ጋዜጠኛ እና መምህርት ርዮት አለሙ “አሸብረሽናል” ተብላ አስራ አራት አመት እስር እና ሰላሳ አምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባት (መቼም የዛሬ ፈራጅ ከየት ይመጣል ብሎ አያስብም…) ብቻ በአሁኑ ሰዓት በቃሊት እስር ቤት ትገኛለች።

ርዕዮት ከፍርዱ በፊት “ኤልያስ ክፍሌ አሸባሪ ነው” ስትይ መስክሪ እና ትፈቻለሽ ተብላ፤ በማስፈራራትም በማባበልም ብትጠየቅ አሻፈረኝ “እኔ የማውቀው ኤልያስ ጋዜጠኛ እንደሆነ ነው። በማላውቀው ጉዳይ ላይ አልመሰክርም።” ብላ በአቋሟ በመፅናቷ አሳሪዎቿ፤ “እንዲህ ጠንካራ አቋም ካለሽ ለምን ጫካ አትገቢም”  ብለው ሲዘባበቱባት እንደነበር በዛ ሰሞን ስንሰማ ሰንብተናል።

ታድያ ይቺ መምህር እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በጡቷ አካባቢ ያጋጠማትን ተደጋጋሚ ህመም ለእስር ቤቱ ኃላፊዎች ስታመለክት የቆየች ሲሆን አንድ ግዜ “ፓራሲታሞል ዋጪበት” ስትባል። ሌላ ግዜ ደግሞ “አንቺን ሃኪም ቤት የሚወስድ ሴት ፖሊስ የለም” እየተባለች በህመም ስትሰቃይ ቆይታለች።

ማክሰኞ ሚያዝያ 16/2004 ዓ.ም ግን ፓራሲታሞሉም ከቃሊቲ አለቀ፣ ሴት ፖሊስም ተቀጠረ መሰለኝ (ይሄ የኔ ጥርጣሬ ነው) ፖሊስ ሆስፒታል ተወስዳ ነበር። ርዕዮት በሆስፒታሉ ኦፕሬሽን አድርጋ በዛው ቀን ወደ ቃሊት እስር ቤት ተመልሳለች። አረ ግፍ ነው… ትንሽ እንኳ አረፍ ሳትል? ቢሉ የሚመልስልዎ መንግስት የለም።

በአሁኑ ግዜ መመህርት እና ጋዜጠኛይቱ “አሸባሪ” ሻል እያላት መሆኑንም ሰምቻለሁ!

በመጨረሻም

ኦፕሬሽን ስል ምን ትዝ አለኝ መሰልዎ…

ርዕዮት በታሰረችበት የነ ኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ ከታሰሩት መካከል የአውራምባው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በፍርድ ቤት ማስረጃ ሆኖ ከቀረበበት የስልክ ለውውጥ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፤

ውቤ ወንድሙ ከውጪ ሃገር ይደውልለታል። የሚጠይቀው ስለ አባታቸው ህመም ነበር። ታድያ ወንድምየው… “እሺ አሁን አባባ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?” ይለዋል። ውብሸትም “ኦፕሬሽኑ ተከናውኗል። ስለዚህ ገንዘብ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል” ብሎ ይመልስለታል።

እናልዎ ጠላፊው ከመጀመሪያው ጀመሮ ስልኩን በትጋት አልጠለፈም መሰለኝ… “ኦፕሬሽኑ ተከናውኗል ገንዘብ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል” ያለውን ብቻ ቀድቶልዎ…   “ኦፕሬሽንን” ያልከው የሽብር ኦፕሬሽን ነው። በሚል ማስረጃ ሆኖ ቀረበልዎታ…

አረ ይሳቁ ወዳጄ ከት ብለው ይሳቁ እንጂ…!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

2 responses »

  1. rediet says:

    HAHAHAHAHAHAHAHAHAHAHAHAHAHAHA…….wey abe

  2. በለው! says:

    “አሸብረሽናል” ? አልገባኝም !! (አሸብረ_ናል) (አ_ብረሽ) (አ_ብረሽናል) (_ _ _ረሽና_) (አ_ _ረ_ናል) ይህ ቃሊቲ የሚወረወር ሁሉ ለአውራው ፓረቲ ማጠናክሪያ ነው ?ወይንሰ በእስር ላይ ሆኖ ቦነድ እየገዛ ይሆን ይህ ሁሉ ገንዘብ የሚፈረድበት? ? ? የዚህ የጠለፋ ነገር ጠ/ሚ እንዳሉት” የኢትዮጵያ መንግስት ያበደ እንደሚሆን የማይገምት የለም ” አሁንም በሰሜን ጎረቤት ሀገር የታሰበው ኦፕሬሽን ወደ ታችም ዝቅ ብሎ ቢቆርጥ ሰላም ይሆን ነበር እስከዚያው መልካም ቀዶ ስንጠቃ ይሁን በለው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s