የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመሰገን ደሳለኝ ከዚህ በፊት በምታወጣቸው ፅሁፎች በፍርድ ሂደቱ ላይ ጣልቃ ገብተሃል  ተብሎ ተከሶ እንደነበር ይታወሳል።

ተመስገን “የተከሰሱኩት አለ አግባበብ ነው ነው” በሚል ተከራክሮ ፅሁፉ ተከሳሾች የሰጡት መሆኑን አስረድቶ ነበር። ይህንንም ለማረጋገጥ አቃቤ ህግ አበበ ቀስቶ (ክንፈሚካኤል ደበበን) ለምስክርነት ጠርቶት የነበረ ሲሆን መስካሪውም “በፅሁፉ መጠየቅ ካለብኝ የምጠየቀው እኔ ነኝ። ሃሳቤን በፍርድ ቤት ለመግለፅ ባለመቻሌ ጋዜጣ ላይ እንዲወጣ አድርጌያለሁ!” ብሎ ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር።

በዚህም ዛሬ ሚያዝያ 22/2004 ዓ.ም ድጋሚ ቀጠሮ ይዞ የነበረው ፍርድ ቤት በተመስገን ደሳለኝ ላይ አራት ወር እስር ወይም ሁለት ሺህ ብር እንዲሁም በአበበ ቀስቶ ላይ ወደፊት ከሚፈረድበት ላይ የሚጨመር ስምንት ወር እስራት ተፈርዶባቸዋል።

በአሁኑ ሰዓት ተመስገን በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኝ ሲሆን ከባንክ የሁለት ሺህ ብር ሲፒዮ ጓደኞቹ አሰርተው እስኪመጡለት ድረስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ተመስገን ሲፒኦው ለዛሬ ካልደረሰለት ነገ የስራ ቀን ባለመሆኑ ዛሬ እና ነገን እስር ቤት ለማደር ሳይገደድ አይቀርም ሲሉ ወሬውን ያቀበሉኝ ወዳጆቼ ስጋታቸውን ገልፀውልኛል!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

6 responses »

 1. Yigermal.. says:

  Ere Yidebral…Betam Yidebral
  Ejig Eji Eji Yale Mengit Hone!!!!

  Shame Yelem Ende bageru???

 2. Viva says:

  Lets also see what the court will decide on ETV. If simillarly treated ETV deserves 20 years for airing the ‘Akeldama’

 3. Kulich says:

  What about Meles Zenawi who declared in parliament that all the defendants in the terrorism trial are already guilty?

 4. Kinfe says:

  Greetings,

  It wasn’t a surprise for me. But, I would like to point out to you that these days your blog is serving like a news feed website. While no one hesitates to read news from the blog, you are better off writing your own thoughts, satirical comments, not reporting news. It would be very kind of you to transmit such kind of information/news to outlets such as ESAT.

  Secondly, you are also posting almost on a daily basis. In my view, that reduces the strength and readiblity of your posts. The more time you take, the more informative and satirical your blogs will be. Hence, I would suggest posting, say, three times in a week as opposed to on daily basis.

  Else, keep up the good work.

  Best,

 5. በለው! says:

  እንኳንም ዓቃቢ ሕጉ ዳኛው ካድሬውም የመከላከያ መልሱን ማንበብ በመቻላቸው ተመስገን ደስ አለኝ የዚች ፳፻ ብር ቅጣት፡በሗላ ትንሽ፡ መዘዝ፡አላት፡መጠንቅ፡ነው፡፡ በምንም ተዐምር፡በቀን፡፩፯ ብር፡ሂሳብ፡ቦንድ፡አይሸጥለትም፡!!! የሚያስቀው፡ነጥብ፡የተፈረደበት፡ገና፡ሊወጣ፡በታቀደ፡ህግ፡መሆኑ፡ነው ።በ>ሳ>ቅ ቅ፡ቅ፡ቅ፡ ጠርጥር>>በ>>ለ>>ው!

 6. በለው! says:

  ቶሎሳ ኡርጌሳ የሚባል ካድሬ አይጋ ፎረም ላይ ካሰፈራት የጠ/ሚ ቃል እንደሕግ ለሕዘብ ተገልበጦ ሲፃፍ…
  “‹እስክንድር ነጋን ሳስበው…፪› በሚል ርዕስ
  ድብቅ ዓላማቸውን ተፈፃሚ ለማድረግ ተሯሩጠዋል፡፡ ራሳቸውን በጋዜጠኝነት ስም ጀቡነው በምግባር
  ከጋዜጠኝነት መርሆዎች ጋር የማይተዋወቁት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ፣ በዚህ ጭፍን ፅሑፍ እንዲህ በማለት
  ከሽብር ተጠርጣሪው ግለሰብ ጋር በቃሊቲ ተነጋገርኩ ይሉናል፡፡…
  ተጠርጣሪ — ‹…ክሱ ምንም ይሁን ምን አያሳስበኝም፡፡ አሸባሪ አለመሆኔን ታውቃለህ፡፡…›
  አቶ ተመስገን— ‹አውቅሃለሁ ፡፡ ለሀገርህ ከላይ ታች ስትል በቅጡ እንዳልኖርክም አውቃለሁ፡፡…›”
  ******የተወደዳችሁ ምእመናን ይቺ ዓረፍተ ነገር ናት ፳፻ ብር ያወጣችው ወንጀል ? ?
  “እርግጥ እዚህ ላይ አቶ ተመስገንና አጫፋሪዎቻቸው አስመልክቶ በርካታ ጥያቄዎችን ማንሳት
  ይቻላል፡፡ ይኸውም እነዚህ ወገኖች ስለምን በሽብርተኝነት የተጠረጠሩትን እንደ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣
  እስክንድር ነጋ፣ ክንፈሚካኤል አበበ ወዘተ… የመሳሰሉ ግለሰቦችን ደብዳቤ ከፍርድ በፊት እያተሙ
  ያሰራጫሉ ፣ ስለምን ክሱን የሚያጣጥል ዘገባ ያቀርባሉ፣ ስለምንስ የዳኞችንና የአቃቢያነ ህጎችን የስራ
  ነፃነትንና ተዓማኒነትን ለማጉደፍ ይሯሯጣሉ? ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በመፃረር ስለምን ህገ-መንግስቱን
  የሚሸረሽሩ የቁራ ጩኸታቸውን ሰሚ አልባ በሆነ ጭው ያለ በረሃ ላይ ይዘራሉ? በዓላማ ቁርኝት የእነማንን
  አጀንዳስ እያራመዱ ነው?.. (ቶሎሳ ኡርጌሳ የጠቅላይ ሚ/ሩን የፓርላማ ቀረርቶ በትረካ መልክ ካስነበበው)
  ኢሕአዴግ ጥሩ ጥሩ ቀልመማዳዎችን ፈልፍሏል!! ታዘብን በለው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s