በፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ሆና በምትሰራበት ወቅት “አሸበርሽ” ተብላ የታሰረችው ርዮት አለሙ “ኢንተርናሽናል ውመን ሚዲያ ፋውንዴሽን” የተባለ ድርጅት የሚዲያ ጀግና ሲል ለሽልማት መረጣት።
ሽልማቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ራስን ለአደጋ አጋልጦ በጋዜጠኝነታቸው ለተጉ ሴቶች የሚሰጥ ሲሆን፤ ከርዮት አለሙ ጋር አንዲት የፓልስቲን እና አንዲት የአዠርባዣን ጋዜጠኞች ለሽልማቱ ተመርጠዋል።
እንደሚታወቀው ርዮት አለሙ በአሁኑ ግዜ የገንዘብና የእስር ቅጣት ተወስኖባት በቃሊቲ እስር ቤት የምትገኝ ሲሆን “አሸባሪ” ተብላ በተከሰሰች ግዜ ለማስረጃነት ከቀረቡባት መካከል የፎቶ ካሜራ እና በፍትህ ጋዜጣ ላይ ያሳተመቻቸው ፅሁፎች እና በፌስ ቡክ በኩል ሰዎች “ታግ” ያደረጓት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሚያላግጡ ምስሎች ይገኙበታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስክንድር ነጋን ሽልማት ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል አሜሪካ ሄዳ መቀበሏ ተሰምቷል። (እየተከታተላችሁ ያላችሁት… ልላችሁ እኮ ምንም አልቀረኝም…!)
ጥርጣሬ
መንግስታችን “አሸባሪ” ያላቸውን በሙሉ በተለይ በአሜሪካ የሚገኙ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጀግና እያሉ እየሸለሙ ይገኛሉ። አሁን አንዳች ነገር ጠረጠርኩ። በዚህ ብስጭት መንግስት አሜሪካ አሸባሪ ብላ የገደለችውን ቢላደንን እዛው ያለበት ድረስ ሄጄ የጀግና ሽልማት ልስጠው እንዳይል እየሰጋሁ ነው። እልህ ጩቤ ያስውጣል አይደል የሚባለው!
በመጨረሻም
ርዮት አለሙ እና ወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም የሙያ አጋሮቿን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ!
እስክንድር ተሸለመ !በማን ሲባል በአንድ መቀመጫው ኒዮርክ የሆነ ኒዮርክ አቀፍ ድርጅት ይባላል ; ብርትኳን ተሸለመች በማን ሲባል በአንድ መቀመጫው ዲሲ ያደረገ ዲሲ አቀፍ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት;ይባላል አሁን ደግሞ ርዮት አለሙ ልትሸለም ነው ሲትለኝ ተስፋ አርጌ የነበረው በቃ እችን’ማ ኢትዮፕያውያን (የኢትዮፕያ ህዝብ) ሊሸልማት ነው የምትል መስሎኝ ሰፍ ብየ ነበር ግን እንደጠበኩት ሳይሀን ያው እንደተለመደው አንድ በአሜርካ የሚገኝ የሴቶች ሚድያ ምናምን ይላል ልብ በል መንግስት ይሸልማት አላልኩም እኔ የምለው እነዚህ ሰዎች ”ለነጻነት” የሚታገሉለትን ህዝብ የአሜርካ ህዝብ ነው’ንዴ ሁሌ የአሜርካ ድርጅት የሚሸልማቸው እርግጠኛ ነኝ ለኛ ቢሆን የሚታገሉት ምን አሜረካ ድረስ አስደከማቸው እኛው እዝች አድስ አበባቸን አኮ እንሸልማቸው ነበር እናማ አቤ አሁን 2 ነገሮቸን ነው የሚታዩኝ አንድም እነሱ 20 አመት ሙሉ ”እየታገሉት”ያሉት ለሌ ህዝብ ነው ማለት ነው ይህ ያልኩበት ምክንያት ሁላቸሁም ተቃዋሚዎች ነን ባዮች ”እኛ የምንታገለው ይህን ህዝብ ከዚህ ጨቋኝ ስርአት ነጻ ለማውጣት ነው” ስትሉ ነው የምንሰማቹ አንድ ሰው ለራሴ ለመብቴ ነው የምታገለው ስል ሰምቼ አለላውቅምና ካልሆነ ደግሞ የኢትዮፕያ ህዝበ ኑፍግ ሆኖዋል ማለት ነው ግን ደግሞ የአገራችን ህዝብ በዚ የሚታማ አይደለም እና መቼ ይሆን እነዚህ ሰዎች ራሱ የኢትዮፕያ ህዝብ የኔ ናቹሁ ከአብራኬ ወጥታቹ ለኔ የምትታገሉት ብሎ በአገሩ የሚሸልማቸው አደራ መልሳቹ ግን ”በቅርብ”ነው እንደዳትሉኝ ቅርብ ነው እያለላቹ 21 አመተታት ሄዱ በመጨረሻ አቤ ያንተ ሽልማት ግን በናትህ ለየት አድርገው (አንተ ነህ የቀረሀሄው ብየ ነው) ባይሆን ጎረቤት አገር አድርገው አስመራ
Hi yosef,what a shame you have little knowledge of what is going in the world since you escaped from the jungle.its embarrassing, u don’t know about international prizes like the noble prize…..you have to be careful ur masters will not be happy,they are trying to win the prize of being the most arrogant tyrant leader in the world from a foundation based itself in china and north Korea.
አቤ ግን ሽሙጥህ ወግ ቢኖረዉ ጥሩ ነበር በተለይ የህዝብ ልጆች ላይ ጥንቃቄ ብታደርግ ወይስ ሽሙጥ ወግ አያዉቅም አመለካከትህ እንዳለ ሆኖ የሌሎችንም ስሜት ብትጠብቅ ደስ ይለኛል በቴዲ ላይ የሰጠኸዉ አ ስተያየት ሚዛናዊ ስላልመሰለኝ ነዉ እና ሽሙጥህን ወደራስህብታዞረዉ ጥ ሩ ነዉ ግን አድናቂህ ነኝ
Hi Sister you are the bist and good!! you did marvelous history!!I am proud of you all Ethiopia proud of you and you very proud to be from Ethiopia !! and you stad form this brutlly woyane foscist abd racist rorganiz mafia , you are a victim of evil an you struggle for freedom!! betam ewedsholew!!you will be soon free!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
God bless you and keep you!!!
Yosef!!
Do you think Ethiopians can award a journalist labeled by the woyane as “terrorist”?
They are telling us not to have tea with them let alone awarding! Those true journalists are always with the people! which means against the woyane tyrant group! But we Ethiopians love them and acknowledge their sacrifice. and guys like you chase, harasser, imprison and kill them.