ሰሞኑን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከነ አንዷለም አራጌ ጋር በተያያዘ ባወጣው ዘገባ ምክንያት አቃቤ ህግ “በፍርድ ሂደቱ ላያ ጣልቃ ገብተሀል” በሚል ፍርድ ቤት እንዳቀረበው ይታወሳል። (በቅርቡ አይደል እንዴ… እንዴት ይረሳል…? ብለው ይከተሉኝ) ያንን ወሬ ባቀበልኩዎ ግዜ ከዚህ በፊት ኢቲቪ አካልዳማ የተባለውን “ፊልም” ሲያቀርብ አቶ አንዷለም አራጌ “ኢቲቪ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ ገብቷል” ብለው ቢከሱ የሚሰማቸው እንዳላገኙ አውርተን ነበር። በነገራችን ላይ አቶ አንዷለም በወቅቱ የኢቲቪን አኪልዳማ በከሰሱ በነጋታው ፊልሙ በህዝብ ጥያቄ ተብሎ ተደግሟል። (በወቅቱ እኔም በሆዴ በብሽሽቅ እኮ መንግስቴን የሚችለው የለም። ብዬ አድንቄ ነበር።)
ትላንት ማታ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳወራው ደግሞ የአኪልዳማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ እና ኢቲቪ፤ አንድነት ፓርቲ በከሰሳቸው መሰረት ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሆነ ነግሮናል።
ዜናው በዚህ አበቃ ቀጥሎ የኔ አስተያየት ይቀርባል። አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ…
እኔ የምለው ወዳጄ ፍርድ ቤቱ በኮመዲያኖች ቁጥጥር ስር ውሏል እንዴ? ብዬ ልጠይቅ ነበር አጓጉል መዳፈር ይሆንብኛል ብዬ ትቼዋለሁ። ነገር ግን፤ አቶ አንዷለም አራጌ በአኪልዳማ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ ስንት ግዜያቸው? ያኔ እርሰቸው አቤቱታውን ሲያቀርቡ የተሰጣቸው ምላሽ ወደር የለሽ ድብደባ እና “ምን ታመጣለህ!” በሚመስል መልኩ ፊልሙን ደጋግሞ ማሳየት ነበር።
በዚህ የተነሳ በርካቶች “የተከበረውን ፍርድ ቤት” የተቀበረ ብለውታል ምን እርሱ ብቻ ብዙ ምድራዊ ስድቦችን እና ርግማኖችንም አውርደውበታል።
ታድያ ዛሬ እነ ተመስገን ፍርድ ቤት በቀረቡ በነጋታው ኢቲቪም ተጠራ። ከዚህ ምን አንደምጠረጥር ልናገርማ…
ኢቲቪ ያደረገው ስህተት ፍርድ ቤቱ አላጣውም… ታድያ ያኔውኑ አቶ አንዷለም እንደከሰሱት ችሎት ላይ ሊያቆመው ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ፍርድ ከላይ ነውና “እነ ፍትህ ካልቀረቡ ኢቲቪም አይቀርብም ሲሉ የበላዮቹ አዘዙ… (መጠርጠር መብቴ ነው) ታድያ እነ ፍትህ ጋዜጣ በምን ስህተት ፍርድ ቤት ይቅረቡ? ሲፈለግ ሲፈለግ ይሄንን ያህል ግዜ ወሰደ። አሁን ገና በአቃቤ ህጉ አይን ፍትህ ጋዜጣ ላይ ስህተት የሚመስል ነገር ተገኘ። ከዛስ… ከዛማ በል ኢቲቪ አሁን አንተም ና… ተባለ። ይሄ ልጅነቴን አስታውሰኛል…
ልብስህን ቀይር…. እርሱ ካልቀየረ አልቀይርም።
ትምህርት ቤት ሂድ … እርሱ ካልሄደ አልሄድም።
ፍርድ ቤት ቅረቡ እነሱ ካልቀረቡ አንቀርብም….! (አይ ጉልቤ መሆን ደጉ)
እኔ ደንቆኛል… እርስዎስ…?
Negativity!! I hate it.
በራሳቸው ጊዜ ጣጣ ውስጥ ገቡ፡፡ አሁን የሚሰጠውን ፍርድ ማየት ነው!! ምክንያቱም ተመስገንም ኢቴቪም የተከሰሱበት ፍርድ ተመሳሳይ ነው፡፡
ke 13 amet belayim hone betachi yale sew liyayew yemayigeba film lol
ወይ ትይአትር አሉ።
ቀለዱ፤ ሰው በሃገር በህዝብ ሃብት እንዲህ ይቀልዳል፤ በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን????
ማሰብ በተሳናቸው ውሸትና ማጭበርበር ብቻ የተካኑ ነገሮችን ከሩቅ አስቦ ማቀድና መፈጸም በማይችሉ ድውያን የተሞላ መንግስት!!!!!!!
Don’t mix up the Temsgen and ETV are not charged by the same case and the issue are totally different.
አሁን የተካሳሾቻችን ቁጥር ተበራከተ። የጠ/ሚ ቴሌቪዥን “አኬልዳማ” ወይንም ” የውሸትዳማ” በተከሳሾች ላይ በዓቃቢ ሕጉ በፍርድ ቤትም ሆነ በፓረላማ ( በውሸት ማማ) በቀረበ ጊዜ የሰጠነው አስተያየት”በፅሑፍም ይሁን በቃል ያቀረባችሁት ክሰ እና የመስለቅርፅ ማስረጃ አይገናኙም በማስረጃነት ሊቀርብ አይገባውም ብለን ነበር ! ” ይህንኑም አስመልክተው አቶ አነዱዓለም አራጌ ኢቲቪ ሥም እና ክብሬን ነክቷል ሲሉ ቃላቸውን አሰሙ። በዕለቱ በችሎቱ የተየሙት ዳኛ “በኢቲቪ የተላለፈው ‘አኬልዳማ’ የተስኘው ድራማ ለሕዝብ የተላለፈው ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለሕዘብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንጂ በዚህ መዘገብ ለቀረበው ክስ ለማስረጃነት አያገለግልም ተያያዥነት የለውም ብለዋል። እኛም በበኩላችን ሕዝብን የሚያሸብረው እራሱ የወያኔ መንግስት ነው።ስለዚህ እዚህ ወንጀል ውስጥ አልተሳተፉም ብላችሁ ዳኛው ከመሰከረ ሌላ አማራጭ ተመሳሳይ ክስ ከማፈላለጋችሁ በፊት (ሀ) ክሱ በጠቅላላው መውደቅ አለበት (ለ) ተጠርጣሪዎች ለሀገር እና ለሕዘብ የሚያሰጉ አደሉም ከእስር ውጪ ሆነው ጉዳያቸውን የመከታተል የዋስ መብታቸው መጠበቅ አለበት!!።ወያኔ ከመመስረቱ በፊት ፤ባንዳዎችም ሳይወለዱ፤ ወይንም ካድሬዎቻቸሁ በሶሺያሊስት ርዮተ ዓለም ከመጠመቃቸው በፊት ኢትዮጵያ ህግ ያላት ሀገር ናት ትውልዱን አታጭበርብሩ፣ አታወናበዱ፣ አትቀሳፍቱ፣አታሸብሩ!! አሁን ፍ/ቤቱ እራሱን ጠርቶ በአቶ ተመስገን ደስአለኝ መዝገብ ከሰሰ? ? በለው ! በለው ! በማስረጃነት ያልተቀበለውን የቲቪ ፕሮግራም ለምን ትችት ቀረበበት ካለ የፍትህ ሳምንት ሳይሆን “የፍትህ የእንግልት ዓመታት” ተብሎ መሰየም አለበት። “በፍርድ ሥርዓት ጣልቃ በመገባት” ? ? አቶ ተመስገን ደስአለኝ በፍርድ ቤት የትኛው መቀመጫ ላይ ተቀምጠው ነበር? ? ? የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆነው ዳኝነትም ደርበው ከሰሩ የተከሰሱት ከአቶ መልስ ጋር የሥልጣን ሽሚያ(መጋፋት) (በሕዝብ ያገኙትን ኮንትራት በመቀናቀን) (ፍትህ የሚለውን ቃል ከሕገ መንግስቱ ላይ በመውሰዳቸው)(ለሕዳሴው ትጋት ባለማሳየታቸው)(በቀጥታ ሳይሆን በጨርፍታ በመወረፋቸው)(ሳያጨበጭቡ ሁል ጊዜ ጉንጫቸውን ደግፈው ምድረ አውረቶ አደርን በመታዘባቸው ) (ግባ፤ ውጣ ፤ዝጋ፤ አልተመቻቸውም) ለሁሉም ትዘብት! ከሀገረ ካናዳ እ>>>ን>>>>ቢ>>>>>ኝ>>>>በ>>>>>ለ>>>>ው!>>>በቸር ይግጠመን ።
LIKE
እኔንም በጣምም……………….ነው የገረመኝ!!!!!!! አቤ
ጋዜጠኛውን ግን ልብ ብላችሁ አይታችሁታል video የታየ ጊዜ ፡ ኢትዮጲያዊ አይመስልም ።