ኢናሳ የተባለው የኢትዮጵያ ቆላፊ እና ጠላፊ መስሪያ ቤት የግለሰቦችን ፌስ ቡክ ሳይቀር በመቆለፍ ስራ ተጠምዷል። በትላንትናው ዕለት በርካታ ብሎጎች ድጋሚ እንደተዘጉ ሰምተናል። መንግስቴ ፈርቷል… በእውኑ እንዲህ ያለው ፍርሃት “ተራሮችን ካንቀጠቀጠ ትውልድ” አይጠበቅም…

እኔን ጨምሮ ሌሎችም “ባለ ብሎጎች” አንዱ ቢዘጋ በሌላ መስኮት ወደ አገራቸን መግባታችን እና ከወዳጆቻችን ጋር መጨዋወታችን እንደሚቀጥል እርግጠኛ ነኝ። ስለዚህ የተዘጋው በር ሁሌም  መንኳኳቱ አይቀርም ማለት ነው። ታድያ በተንኳኳ ቁጥር መንግስት እየተነሳ ሲዘጋ መንግስቴን ስትራፖ እንዳይዘው ሰጋሁለት…!

የዛሬ ሃሳቤን  በግጥም ብገልፅ በደንብ ይወጣልኝ ነበር። ነገር ግን ብንደፋደፍ ብንደፋደፍ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። ታድያ ከወዳጆቼ ጋር ለምን አናዋጣም ብዬ እንደዚህ ጀመርኩ፤

በአንኳኪ ብዛት ሰላም ከምታጣ

በርህን ክፈተው ያሻው ይግባ ይውጣ…

ይበሉ ወዳጄ አንድ አንድ ስንኝ ያዋጡ… ከዛ ዜማ አበጅተን እንዘፍናት ይሆናል።

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

10 responses »

 1. HGOS says:

  አልከፍተውም ብለህ ዘግተህ ከተቀመጥክ
  ሁሌም ስናንኳኳ ሰላምክን ታጣለክ…..

 2. ቁልፎቹ ላይ ቆመህ በፋራ ረገጣ
  “በመስኮት ዝለሉ” ካልከን በለገጣ
  ልናርፍ እንችላለን ከራስህ መላጣ

 3. ETHOPAR says:

  በአንኳኪ ብዛት ሰላም ከምታጣ
  በርህን ክፈተው ያሻው ይግባ ይውጣ
  ብየ ባማክረው የእቴጌዋን ባል
  አንት አሸባሪ እስር ይገባሃል
  ብሎ መለሰልኝ ፍርድን ቀለል አድርጎ
  ቀጥሉበት …..

 4. ermi says:

  ማሪያምን ብያለሁ ክፈተው በሩን
  ደምም ሳንፋሰስ ሳልመዘው ጦሬን፤
  በጣም ተከፍቼ ብሶቴን ሳሰማ
  ጆሮ ዳባ ካልከኝ ምንም እንዳልሰማ፤
  ቤቴ የገባሁ ቀን…፣ ቤቴ የገባሁ እለት!!!
  በጦሬ በጥሼ የበሩን ሰንስለት
  አንተን አያድርገኝ አቤ..ት ያችን ሰዐት።

 5. Time19 says:

  በመረጃው ዘመን ዓለም አንድ ሆና
  ካንዱ ጫፍ አንዱ ጫፍ በሰኮንዶች ፍጥነት እያገኘን ዜና
  ያለም ሳይንቲስቶች፤ ጠቢባን ጉድ በሉ
  ጦቢያ በብረት ቁልፍ ተዘግታለች አሉ።

  ልጆቿ አለቀሱ፣እራበን እያሉ፥
  የንጀራው ሲገርመን መረጃም ተራቡ፣

  ያለም ሃገራትን እድገት ነፃ አዋጣ፥
  ከድህነት ማዕበል ከልመና ጣጣ
  ነገር ተገልብጦ እሱስ በኢትዮጵያ አሳር ይዞ መጣ፥
  እንጀራ እየቀጣ ሰው ዜና እያሳጣ።

  የበሩ ዘበኛ አንተ ቆላፊው
  ከማንስ አይተህ ነው፥
  ከየት ተማርከው።
  ማርክም በፌስቡኩ ዓለምን አንድ ሲያረግ፥
  አንተ እንደ ግመል ሽንት ወደኋላ ወረድክ።
  አሁንም ልምከርህ፥
  ጊዜው ሳይረፍድብህ
  ለቅዘን ያለው ቂጥ ምንግዜም ላይጠራ
  በአንኳኪ ብዛት ሰላም ከምታጣ
  በርህን ክፈተው ያሻው ይግባ ይውጣ…

 6. በለው! says:

  ኢናሳ የኢትዮጵያ ቆላፊ፤ መረጃ ጠላፊ አስጠላፊ፤ ቀበኛ የጓዳ አይጥ ቀፋፊ ፤ ቀንህ ደርሶ ሳትመታ በጥፊ ፤ ክፈት ብለናል በሩን ፤ የሕዝቡን ልሳን የዘጋኸውን ፤ አቁም ፍራቻን መደናበርክን፤ መርጠን እኮ ነው መከባበሩን፤ መች ጠፋን እና ሰበሮ መገባትን፤ ያሻው ይውጣ ይግባ ይተያይ ፊቱን፤ ቁልፍ እና ሰነሰለት የማይበግረን፤ ሲንኳኳ ተሸበርክ እንኳንም ከፍተን፤ ልብ ካለህ ክፈትና ግጠመን፤ ሰሚ ብናገኝ ተው በለው! አልን።

 7. በለው! says:

  ኢናሳ የኢትዮጵያ ቆላፊ፤ መረጃ ጠላፊ አስጠላፊ፤ ቀበኛ የጓዳ አይጥ ቀፋፊ ፤ ቀንህ ደርሶ ሳትመታ በጥፊ ፤ ክፈት ብለናል በሩን ፤ የሕዝቡን ልሳን የዘጋኸውን ፤ አቁም ፍራቻን መደናበርክን፤ መርጠን እኮ ነው መከባበሩን፤ መች ጠፋን እና ሰበሮ መገባትን፤ ያሻው ይውጣ ይግባ ይተያይ ፊቱን፤ ቁልፍ እና ሰነሰለት የማይበግረን፤ ሲንኳኳ ተሸበርክ እንኳንም ከፍተን፤ ልብ ካለህ ክፈትና ግጠመን፤ ሰሚ ብናገኝ ተው በለው! አልን።

 8. mimi says:

  መንግሥት ቤቱን ዝግቶ ብቻውን ይብላል
  አበው ተናግረዋል ብቻዉን ይሞታል

 9. selam says:

  እኔስ እገባልሁ በተገኘው ቦታ አሁንስ ይበርግግ ሲሰማ ኮሽታ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s