ያው እንደሚታወቀው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፍቅር ከወደቅሁኝ ቆይቻለሁ። ስለዚህ ነጋ ጠባ ኢቲቪን ብጠቅስብዎ አየሰልቹ።

ዛሬም “ቸር ያሳደርከኝ ቸር አውለኝ፣ ከተናግሮ አናጋሪ አገናኘኝ” ብዬ ፀሎት ካደረስኩ በኋላ መጀመሪያ ያገኘሁትት የኢቲቪ ዜና አንባቢን ነበር። ባትሰማኝም “ደህና አደርሽ እግዚአብሄር ይመስገን” ብዬ ተቀበልኳት። እርሷም ዜናዋን ቀጠለች።

“የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ ሊከበር መሆኑ ተገለጠ…” አለችኝ። እውነትሽን ነው? ፍትህ …ፍትህ… ፍትህ የቱ…? ብላት ግዜ  “አቶ ወርቅነህ ገበየሁ እንደገለጡት ከሆነ የፍትህ ስርአቱ በሀገራችን እየተሻሻለ መጥቷል።” ስትል ጨመረችልኝ። እሰይ ከተናግሮ አናጋሪ አገናኘኝ ብዬው አይደል? እንዲህ ነው እንጂ ጌታዬ ተመስገን በማለት የፍትህ ስርዓቱን በረከቶች እንዳመጣልኝ መቁጠር ጀመርኩ።

አንድ

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ልጅ “ፍትህ ውብሸት” ይባላል። አራት አመት ቢሞላው ነው። አባቱ “አሸባርከን” ተብሎ ታስሯል። ውብሸት በታሰረበት ወቅት አቶ ዘላለም፣ ሂሩት ክፍሌ እና ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙም አብረው ታስረዋል።

እናም በተሻሻለው የፍትህ ስርዓት መሰረት አስራ ምናምን አመት እስር እንዲሁም፤ የቦንድ መግዣ ከሰላሳ አምስት እስከ ሃምሳ ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል። ታድያ በቅርቡ ምን ሰማሁ መሰላችሁ።  ለነዚህ ወዳጆቻችን መፅሀፍ  ወደ ቃሊቲ ብትልኩላቸው፤ ከመግባቱ በፊት ለዚሁ ስራ የተመደበ ሰው “ሙልጭ አድርጎ” ያነበዋል። ከዛም በውስጡ ምንም ክፉ ቃል አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ ያሳልፍላቸዋል። እንዲህ ነው እንጂ የፍትህ ስርዓት መሻሻል ብለው ይከተሉኝ። (እዚህ ላይ ርዮት አለሙ ጡቷ አካባቢ እየተሰማት ላለው ህመም ህክምና  ጠይቃ “ፓራሲታሞል ይበቃሻል” ተብላ በህመም ስትሰቃይ “አረ የፍትህ ያለ” እያለች ጆሮ ዳባ ተብላ እንደነበር ማንሳት እችላለሁ። ነገር  ግን ገና በቁጥር አንድ እንዲህ ያለ ሀዘን አላሰማዎትም ብዬ ነው)

ሁለት

ወጣቱ ፖለቲከኛ ናትናኤል “አሸባሪ” ተብሎ ከታሰረ በኋላ በምርመራ ላይ የደረሰበትን ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ ነበር።

ርቃኑን በማድረግ እጁን ወደላይ አስረው ቀዝቃዛ ውሃ በላዩ ላይ እየተቸለሰበት ለሶስት ቀናት  ምግብ ተከልክሎ መከራውን ሲያይ እንደከረመ። ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ምን አለው… “እንደው ከጀመርክ እናስጨርስህ ብለን እንጂ እኛ ይሄንን ልንሰማ አልተሰየምንም” ብሎት እርፍ። ፍክንያቱም የፍትህ ስርዓቱ ተሻሽሏላ።

ሶስት

አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ መታሰሪያ ቤት ታስሮ የከሳሾቹን ፍርድ እየተጠባበቀ ይገኛል። በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ፍረደኛ ሰው ፍርዱን ከሚጠባበቅ ሰው ጋር አይቀላቀልም።

ለእነ አንዷለም አራጌ ሲሆን ግን የፍትህ ስርዓቱ ይሻሻላል። በዚህም መሰረት በአደገኛ ወንጀል አደገኛ ፍርድ የተፈረደበት አደገኛ ሰው እነ አንዷለምን ተቀላቀላቸው። ከተቀላቀለም በኋላ አደገኛ በሆነ መልኩ አቶ አንዷለምን ደበደው። የፍርድ ቤቱ ምላሽ ምን እንደሆነ አልሰማንም! “የፍትህ ስርዓቱ መሻሻል ውጤት ነው” መባሉ ግን አይቀርም።

አራት

ዜና አንባቢቱ እንደነገረችኝ ከሆነ “የፍትህ ስርዓቱ ተሻሽሏል” ብለው የተናገሩት የፌደራል ፖሊሱ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው። እኒህን ሰው በምን መሰላችሁ የማስታውሳቸው…? ያኔ ገና መንግስት፤ “ሽብርተኝነት ሽብርተኝነት” መጫወት ከመጀመሩ በፊት እስክንድር ነጋን ቢሯቸው ድረስ በፖሊሶች አሳግተው ወሰደውት ነበር። ልብ አድርጉልኝ ፖሊሶቹ መጥሪያ ወረቀት እንኳ አልያዙም። እንኳንስ ወረቀት ለመጥሪያ የሚሆን ፉጨትም አላፏጩለትም። እስክንድር ሀገር ሰላም ብሎ ቁጭ ካለበት ኢንተርኔት ካፌ መጡ አንጠልጥለው ሜክሲኮ አደባባይ ከሚገኘው አቶ ወርቅነህ ቢሮ ወሰዱት። ታድያ እርሳቸው ምን ቢሉት ጥሩ ነው…?

“በዘጠና ሰባቱ ምርጫ የደሀ ልጅ ተገድሏል። አሁን ግን የደሀ ልጅ አይገደልም። አንድ ነገር ኮሽ ቢል መጀመሪያ ርምጃ የሚወሰደው አንተ ላይ ነው። እርምጃው እስር እንዳይመስልህ እንደፋሀለን” አላሉትም መሰላችሁ! አይገረሙ ይሄ የፍትህ ስርአቱ መሻሻል መገለጫ ነው።

እንግዲህ ሰሞኑ የፍትህ ሳምንት በኢትዮጵያ የሚከበርበት ሰሞን ነው።  ልብ አድርጉ የሚቀበርበት አይደለም ቀብሩ ትንሽ ቆይቷል። እናም መልካም የፍትህ ሳምንት ልመኝልዎት። እንዲህ ነው እንጂ ስላቅ አይሉኝም!

በመጨረሻም

ትላንት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ስለ ኑሮ ውድነቱ በአንዲት ወይዘሮ የፓርላማ አባል የተጠየቁ ግዜ፤ የዋጋ ግሽበቱን ከሚያባባብሱት ነገሮች መካከል የአለም ነዳጅ ዋጋ መጨመር እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። ከዚህ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባል “የነዳጅ ድጎማ ለምን ቀረ?” ተብለው ሲጠየቁ “እኔ እስከማውቀው ድረስ ሰማንያ አምስት በመቶ የሚሆነው ህዝብ በእግሩ ነው የሚሄደው። ነዳጅ የሚጠቀሙት ሀብታሞች ናቸው ስለዚህ የነዳጅ ዋጋ በገበያው ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል ብዬ አላምንም። ስለማላምንም አልደጉምም” በማለት ተናግረው ነበር።

እኔ የምለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ የስራ ማስታወቂያ ማውጣት ያለባቸው አይመስላችሁም? ምን አይነት በሉኝማ…  የስራ መደቡ መጠሪያ “አምና የተናገሩትን  ዘንድሮ አስታዋሽ።” ልዩ ችሎታ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ አቤት ውሸት ብሎ የማይሳቀቅ!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

9 responses »

 1. yosef says:

  i know there is no justice in ethiopia

 2. Waldiba says:

  Emnetachin ena maninetachin eyetefa yemin fithihi newu…..

 3. elias says:

  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ አቤት ውሸት ብሎ የማይሳቀቅ! Thanks for this !!!

 4. boss says:

  he must be the other yosef..he wright his name on amharic,”yosef” behone noroma yhene besak fendeten neber!! he must publish those commentes in title “YE YOSEFE COMENTOCH BE ABE SHUMUTOCH” andega neber migezaw i hope demo,ende tedy tkur sew album ADDICA sponsor yader gew neber.yosi arif hsab new aydel?bel commentochihen sebseb!! YOSEF LEZELALEM KEBLOGACHIN LAY YNUR!!
  AMEN,AMEN AMEN.

 5. boss says:

  ere resechaw.. abe… .ethiopiawest ye web gedeb ketegemere gemero ene
  tegedebobegn a yawekem…endet malet tiru….mert unblocker yemibalu proxy wesitoch alu ene azewetre yemetekemebeten 1,2 tun lengerh..en AA lalew guwadegnah asmokerew..www.webevade.com,www.phproxysite.com,www.netunlocker.com,beka enezih west gebto yetegedeben web mtsaf keza hulum wellel blo yekefeta.,chek it out.BEKA GIDEB BEKA beleh andeken ashmuatebet.[u can have over 150 unblock-er webs}

 6. ዳግማዊ says:

  አቶ ወርቅነህን ጠንቀቅ ማለት ተገቢ ነው፣ የተናገሩትን የመፈፀም የዕብደት መብት አላቸው፡፡ ከ1967 ጀምሮ የታገሉት እነ አቶ ስየ ተፈንግለው ከ1983 በኋላ የታገሉት አቶ ወርቅነህ የደላቸው በዋዛ ፈዛዛ አይደለም፡፡

 7. TADEY says:

  no justice ETHIOPIA

 8. በለው! says:

  “የፍቺ ሳምንት” በኢትዮጵያ ሊከበር ነው፤ መቼም ተጋቡ ውለዱ፤ ክበዱ፤ ለክርስትና እንመጣለን ገና ይባል ነበር አሉ ድሮ…… ዛሬ ከማዘጋጃ ቤት መልስ ፍቺው ቀልጧል በጅምላ ማፋታቱ ለቁጠባ ያመቻል ተብሎ ነው ገቢው ለግደቡ ይሆናል!!! ስለፍትህ ነገር ያላቸሁት ስላልገባኝ ነው ፡ በአዲስ አበባ ከፍተኛው ፍ/ቤት የቀረበን የዐቃቢ ሕግ የክስ ማመልከቻ ያነበበ ወይንም ለማንበብ ፍቃደኛ የሆነ ግን ማንበብ ያቃተው ወይንም ለማንበብ ሞክሮ ዕድሉን ያላገኘ ወይንም ክሱ ከተመሠረተበት ጊዜ አንሰቶ ቢያነበውም ያልገባው ወይንም አሁንም እያነበበ ሆኖ ጭብጡ ያልተያዘለት ወይንም የቋንቋ ችሎታ ማነስ መስሎት ስማ በለው ሲያፈላልግ የከረመ ወይንም የጉዳዩ ውስብስብነት እና የሕጉ ዘመናዊነት ያስደመመው ወይንም የሕግ የበላይነት እያለ ቱሪናፋውን የሚለቅ አሽቃባጭ ወይንም ሕግን እንደ ፖለቲካ አጀንዳ ያነበበ ያስነበበ የተረጎመ ወይንም ሲፈረድበት እና ሲፈረድበት ያልገባው እንዲው በደፈናው በድን ነው የፍትህ ሳምንት ሳይሆን የፍትሃት ሳሕታት ያስፍልገዋል በለው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s