት ያሻውን ቢናገር ያሻውን ቢያወራ ዝም ብለን እንሰማለን እንጂ አንዘጋውም። በርግጥ ብዙ ግዜ የቴሌቪዥናችን ፕሮግራሞች እርሾ ይበዛባቸዋል መሰለኝ ሆድ ይነፋሉ። ቢሆንም ግን ተመልክተን ከጨረስን በኋላ ቀንዶ ወይም እናትና ልጅ አረቄ ጠጥተን እንበትነዋለን እንጂ ፕሮግራሙን “ብሎክ” አድርገን ወይም አቋርጠነው አናውቅም።

ውይ ኢቲቪን ሳነሳ ምን ትዝ አለኝ መሰልዎ አንዱ ፀሀፊ በቅርቡ በእናንተ ላይ የፃፈውን አይቼ እንዴት እንዴት ስበሳጭ እንደነበር ቢመለከቱኝ፤ ምን ያህል ተቆርቋሪዎ እና ወዳጅዎ እንደሆንኩ ይረዱልኝ ነበር። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ገበና እና ሰው ለሰው ድራማ መቼም ሳይከታተሉት አይቀሩም…! እናልዎ በዛ ላይ ያሉ እኩይ ገፀ ባህሪ ሆነው፤ ነገር ግን ሁሌ ሲሳካላቸው የሚታዩ ሰዎች አሉ። የሰው ለሰዉ አስናቀ እና የገመናዋ ለምለም። ታድያ ይህ ያበሳጨኝ ክፉ ፀሀፊ አቶ አስናቀን ከአቶ መለስ ጋር ወ/ሮ ለምለምን ደግሞ ከእርስዎ ጋር አመሳስሎ አላየሁትም መሰልዎ…!? በእውነቱ በብስጭት ደሜ ከዋጋ ግሽበቱ በላይ ነው የጨመረው።

ታድያ ከላይ እንዳልክዎ በየ ድረገፁ የምንለጥፈው ፅሁፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ሲከለከል ለእርስዎ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሬም የምልከው መልዕክት ሳይደርስ ይቀራል ብዬ እሰጋለሁ። ወይስ ቤተ መንግስቱ ከኢትዮጵያ ውጪ ነው የሚገኘው…? አንዳንድ አሽሟጣጮች እንደሚሉት ከሆነ አገሪቷ ላይ የሚመጣ ችግር አንድም ግዜ ጎብኝቶት ስለማያውቅ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ለማለት አያስደፍርም ይላሉ።

ለምስሌ “የገበያ ዋጋ መናር ለቤተመንስግስት ሰዎች ምናቸውም አይደለም ምክንያቱም ገበያቸው ዱባይ እና ቻይና ነው” እያለ ሰዉ ያልተጠየቀውን ሲያወራ ቢሰሙት ይደነቃሉ። ይቺ ይቺ እርስዎን ለመንካት ነው። እኔ ግን እከራከርልዎታለሁ። ለራስዎ “በአለም ላይ ደሃ ከሚባሉ መሪዎች መካከል አይደሉ እንዴ?” አረ ይልቁንስ ሰሞኑን የሰማሁትን ሳልነግርዎ… እኚያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ አፍሪካ የሄዱ ግዜልዎ… ወደ አስር ሺህ ዶላር አውጥተው ጌጣጌጥ ሲገዙ ነበር አሉ። ይሄ ነገር ግን ለድርጅታችን ስም ጥሩ ነው ይላሉ? ለአባይ መዋጮ ሰዉን በምናስጨንቅበት በዚህ ግዜ ባለስልጣኖቻችን ይህንን ያህል ወጪ ሲያወጡ መልካም ነው…? በእውነቱ ጥሩ አይመስለኝም። በርግጥ እኔ በበኩሌ  ይሄንን የሰማሁ ግዜ ድሮ ድሮ በእንዲህ ያለው ነገር የሚጠረጠሩት እርስዎ ስለነበሩ ጎሽ ትንሽ ከሳቸው ራስ ላይ ገለል ይላሉ ብዬ ውስጥ ውስጡን ደስ ብሎኝ ነበር።

ምን ዋጋ አለው በነጋታው ሌላ ወሬ መጥቶ የእርስዎን ስምም አደባባይ አገኘሁት። በርግጥ እንደተለመደው ስምዎ ሲነሳ የሰማሁት ከቅንጦት ገበያ ጋር ተያይዞ ባለመሆኑ ተደስቻለሁ ቢሆንም ግን… በአደባባይ ስምዎ ሲነሳ ቅር ይለኛል። ምን መሰልዎ…? ያ ጎረምሳ ልጅዎ፤ ነፍሱን ይማረውና ከቀድሞው የደህንነት ሹም አቶ ክንፈ የሚወለደው… እ! እሱልዎ በየ ጋዜጣውና መፅሔቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ይዝታል አሉ። አረ እንደው ሌላ ሰው አይስማን እንጂ እንደርሱ አባባልማ ለአባቱ ሞት ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው። እኔማ በየድረ ገፁ ላይ ይህንን ባየሁ ግዜ በእውነቱ ይሄ ጉርምስና ነው…! ብዬ ወቀስኩት። በምን አነሳሁት እቴ…

የኔ ነገር አንድ ግዜ ጨዋታ ከጀመርኩ እና እህ… ብለው ከሰሙኝ መቼም ማብቂያም የለኝ፤ ወደ ዋናው ቁም ነገሬ ስመጣ ያንን ነገር እንዴት አደረጉልኝ ወ/ሮ አዜብ? ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲመክሩልን ጠይቄዎት ነበር። ባለፈው ግዜ እንዳልኩዎ በእርስዎ ያምራል። እኛ ያሻንን ያህል ብንለፋ እርስዎ በሚስት ብልሀት የሚመክሩትን ያህል አይሆንልንምና ባለቤትዎን በዘዴ በዘዴ ይምከሩልን! ብዬዎት ነበር።

እውነቴን ነው የምልዎ ወ/ሮዬ እኛ ከአንጀታችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር  የወደቅነውን ያህል ብዙ ሰዎች ደግሞ ከልባቸው እየተቀየሟቸው ነው። ይህንን በስንትና ስንት ስለላ ያገኘሁት መረጃ መሰልዎ…! ባለፈው እንዳልኩዎ የሰዉም ሁናቴ የሳቸውም ምላሽ በዚሁ ከቀጠለ ወደፊት እንኳንስ  ህዝቡ እና የገዛ ጉርሻቸው እሺ ብሎ አልጠቀለል የሚላቸው ግዜ ሊመጣ ይችላልና ከአሁኑ ተመካክረን አንዳች ዘዴ እንዘይድ በሚል ነው ይህንን ደብዳቤ መፃፌ!

ይኸውልዎ ወይዘሮ አዜብ ህዝብ ሲከፋው፤ ህዝብ ሲበሳጭ ምን ሊያደረግ እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትራችንም ጠንቅቀው ያውቁታል። እና ሳስበው ከእርስዎ ብዙ የሚጠበቅብዎ አይመስለኝም። እርሱን ብቻ ያስታውሷቸው እርሳቸው አንድም ስራ ስለሚበዛባቸው አንድም በሌላ ሌላ ምክንያት ሊረሱት ይችላሉ።

ቀዳማዊት እመቤት ሆይ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ መፅሐፈ አስቴር በሚለው ምዕራፍ ውስጥ የአስቴርን ታሪክ አንብበውታል? “ምን ይሄ የቤተመንግስት ጣጣ እኮ ለእንዲህ ያለ መንፈሳዊ ምንባብ ግዜ አይሰጥም” ብለው እንደሚያጉረመርሙ በጠረጠርኩ። አይዞት እኔ እያለሁ ሀሳብ አይግባዎት ትንሽ ቀንጭቤ ከታሪኩ እንደሚከተለው እነግርዎታለሁ፤

በዛን ወቅት አርጤኬስ የሚባል ንጉስ በአስቴር ፍቅር ወደቀና ንግስት አደረጋት። እሷም በዛ እየኖረች ሳለ አሳዳጊዋ መርደኪዮስም ሆነ አጠቃላይ ህዝቧ እና ወገኗ ለታላቅ መከራ ተዳረጉ። ሐማ በተባለ የንጉሱ ሰው (ልክ በአሁኑ ግዜ እኛ ስራ አስፈፃሚ አካላት እንደምንላቸው ሹማምንት መሆኑ ነው) ህዝቡን ክፉኛ ስጋት ላይ ጣለው። እንደ እቅዱና አሳቡ አባቷን መርደኪዮስን ጨምሮ ህዝቡን በሙሉ ማጥፋት ነበር። በዚህ ግዜም ህዝቡ “አስቴር ወገናችን አንቺ በቤተመንግስቱ ውስጥ ነሽና እባክሽ ለምኝልን! ሊያጠፉን ቆርጠው ተነስተዋል…!” ሲሉ ወተወቷት። አባቷ መርደኪዮስም የሚመጣባቸውን መከራ በማሰብ የተነሳ ማቅ ለብሶ ሰነበተ።

የዛኔ አስቴር በንጉሱ ዘንድ ያላት አቅም እርስዎ ዛሬ በአቶ መለስ ላይ ያልዎትን አያክልም ነበር። እንደ ልቧም ገባ ወጣ እያለች “ያንን ነገር እንዴት አደረግኸው?” ብላ መጠየቅ አትችልም። በዚህም የተነሳ ለንጉሱ “በህዝቤ ላይ የተጫነውን መከራ አንሳልኝ” ብላ ጥያቄ ከማቅረቧ በፊት ለድፍረቱም ለስኬቱም እንዲሆን ህዝቡ ሶስት ቀን ሶስት ለሌት እንዲፆም አዘዘች። እርሷም ፆም እና ፀሎት አደረገች። ከዛም ለንጉሱ እራት ግብዣ ካደረገችለት በኋላ፤ “ወገኖቼ በአንተ ትዕዛዝና በአስፈፃሚህ ሐማ የተነሳ ሊያልቁ ነው እባክህን ይህንን አታድርግ አለችው።” ይገርምዎታል ወድያውኑ ልመናዋን ሰማት።

ወ/ሮ አዜብ ህዝብዎ ላይ መከራ ተጭኗል። አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ አበሳ ውስጥ ነው። ከዛም ወረድ ብለን ይበልጥ ወደ እርስዎ ህዝብ ጠጋ እንበል ካልን የወልቃይት ጠገዴ ሰው መከራውን እያየ ነው። የመላው ትግራይ ህዝብ አበሳውን እየቆጠረ ነው። አማራው ጉራጌው ኦሮሞው ከንባታው ሃድያው እውነት እውነት እልዎታለሁ አንድም የደላው ሰው የለም። ድሎቱም ምቾቱም ያለው እዛችው አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ውስጥ ብቻ ነው።

በኑሮ ውድነት የሚጠበሰው አንሶ ለተለያዩ ልማታዊ መዋጮዎች በየቀኑ ገንዘብ አምጣ እየተባለ ነው። መሬቱ እየተወሰደ፣ እምነቱ እየተሸረሸረ፣ ቤተ አምልኮው እየፈረሰ ያለው ህዝብ የእርሶው ህዝብ ነው። እናም እንደ አስቴር ከንጉሱ ዘንድ የተጫነብን እንዲነሳልን ለምኑልን ብለን አብዝተን እንጮሀለን። አይዞት ሶስት ቀን ሶስት ሌት ፁሙ ማለት አይጠበቅብዎትም እኛ ቀድሞውንም እየፆምን ነውና ሃሳብ አይግባዎ…!

ባለፈውም ግዜም ያልኩዎት ይህንኑ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ በላይ ከህዝቡ ኡኡታ በላይ የእርስዎን ምክር እና ልመና ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አምናለሁ። እናም እባክዎ ለእርስዎ ጠቅላይ ባለቤት ለእኛ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት አቶ መለስ በህዝቡ ላይ የጫኑትን መከራ ያነሱ ዘንድ ይምከሩልን ይለምኑልን!

ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ብላችሁ ሁለታችሁም ዘወር ብትሉልንማ የመከራዎች ሁሉ መከራ ቀለለ ማለት ነበር።

ብቻ ቀዳማዊ እመቤት ይምከሩ እና እንደሚሆን ያድርጉ እባክዎን ጉዳዬን ችላ አይበሉብኝ። ኋላ ጥሩ ላይመጣ ይችላል።

አክባሪዎ…!

ወዳጄ እስቲ ቸር ያሰማን!

አማን ያሰንብተን!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

7 responses »

  1. susan says:

    HAhahahah……she never be smart like Aster Gadem lady never never……yekoshehsenebs yeyazech keletam set.

  2. Agazi Meles Kendebbo says:

    wow….Abe Tnx ! its nice !!

  3. zienamarqos says:

    ቁም:ነገሬ:ካሉት:ጠቃሚ:ምክር:ነው::በኋላ:አልሰማ:ብለው:መጥፎ:አድራጎት:ቢያስከትል:እንኳ:”ምከረው:ምከረው:እምቢ:ቢልህ:መከራ:ይምከረው”::ይላሉና:አንተ:ከፀፀት:ድነሃል::

  4. Eyob says:

    Abe betam emigerm tsihuf new….I really liked the way you spell every thing.Go on doing so please.

    Eyob

  5. Nehemiah says:

    ”ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ብላችሁ ሁለታችሁም ዘወር ብትሉልንማ የመከራዎች ሁሉ መከራ ቀለለ ማለት ነበር።”

    What a big Curse in the disguise of Blessing

  6. ከአዜቢና በለው! says:

    ለመልካም አሳቢያችን፣ ደጋፊያችን፤ታማኛችን ሆይ ባለፈው የላክልን መልክቶች ሁሉ ደርሶናል እኛም አስተያየታችንን በጊዜው ለመጻፍ ሞክረን ባለቤቴም በሥራ ተቦጠረ እኔም በስበሰባ አንድ ላይ ተቦጣጠርን በዚያም ላይ እንደምታውቀው ዓመት በዓሉ መጣ ብክንክን ብለን ሰነበትን መቼም የሀገሪቱን የዋጋ ግልቢያ ታውቀዋለህ ሳይቸግረን ሀገር እናሳድጋልን ብለን ድሮም ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮአችንን ለሕዘቡ እንዲረዳው ስናገር ሰምተሃል”ከአለም በድህነት አሉ ከሚባሉ መሪዎች ቀዳሚዎቹ እኛ ነን” ያቺን ፷፻፪፻የኢ/ብር ምን ስንት ቦታ ላድርጋት ደግንቱ ልጆቼ ቻይና እና አውሮፓ ሄደው በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ እነስሳትን እና ነፍሳትን መብላት ባይለምዱ ምን ይውጠን ነበር ?ወዳጆቻችንን ዛሬ እንደድሮው ሚኒስተሮችን ታጋይ ጓዶችን ጠርቶ መንበሽበሽ ቀርቷል። አራት ነጥብ። “ቢቻል የሚስማማችሁን መጠጥ አስጠቅላልላችሁ ኑ” አለበለዚያም ሚስ ኮል አድርጋችሁ የአምስት ዓመቱን ዕቅድ፣ ለሕዳሴው ግድብ አንደኛ ዓመት፤ፋሲካው በ፲፩በመቶ እድገት መሳካት ታስቦ መዋሉን ኤስ ኤም ኤስ ደስታችሁን ግለፁ ብለን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሁሉ ተላለፈ በአጭሩ ተገላገልን ይህ ከአንተ ወዳጃችን የሚደበቅ አደለም ምክንያቱም ብዙ አሽሟጣጭ እና በስላቅ የተካኑ ስላሉ ወሬውን ከእነሱ ከመስማትህ ብዬ ነው። በጣም ለቀረቡ እና አብረውን ከሚጨነቁ ታጋዮች ጋር ያሳለፍነው ፋሲካ ጤፍ ሰርገኛ ፲፻፬፶፤ በግ ፳፻፭፻ ;፤ቅቤ ፩ ኪሎ፻፹፤ ሽንኩርት ፵ብር ፤ዶሮ ፪፻ብር፤ ቅመማ ቅመም ፡ሰንደል ዕጣን(ከሕንድ የመጣ)፡ሰው ሰራሽ የረከቦት ሥር ጉዝጓዝ በስጦታ የተገኘ ፤ስንዴ ለአባሻ እና ለመድፊያ ፳፭ ኪሎ ፪፻፶፤ የተለያዩ መጠጦች ከግምሩክ የተወረሱ በስጦታ ጠላ የለም ህዘቡ የጠላን ይበቃናል ብለን ተውነው አንድ ጠጅ የሚወዱ ታጋይ አሁን ጉሉኮዝ እየጠጡ ስለሆነ ከመፎገር ዳንን እልሃለሁ አብዬ …. ለአይነት መስሪያ ለአልጫዎች ማለቴ ነው አንድ መደብ ቅርጫ፲፻፭፻ ብር (ጠቅላላ ወጪ )ሆኖ የተረፈው ፹ ብር ለመንገድ ላይ ልጆቼ እንዲበሸበሹበት አደረግሁ።አራት ነጥብ።ለመሆኑ አንተ ባለህበት አካባቢ ጭንቅላት የሚገዛ ታገኝልኛለህ ?አንተ የጠየከውን ሁሉ ለማድረግ ከፈለክ እዚህ ባለቤቴን ከሚሳለቁበት ሸጬ ባርፍ ብዬ ነው ።አልቻልኩም! አልቻልኩም! ይቺን ማስተዋሻ በራሴ ሥም ብፅፍልህ እንዳልፎገር ብዬ በዚህ በኩል ያድርስልኝ በለው!

  7. Danny says:

    Webanche Nafekechegn! Yezhch yemegermew, kegeter meta, yeBole baltet lehun maletuwa new. Men ale sew rasun behon?! Fetalash degmo Azo nekesat yemel mister tesemtuwal!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s