ትላንት ለሊቱን በሙሉ ማውጊያ ብሎጋችን ኢትዮጵያ ውስጥ የማይዘጋበትን መላ ሳንሰላስል ነበር። ታድያ አንዳች ዘዴ መጣልኝ። ልማታዊ ጨዋታዎችን መጨዋወት ጥሩ ዘዴ እንደሚሆን አስብኩ። ታድያ ልማታዊ ዜና ከየት ይመጣል…? ብዬ ሳስብ፣ ሳስብ፣ ሳስብ… አንድ ወዳጃችን በዚህ ሳምንት ውስጥ በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ የለጠፈው አሪፍ ልማታዊ ዜና ትዝ አለኝ። ወዳጄ ስሙ ጠፋኝ… (ምን የስደተኛ ነገር እንኳን የሰው ስም የራሱንም ስም ይረሳል እኮ…! እናም ወዳጃችንን ይቅርታ ጠይቄ እቀጥላለሁ!)
ይህ ወዳጃችን የለጠፈው የምስራች ሮይተርስን ጠቅሶ ሲሆን፤ ሀገራችን አለ የተባለ እድገት እያሳየች እንደሆነ ያወሳል። ዕድገት ቢልዎት ደግሞ ዕድገት ብቻ አይምሰልዎ “ፈጣን እድገት” ብሎ ነው የዜና ወኪሉ ሮይተርስ የገለፀው። ታድያልዎ ክፉ ክፉውን ብቻ ሁሌ ከምናወራ እና ብሎጋችንንም ከምናዘጋ፣ ከፀሐዩ መንግስታችንም ከምንቀያየም ለምን እንዲህ ልማታዊ ጨዋታዎችን እየተጨዋወትን ግዜውን አንገፋም ስል አሰብኩ።
በርግጥ በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው እድገታችን 7.5% የሚል ነው። በዚህ ብዙ ቅር አይበልዎ። ይሄ የምናዛሬ ጉዳይ ነው ድሮም ቢሆን ቁጥር በነርሱ ሲሆን ዝቅ በኛ ሲሆን ከፍ ይላል። እንኳንስ ሌላ ይቅርና ሰዓት ራሱ እኛ ሰባት ሰዓት ሆኗል ስንል እነርሱ አንድ ሰዓት ነው ይላሉ። ገንዘባቸውም እንደዛው ነው። እነሱ አንድ ሲሉ እኛ አስራ ሰባት እንላለን። ባጠቃላይ እኛ ቁጥር ላይ ቁጥ ቁጥ አናውቅም እነሱ ደግሞ የቁጥር ገብጋቦች ናቸው። ስለዚህ በእድገቱም 7.5 ቢሉንም 11.2% ጋር እኩል ነው እና ደስታዎን ይቀጥሉ።
አዎ መንግስታችንን ማመስገን አለብን! የእምነት ተቋማት ረዥም እድሜ ለምንግስታችን እንዲሰጠው ምዕመናኖቻቸውን ለፀሎት መጥራት አለባቸው። ባለውቃቢዎች የእድገት ባለቤት ያደረገን መንግስታችን ዘላለም እንዲኖር ውቃቢያቸውን መለማመን ይገባቸዋል። መጫኛ የሚያቆሙ ደብተራዎች መንግስታችንን እንደመጫኛው ቀጥ ብሎ እንዲቆም ጥበባቸውን ሊጠቀሙ ይገባል። (እዝች ጋ አሽሟጣጮች አሁንስ ተጠቅልሎ ነው ያለው? ብለው ፈታኝ ጥያቅ ቢጠይቁንም እንዳልሰማ እናልፋለን!)
የዚህ አይነት ዕድገት ባለቤት ያደረገን እርሱ ኢህአዴግ የተባረከ ነው! ብለንም እንዘምራለን! እልልታውንም እናቀልጠዋለን!
ሀገራችንን በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያሳዩ ካሉ ሀገሮች ከቀዳሚዎቹ ተርታ አሰልፏታልና! እርስዎም ይደሰቱ! … እኔ በበኩሌ ደስታዬን ለመግለፅ ድግስ ሁሉ ለመደገስ አስቢያለሁ። አስቡት እስቲ ከሃምሳ ምናምን አገሮች በእድገታችን ግንባር ቀደም ከሚባሉት ወገን መሆን ከየት ይገኛል? እውነቴን ነው የምልዎ እስከዛሬ ድረስ መንግስታችን ሲናገር ለፕሮፖጋንዳ ይመስለኝ ነበር። ለካስ እርሱቴ ምን በወጣው…! በእውነቱ ስናውቅ በድፍረት ሳናውቅ በስህተት ላንጓጠጥነው እና ላሽሟጠጥነው ይቅርታ መጠየቅ አለብን!
ወዳጃችን ከሮይተርስ ያገኘው ዜና ይህ ነው፤
Reuters- According to reports released by the International Monetary Fund, five of the fastest growing countries last 2011 are in Africa. This includes the countries of Ghana (13.5%), Eritrea (8.2%), Ethiopia (7.5%), and Mozambique (7.2%).
ምነው…? ምን ያስቅዎታል? አዎ ፈጣን እድገት እያሳዩ ያሉ ሀገሮች ውስጥ ተካተናል። በርግጥ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ኤርትራ በዕድገት ደረጃዋ ከእኛ ትበልጣለች። ይሁና! እባክዎ ወዳጄ አይሳቁ ብሎጉን እንዳያዘጉብን!
እኔም ሳቄ ሳያመልጠኝ ልሰናበትዎ… ካልተዘጋ በዚህ ከተዘጋ በሌላ ማውጊያ እንገናኛለን!
Abie, I really love your ‘shimut’.
If you blog on https://sites.google.com/ there will be no chance for TPLF to block your site (Blocking your site will be blocking google).
PM Meles to our president Girma w/giorgis
ያኔ ሲነግረኝ ሰው ፈርቶ
አቛቛሙን አይቶ
ለኔ እንደማትሆነኝ
አልሰማም አልኩና
ስትቆም ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
እምቢ አለ ሆዴ ካለሱ
መቆም ሲጥር በራሱ ።
እግሩ ሊሄድ ሲነሳ
ዎፌ ቆመች እምቦሳ።
ስትቆም ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
ባለፈው ሞተ ብለው ቢነግሩኝ
እኔ አላምንም አልኩኝ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
“ፈጣን እድገት”….” በከፍተኛ ደረጃ”…”በተከታታይ”… “ደብል ድጅት”… 11% ያለማቋረጥ ላለፉት አምስት ዓመት” “መካከለኛ ገቢ ካላቸው ጎን መሰለፍ” ሰሞኑን ሾላ ገበያ የወጣቸው ዶሮ ማንበብ ብትችል ኩኩሉ ባለች ነበር፤ አውራ ዶሮ ለአውራው ፓርቲ ሥልጣኑን ስለለቀቀ እነኳንም ኩኩሉ ሊል እንቁላል ስረቶ ለማሰራት ተዘናገቷል፤ ትውልዱ እንኳንስ እንቁላል ሊበላ በስዕል ወረቀት ላይ ለመሳል ተቸግሯል! ለመሆኑ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከእንግሊዝ ኢኮኖሚ በጥፍ በልጧል ብሎ ሰሞኑን ያወራኝ ማን ነበር? ? ለመሆኑ 11.5% ደብል ድጅት 2 X 5 ዓመት =21.5% ዕድገት ? ላለፉት ሰባት ዓመት 6.5 የበለጠ ዕድገት አፍሪካ አደለም ሌላም አህጉር አልታየም፤፤በእውነት ይህ እድገት በጥቂት አውርቶ አደርና ሰርቆ አደሮች አካባቢ አለ የወደፊቱ የሀገሪቱ መጨረሻ ምስቅልቅል እና የትውልዱ በቁም የመሸጡ ሁኔታ አሳሳቢ ነው፤!!! የዲያስፖራው(የፈላሹ) ኢንቨስተሮች፣ አውቆ አበድ ምሁራን፤ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ሀገሪቱ መውደቋን ይመሰክራሉ(…) ተንበርክከው ብቻ አደለም መሬት ላይ ተንደባለው በዓለም የታወቀው ነጋዴ (WALMART) ሀገራችን ገበቶ ገበያውን ካልተቆጣጠረልን በከፍተኛ ደረጃ ችግር ይገጥመኛል ይላሉ፤የባሰ የሸቀጥ መጥፋት እና የዋጋ መናር እንደሚከሰት አስጠንቅቀዋል፡ ይህም የሕዝብ ፍጆታ የሆኑ የምርት ውጤቶች በነፃ ገበያ ብቻ ሳይሆን በነጻ ጎዳና በማለፋቸው ነው፤ የት? ዲያስፖራውን ጠይቁ ! በጣም ያሳሰባቸው ይህ ገበሬ፣አርበቶ አደር፤ከፊል አርበቶ አደር፤እነዲሁም አዲሱ የአማራ ስያሜ “ሞፈር ዘለል” ስለ ድሃ ልጆቹ ጥራጥሬ እና ዳቦ ሳይሆን የኢንቨስተሩ ልጆች በሀገር ውስጥ የሚመረትን ምግብ በጥራቱ ስለማይተማመኑበት ‘ዎልማርት’ ሲመጣ ጥራት ያለውን ምግብ ልጆቻቸው እንደሚያገኙ እምነት አላቸው። አወይ የነበሩበትን መዘንጋት!! የድሃው ልጅ ተርቦ ፤ተሰድቦ፤ተዋርዶ፤ተሰዶ፤ በሀገሩም የበይ ተመልካች ሆኖ በንዴት ከሚቃጠል ከወዲሁ ለመብቱ፤ለነፃነቱ፤ለእኩልነቱ፤ለዜግነቱ፤ለህልውናው መቆም አለበት፡አድሎን እንቢኝ በለው!ከሀገረ ካናዳ.
በለው
Thank you for your comment.
Development exchange rate:
International (IMF) Rate Local (Shabiya/Woyane) Rate
Ethiopia 7.5% 11.2%
Eritrea 8.2% 17%