ይህንን ጨዋታ ስፅፍ ፋሲል ደሞዜ የተባለ አቀንቃኝ “አለ ነገር…” እያለ የሚያንጎራጉረውን ሙዚቃ እየሰማሁ ነው! ልብ አድርጉልኝ ይህ ስጋት ነው እንጂ ቅስቀሳ አይደለም! ምክር ነው እንጂ ቁጣም አይደለም! አክብራቹሁ ብሎጋችንን የምትዘጉ ሰዎች ምክራችንንም ስሙ…!
አስቲ ሰሞኑን የሰማኋቸውን አጫጭር ዜናዎች ልንገራችሁ።
አንድ
በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባብን” ያሉ ሙስሊሞች ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች በተከፈተባቸው ተኩስ አምስት ሰዎች ተገደለው በርካቶች ቆስለዋል። መንግስትም “አስር ፖሊሶቼ ተጎድተውብኛል ብሏል።” ይህ እንግዲህ የመርካቶው አንዋር መስጊድ እንቅስቃሴ አካል ነው። ይህንን መንግስት በሰላም እንዲፈታ ሁላችንም መክረናል ለምነናል ሰሚ ግን አላገኘንም እናም፤ መርካቶ አለ ነገር አትሉልኝም!
ሁለት
ጋምቤላ ከመሬታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰቡ አካላት በሼኩ እና በፓኪስታኖቹ የሩዝ አምራቾች ላይ እያሰሙ ያሉት ተቃውሞ ከእለት እለት እየተባባሰ፤ ወደ ተቀናጀ ጥቃት ተለውጦ አሁን በቅርቡ በሩዝ እርሻው ላይ ሲሰሩ የነበሩ የውጪ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ላይ እስከ ሞት የደረሰ ጉዳት አድርሰውባቸዋል። ይህንንም አቤት እያሉ ሲጮሁ የነበሩ ብዙ ናቸው ግን ማን ይስማ…? በዚህም የተነሳ ጋምቤላ አለ ነገር! ያስብላል።
ሶስት
የዋልድባ ገዳምን ህልውና በሚፈታተን መልኩ የስኳር ምርት ሊያመርት መንግስት ደፋ ቀና እያለ ነው። የገዳሙ ሰዎችም “ተዉ ስለ እግዚአብሄር ብላችሁ አትንኩን” ብለው ቢለምኑ ቢማፀኑ የሚሰማ አላገኙም። መንግስት ነብሴ በቴሌቪዥኑ “ዋልድባ ሳይነኩት ጮኸ” አይነት ይዘት ያለው ዘገባ አሰራ! ቄሱም ዲያቆኑም መከረ ዘከረ “መንግስት ሆይ እባክህን ነገርህን በልኩ አድርገው!” አሉ። ነገር ግን አልሰማም። ልክ በአሁኑ ሰዓት የጎንደር ህዝብ ነብስ ወከፍ መሳሪያውን ይዞ በአስፈሪ ሁኔታ ወደ ዋልድባ ገዳም እየተመመ እንደሆነ ሰማን… ጎንደር አለ ነገር ማለት ይሄኔ ነው!
“ሶስት በአንድ” ይሄ እነ “ማዘር ቤት” የመሳሰሉ ምግብ ቤቶች ገብተን ምግብ የምናዝበት ቋንቋ ነው። ብዙ ግዜ እንደዚህ የምናዘው ለአራት ሆነን ነበር። አሁን ግን መንግስታችን ብቻውን ሆኖ ሶስት በአንድ አዟል። ደሞ ሌሎች ተከታዮችም አያጣም…!
ታድያልዎ ምን አስጨነቀኝ መሰልዎ… መንግስት ምን ያህል ቢርበው ነው ሶስት በአንድ ያዘዘው? የሚለው ጥያቄ ያሳስበኛል። በአዲስ መስመር እንደተለመደው መንግስቴን እመክራለሁ…
አረ ተዉ ግድ የላችሁም…! አንድ ግዜ ሰዉ ምን እያለ እንደሆነ ቆም ብላችሁ አዳምጡ! እየተጠየቁ ያሉት እጅግ በጣም ቀላል ቀላል ጥያቄዎች ናቸው። ነገር ግን እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ከከበደን የምንከፍለው ዋጋ ይወደድብናል! እባካችሁ!!! ሶስት ለአንድ አያልቅም ትዕዛዝም ልክ አለው! ተዉ…!
true
batam batam tekekel gene mene adereganaw naw endaze mefatatanane ?
“መንግስት ምን ያህል ቢርበው ነው ሶስት በአንድ ያዘዘው? የሚለው ጥያቄ ያሳስበኛል።” ማ ነው ?አቤ ወዳጃቸሁ(…)
በጣሙን ተራበ እጅግ ሞረሞረው ፤
እግዝሐብሔር ቸር ነው የጠየቁትን የማይነሳው፤
እንኳንም አዘውት ቀድሞም ዝግጁ ነው፤
በእያይነቱ ቀርቧል መልካም ጥጋብ በለው!!
woooooooooooooo!!!beqa belew menew! we reject you woyane ,silent vioence and kelleing most stop!! we stand for justice and freedom!!! FREE Andualm!! and all preisn!! and free all ETHIOPIAN!!!
we are one love one Ethiopia!!!!! God bless MAMA ETHIOPIA HAGRE!!!!
*የፓርላማ ውሎ ካለፉት ጊዜዓት በረድ ሰከን ያለ አቀራረብ አለው::ድሮም ውሽት በደጋገሙ ቁጥር ሊቁ,ምሁሩ, ጠበብቱ,ውበት ከቅንድቡ እያላችሁ ግለሰቡን መረን ለቀቃችኋቸው አሁን መመለሻው ቸገረ::እሳቸውም እራሳቸውን ያደንቃሉ! አቤት የነገር ያለህ “የወደድሽው ቂጣ ሰተት ብሎ ወጣ” ተጀመረ እንጂ አላለቀም ቻለው ተው ቻለው(…)
+++ ጠንቋይ/ሚኒስትር በፓርላማ ውሎአቸው “ሲቲንግ ዳውን ኮመዲ” ቀልደዋል የፓርላማ አባላት ጥጋብ ላይ ሥለሰነበቱ እንቅልፍ ላይ ነበሩ። የዋጋ ንረት ምንጩ(ሀ)የአለም ማዕድን እና የግብርና የገበያ ዋጋ መዋዠቅ (ለ) የኢሲያ ሕዝቦች ኑሮ መሻሻል ኢትዮጵያን የሚመለከታት ማዕድን(ነዳጅ) ነው።ለመሆኑ በቆሎ እና ስንዴ ነዳጅ መጠጣት ጀመረ?አሃ ! አሃ ! አሃ ” ባልታወቀ መንገድ የእህል ውጤቶች ወደ ጎረቤት ሀገር መጓዝ? ? ?አይ የብሔር ብሔረሰቦች ሊቀመንበር ይህንን በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ጽሑፍ ላይ በደንብ አስቀምጬልዎት ነበር ሄደው ያንብቡ። ከዚህ በፊት አቤ እንዳለዎ ፌስ ቡክዎ ላይ አድ ቢያደርጉት ከካድሬዎችዎ በበለጠ ብዙ ነገር እናማክርዎ ነበር። “አድሎ እና ሙሰና” መንግስት የሚታገለው በአንድ እጅ ነው ? ? ? ? ? ሁልጊዜም የሀጢያት ሥራ ሲሰራ በድብቅ እና በአንድ እጅ ነው! (እናንት አመለኞች የታች ቤቶች አተረጓጎሙን አታበላሹ) አቶ መልስ ደህና ነዎት? ? ?“የኢትዮጵያ ሕዝቦች መንግሰት” ድሮስ የአላዋቂ ሳሚ “ብሔር ብሔረሰቦች” የት ሄዱ? እርስዎ ሕገመንግስት ከመጻፍዎ በፊት እስላም እና ክርስቲያኑ እንዴት በፍቅር ይኖር እንደነበር ታቦት አይነቀልም ብሎ ይሟገት እንደነበር መሰከሩ::በእርስዎ የሃይማኖት እኩልነት ጊዜ በተለይዩ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያናት ተቃጥለው ሕዝቦች መሬት ላይ እየተንደባለሉ ሐዘናቸውን ሲያሰሙ አየን !!”መንግስት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው” የሚሉት : ለመሆኑ ሕገ መንግስትዎ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ይላል? ? ? >? እርስበረሳቸው ለሚጣረሱ (ለሚናቆሩ) ግን ይረዳል፤ ያበረታታል፤ ይደገፋል:ይመክራል: ያስጠናል፤አሰልጣኝም ይልካል!!!!!! ለመሆኑ ህገ መንግስትዎ የመዘዋወር እና የመንቀሳቀስ መብትን እንዴት ይተረጉመዋል? ሕገ ወጥ ሰፈራ (ሞፈር ዘመት) በተለይ አማራ!! ክቡርነትዎ ተመስገን ደስአለኝ አማካሪዎችዎን በጨረፍታ ሲዥልጥልዎ እኔ ግን ሕገ መንገስትዎን በቀጥታ አልወደድኩልዎትም ሁልጊዜም በሕገመንግስቱ ተጠቅመው ህዝብ እንደሚያወናብዱ፣ እንደሚዋሹ፤ ካድሬዎችዎም ይሁኑ፤ ጆሮ ጠቢዎችዎ፤ አማካሪዎችዎ፤ አውርቶ አደሮችም፤ እንዴት፡የውሸት፡ለመስፈራሪያነት፡እንደሚጠቀሙበት፡ህዘቡ፡መማር፡አለበት።
ሰው ካልተማረ አምና ከአቻአምናው ፤
ችግር ሳያበዛ ዘንድሮ ለነገው ፤
ጀግና ተነስ እና እምቢኝ በቃ በለው!!!!!!