የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ “በአንዷለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋ እና ናትናኤል መኮንን ላይ ያቀረብከው ፅሁፍ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ መግባት ነው” ሲል አቃቤ ህግ በከሰሰው መሰረት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።

ልደታ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ምድብ ችሎት ዛሬ ጠዋት የተከሰሰበትን እንዲያስረዳ ቀርቦ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን በችሎቱ በተገኘበት ወቅት ከተጠበቀው በላይ ሰው በመምጣቱ ችሎቱ ሰፋ ወዳለ አዳራሽ እንዲቀየር ተደርጓል።፡

ተመስገን መከላከያውን በኮምፒውተር ታይፕ አድርጎ ቢያቀርብም “ጥቅጥቅ ያለ ፅሑፍ በመሆኑ አይነበብም እና አስተካክለህ ተመለስ” ተብሎ ለከሰዓት በኋላ ተቀጥሯል። እንደ ምንጬ ገለፃ ከሆነ ተመስገን ፅሑፉ አይነበብም ባሉት ግዜ “እኔ ይነበብልኛል ላንብብላችሁ” ብሎ ፍርድ ቤቱን በትህትና ጠይቆ ነበር። ነገር ግን የተመስገን “ላግዛችሁ” ጥያቄ ውድቅ ሆኗል።

በፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ላይ የቀረበበት ክስ እንደሚለው ከሆነ  በፍርድ ቤት የተያዘ ነገር ላይ ጣልቃ ገብቶ ዘገባ ማቅረብ “ነውር” መሆኑን፤ የሚያስጠይቅም እንደሆነ ያትታል።

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይህንኑ በፍርድ ቤት የተያዘ የእነ አቶ አንዷለም አራጌ ጉዳይ ላይ “አኬልዳማ” የሚል ፊልም ሰርቶ “አሸባሪ” እያለ ሲፈርጃቸው እንደነበር ይታወቃል። እርሱ ብቻም አይደለም፤ አቶ አንዷለም አራጌ፤ “ይህ ጉዳይ በህግ አግባብ ትክክል ባለመሆኑ የፍርድ ሂደቱ ሳያልቅ እንደ ወንጀለኛ የቆጠረን ኢቲቪ ይጠየቅልን” ብለው አመልክተው እንደነበረም ይታወቃል። አሁንም ይህ ብቻ አይደለም፤ ኢቲቪን ማንም ፍርድ ቤት እንዳላቀረበውም ይታወቃል። (የማይታወቅ ከሆነም አሁን ይታወቅ)

በመጨረሻም 1

የፍትህ ሳምንት ክብረ በዓል ከዛሬ ጀመሮ ለአንድ ሳምንት እንደሚከበር ትላንት ነግሬያችኋለሁ። እንዳልኳችሁ በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓቱ በጣም ተሻሽሏል።

በመጨረሻም 2

ትላንት ተመስገን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ እንዳወጋን ፍትህ ለህትመት በምትገባበት ቀን ዘወትር ሀሙስ መብራት ይጠፋል። እንደ ተሜ ገለፃ “መብራቱን ማን እንደሚያጠፋው ከፈጣሪ በስተቀር የሚያው የለም።” እንደኔ ጥርጣሬ ደግሞ ባልቦላውን የሚመልሰው የኤልፓ ሰራተኛ እና አለቃውም እንደሚያውቁ እገምታለሁ።

እዝችው ላይ ይህንኑ አጋጣሚ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በምጫጭርበት ወቅትም አስታውሳለሁ። ብዙውን ግዜ አውራምቦች አርብ አርብ “መብራት ተረኛ ነበሩ” ይሄ ነገር ቢሮ በቀያየሩ ቁጥር ሲከተላቸው እንደነበረም ትዝ ይለኛል። ያኔ በየዋህ ልቦና ነገሩ “የቤት ጣጣ” ይመስለኝ ነበር!

አሁን በአዲሳባ ገበያ ላይ “አርብ አርብ ይሸበራል ኢየሩሳሌም” ብላ በዕለተ ጁምአ ብቅ የምትለው ፍትህ ጋዜጣም በየ ሀሙሱ መብራት እየጠፋባት ተቸግራለች።  ባለፈው ሳምንት መብራቱን ያጠፋው ሰውዬ የህንፃውን በሙሉ ማጥፋት ሲገባው የፍትህን ለይቼ አጠፋለሁ ሲል ከፍትህ ዋና ቢሮ ጋር የማይገናኘውን የመፀዳጃ ቤቱን መብራት ስቶታል። በዚህም ምክንያት ፍትህ መፀዳጃ ቤት በር ላይ ታይታለች።

ይሄንን የቤት ጣጣ ማለት ከባድ ነው… “የመንግስት ጣጣ!” ሳይሆን አይቀርም!

አሽሙረኞችም ብለዋል “እነሆ ፍትህን ከመፀዳጃ  ቤት ደጃፍ የጣላችሁ እናንተ የፍትህ ሳምንትን ማክበር ይቻላችኋልን?”

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

6 responses »

 1. እን ደውም በጣም ተሻሽለዋል ማለት ነው መፀዳጃ ቤት ደጃፍ መጣላቸው ….በነገራችን ላይ ፍትህ ግን ያውቈአታል ? አለቻቸው … አዎ በጽሁፍ ያልችውን ይሆናል !!!
  እውነትም ስላቅ !!!

 2. Kulich says:

  Temesgen Desalegn, editor-in-chief of Fitih- ፍትህ newspaper wrote the following on his paper:

  “የዚህ ‘ስም አጥፊ ግንባር’ ዓላማ አንድ እና አንድ ነው። ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ነች ብሎ ማሳመን። እኔ በግሌ እንደጋዜጣው ዋና አዘጋጅነቴ የዚህ ግንባር ሽለላ እና ቀረርቶ ብዙም አያሳስበኝም። የእነሱ “አሸባሪ የሚል ውንጀላም እንዲሁ ከግምት አላስገባውም። ምክንያቱም እነርሱ “አሸባሪ” ሲሉ እና ሌላው ዓለም “አሸባሪ” ሲል ለየቅል ነውና። ዓለም አሸባሪ የሚለው ለሰላማዊ ዜጎች እና ሕዝባዊ ተቋማት አስጊ የኾኑትን ነው። እነ አቶ ሽመልስ ደግሞ አሸባሪ የሚሉት ለአገር ጥቅም እና ለሕገ መንግሥታዊ መብት የሚታገሉትን ነው። ለዚህም ነው አሸባሪነት እንዲህ ከኾነማ፤ አዎ እስክንድር ነጋ እና ርዕዮት ዓለሙ ብቻ ሳይኾኑ እኔም አሸባሪ ነኝ ያልኩት።
  አዎን የመጻፍ ነጻነት ይከበር፤ ኑሮ ተወደደ፤ ገዥው ፓርቲ በሙስና ተዘፈቀ፤ አገሪቱ ላይ የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ነገሠ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠበበ . . . ብሎ መጻፍም ኾነ መጠየቅ አሸባሪ የሚያስብል ከኾነ “አዎን እኔም አሸባሪ ነኝ!” እደግመዋለኹ “አዎን፤ አሸባሪ ነኝ!”
  በመቀሌ ገረቡቡ የሕወሓት አመራሮች የአፓርታኢድ መንደር መሠረቱ፤ በሙስና ከአገር ተዘርፎ የተደበቀ 8.4 ቢልዮን ዶላር ተገኘ፤ ከስድስት ሚልዮን በላይ የሚኾን ሕዝብ ተርቧል፤ ድህነት እና ሥራ አጥነት ከአቅማችን በላይ ኮኗል፣ ግብር በዛብን የዜግነት መብታችን ተገፈፈ፤ . . .ማለት “አሸባሪ” የሚያስብል ከኾነ አዎ ፍትህ እና ባልደረቦቿም “አሸባሪዎች” ናቸው።”

  I am sure Temesgen will be repeating this in court today. I have great respect for this man. He is a real hero who fights for freedom of speech in woyane’ Ethiopia. According to police chief Werkineh’s assertion, the justice system in Ethiopia has shown improvement. If that is so, why cannot the Federal High Court call out Meles Zenawi who openly declared in parliament that all the jailed journalists and opposition political party leaders are guilty as charged? How can these defendants receive fair trial if Meles already concluded that they are guilty?

 3. soliana says:

  Ere ahunes beza wediyeaaa.they are tracking each and every little thing starting from hacking individual’s f.b account ad email to killing people.

 4. Ayalom says:

  We shall win! Justice shall prevail!

  • Abraha Desta says:

   Hope, Temesgen will continue to provide us his nice political critic and analysis regardless of the suppressive attempts.

 5. በለው! says:

  በከሳሽ ጠቅላይ ሚ/ር መልስ ዜናዊ .. በተከሳሽ ተመስገን ደስ አለኝ መካከል ያለው የክስ መዝገብ በመጀመሪያ የቀረበው በፓርላማ ነበር ፤ከሳሽ በሙሉ ድምፅ በጭብጨባ አሸንፍዋል።
  “በፍርድ ሂደት ጣልቃ መግባት” ተመስገን ያለው” በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ዋሉ ማለት ወንጀለኛነታቸው ተረጋግጦ የተፈረደባቸው ማለት አደለም ነው” ጠ/ሚ ዓቃቢ ሕግ ሆነው “በግለሰቦቹ ላይ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለኝ ሲሉ አስረድተዋል” ችገሩ ይህ የክስ መዝገብ እንዴት ጠ/ሚ ቢሮ ደረሰ? ጠ/ሚ የከፍተኛው ፍ/ ቤት ፕሬዘዳንትም ሆነው በ6200 የኢ.ብር ለማገልገል ቁርጠኝነታቸው አሳሳቢ ነው ።እሳቸው ሰፈር የደሞዝ ማስተካከያ የለም? ? በጣም የገረመኝ የተመስገን ደስአለኝን ጥቅጥቅ ያለ ፅሑፍ አላነብም አንተም በማንበብ አትረዳኝም ያለው ዳኛ በጣም ብልጥ ነው። “አቅምን አውቆ መኖር ታላቅ ችሎታ ነው” ያለው ማን ነበር? እርግጠኛ ነኝ አንባቢ ተገኝቶ፤ ተተርጉሞ፤ ተጠንቶ ፤ተመክሮበት እስኪገባቸው ክረምት ገበቶ ያልወጣ እንደሁ ታዘቡኝ! ኢህዴግ የሕግ አራት ነጥብ ብቻ ሳይሆን ካድሬዎቻቸው የተመስገን ደስአለኝን አርዕስት እንኳን ከመኮረጅ አልቦዘኑም “የጋዜጣ አምደኞችን በጨረፍታ” ድንቄም አልቀረባችሁም በለው!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s