ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ብቸኛው የተቀናቃኝ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተውላቸው ነበር።

ከጥያቄዎቹ መካከልም ስለ ፖለቲካ ምህዳሩ፤

ፓርቲያቸው በይፋ ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ኢቲቪ የቀረፀውን ዋቢ በማድረግ “በህቡዕ በማሴር” ተብለው አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ተከሰውበት እስር ቤት መግባታቸውን፣

ስብሰባ ለማድረግ አዳራሽ አከራዮች “ለሰርግ ካልሆነ በስተቀረ አታከራዩ ተብለናል” በሚል  ስለመከልከላቸው።

እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ደግሞ፤

ከደቡብ ክልል ስለተፈናቀሉ ዜጎች “የክልሉ ፕረዘዳንት “አንድም ሰው አልተፈናቀለም” ብለው ተናግረዋል። በአይናችን ያየናቸው እርስዎ ፅ/ቤት አቤት ለማለት መጥተው ፀሀይ ተንቃቅተው በኋላም በመኪና ተጭነው የተወሰዱ ዜጎች “አንድም ሰው” አይደሉም ወይ?” ያሏቸው ሲሆን፤

ከደምወዝ ጋር በተያያዘ “መምህራን ተቃውሞ ሲያሰሙ ገሚሱ ከስራ ታግዷል ገሚሱ ማስፈራሪያ ደርሶበታል። እንደዚህ አይነት “ሆድ የባሰው” መምህር ይዘን ስለ ትምህርት ጥራት ማውራት እንችላለን ወይ?”

የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቀዋለው።፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም አብዛኛዎቹን የአቶ ግርማ ሰይፉን ጥያቄዎች በመላ በመላ አልፈዋቸዋል። (የእድሜ እና የስልጣን እኩያዬ ቢሆኑ ኖሮ አጭበርብረው አልፈዋቸዋል እል ነበር)

መምህራኑን በሚመለከት በሰጡት ምላሽ ግን “የማስተማር ስራው በተቋረጠ ወቅት ከወላጆች እና ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገን ነበር። “በዛን ግዜም መምህራኑ ቀድሞውንም እንዲባረሩልን አቤት ስንል ነበር” የሚል አስተያየት ከወላጆች እና ተማሪዎች አግኝተናል።” ብለዋል። በዚሀም አላበቁም “እነዚህ ከአምስት መቶ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱት መምህራን በመምህርነት አልሳካ ሲላቸው ሌላ አማራጭ ለመሞከር ያሰቡ ናቸው” ሲሉ አብጠልጥለዋቸዋል።

በዚህም አንዳንድ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህራን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ጠብቀን ማረሪያ አግኝተናል ብለዋል።

በነገራችን ላይ (አዲስ ነገር ጋዜጣ ናፈቀችኝ መስፍኔ በሚፅፋቸው ፅሁፎች ጣልቃ አነስ ያለች “በነገራችን ላይ” የምትል የጨዋታ “ቦነስ” ነበረችው። ሰላም መስፍኔ! ሰላም አዲስ ነገሮች)

ስቀጥልም በነገራችን ላይ

የመምህራኑ ጥያቄ ባለፉት ግዚያት በተደጋጋሚ እንደገፁልን የኢቲቪ የተጋነነ ዘገባ እንጂ የደሞዝ ማሻሻያው አነሰ አላነሰ አይደለም። ኢቲቪ ሆዬ “መምህራኑ ህይወታቸውን የሚቀይር ገንዘብ ተጨመረላቸው” ብሎ በዘገበ በነጋታው አካራዮች አከርካሪ የሚሰብር ጭማሪ አደረጉብን እናም ዘገባው ይስተካከል ነው ያሉት። ካላመናችሁኝ ድጋሚ አንዱን የአዲሳባ ወይም የአማራ ክልል መምህር ጠይቁት።

በመጨረሻም 1

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው የፓርላማ ስብሰባቸው በማሳቁ በኩል ብዙም አልተሳካላቸውም። በዚህም ሳቅ ጨዋታ ጠብቀው የሄዱ የፓርላማ አባላት እጅጉን ተከፍተዋል አሉ። እንደውም አንዳንዶች “ካላሳቁ ይልቀቁ” ሲሉ አጉረምርመዋል ሲል ታማኝ ያልሆነ ምንጭ ሹክ ብሎኛል። እዝችው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሶማሊያ ሲናገሩ “እኛ ሶማሊያ  እንደገባን የሶማሊያ ህዝብ ጫት መቃም ጀምሯል።” በማለት በኩራት ሲናገሩ የሰማ አንድ ወዳጃችን “እንዴት ነው ነገሩ ለማቃቃም ነበር እንዴ የሄዳችሁት?” ሲል የማይመለስ ጥያቄ ጠይቋል።

በመጨረሻም 2

“የግድብ ስራው ተቋረጠ” በሚል አጭር መረጃ አድርሻችሁ ነበር። እኔማ “እስቲ አንዳንዴ እንኳ ጥሩ ወሬ አውራ መንግስታችንን አመስግንልን” ለሚሉ ወዳጆች ጥሩ አጋጣሚ አገኘሁ ብዬ ተደስቼ ነበር። ምን ዋጋ አለው ዌብ ሳይቶቹ ለሶስት ቀናት ተከፍተው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ደግመው ተከርችመዋል። አሉ! በቀደመው ጨዋታዬ ላይ

“…ስለ ኢትዮጵያ የሚያወሩ ድረ ገፆች እንደ ምንጬ አባባል “ፏ” ብለው ይታዩ ነበር። እንዴት ነው ነገሩ መንግስት ተቀየረ… ወይስ ዌብሳይቶችን ሲገድብ የነበረው ሰውዬ ደህና አይደለም?    እነዚህን ጥያቄዎች እርሱ ባለቤቱ ይመልሳቸው።” ብዬ ነበር?

አዎ መልሱን እርሱ ባለቤቱ መልሶልናል። ለሶስት ቀናት ድረ ገፆቹ “ፏ” ብለው የመታየታቸው ምስጢር ገዳቢው ከአመት በዓል ጋር በተያያዘ ጥቂት ጉዳት ደርሶበት ስራውን በአግባቡ ባለመስራቱ ነበር። (ጉዳት የሚለውን ሞቅታ ብሎ መተርጎም አግባብ አይደለም) እናም እንደምንጠረጥረው ልክ  በአሁኑ ሰዓት በ”ኢንሳ” መስሪያቤት  “የዌብሳይት ግደባ እና ቁለፋ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት” የሆነው ግለሰብ በግምገማ ቁም ስቅሉን እያየ እንደሚሆን ይገመታል።

እኔ የምለው ግን ምናለ ምስጋናችን እንኳ ጠፈፍ እስኪል ጠብቃችሁ ብትቆልፉት!?

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

16 responses »

  1. ma says:

    Ya! that was by mistake! do not expect this from the evil meles!!!

  2. ዳግማዊ says:

    የአቶ መለስ ነገር አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሐፍ ቦጫጭቃ አጠበች ዓይነት ነው፣ አለመታደል የሚለው ማማረር ሊገልፀ የማይችል የመሪ ጉድለት አገሪቱን ጠፍንጎ ይዟታል፡፡

  3. Awol says:

    Yehagrune Zaga lemanagre yeteteyefe teklay minster.yigrmal

  4. SAMI says:

    Ethiopia will continue to suffer from the extreme poverty thanks to woyanne, as long as woyanne is gripping on power. Woyane must go! the Ethiopian public’s suffering has to come to an end! Let us all stand against woyanne in union!

  5. Abay says:

    እንደዚህ ዓይነት የአህያ ፋንድያ ፅሑፍ የሚፅፍ ሰው ያስታውቅበታል አንድም ጠጆ ነው ወይም አረቂያም ነው::

  6. Tsinat says:

    @Abay (lalito Yenebeb) enede’enante gin chatam ayidelem

  7. samata says:

    yebeza almeselehim………… ante woregna …..

  8. BROOK says:

    le dedeb hezeb yemayegba best P/M

    • Hilina says:

      woyanewoch engdih endih new hizibun yeminikut ena yemisedibut, chika hizim bilew yele abunu??

    • viva Ethiopia says:

      I was just dropped in accidentally to this blog. I was also expecting a lot to learn from the comments. I dont want to say that but, most of the comments are amazing. It is true that there are a lot of problems in our country. But you people are blaming each other. If we really need to see true changes in Ethiopia, we should unite our selves; love each other. Free our selves from the infection of “ZEREGNET and TEBABNET”. We should stand together.

      Finally for EPRDF members like ato BROOK: What I want to say is that, personally you can support any political party or you can have your own point of view. But rather than revealing the real condition of the country and backing up with appropriate evidences, you prefer to insult the people. It showed that you are are not politicians but ur are recruited to pertained to be politicians. Because are moron, you have nothing to say rather than menacing. But at least try to read and explore what the people feel abut EPRDF. Then may be you can understand what is going on.

      Viva Ethiopia and Ethiopian-ism!!

  9. meretwork says:

    woyane evil meles you con not continue like this dirty mismanagement meles go meles go manem ayfelgehe baqa long live AMHARA !! long live ETHIOPIA!!woyane goooooo!

  10. Ananomus says:

    there are some ways to bypass the block and read the blogs and website you want if you are in ethiopia, for reasons you know, i will not give you the way but strongly advice you to search for a way. I have more than 2 at the moment.

  11. gebreslassie says:

    I am getting crazy by the hopless speech of the PM.

  12. በለው! says:

    ጠንቋይ/ሚኒስትር በፓርላማ ውሎአቸው “ሲቲንግ ዳውን ኮመዲ” ቀልደዋል የፓርላማ አባላት ጥጋብ ላይ ሥለሰነበቱ እንቅልፍ ላይ ነበሩ። የዋጋ ንረት ምንጩ(ሀ)የአለም ማዕድን እና ግብርና የገበያ ዋጋ መዋዠቅ (ለ) የኢሲያ ሕዝቦች ኑሮ መሻሻል ኢትዮጵያን የሚመለከታት ማዕድን(ነዳጅ) ነው።ለመሆኑ በቆሎ እና ስንዴ ነዳጅ መጠጣት ጀመረ?አሃ ! አሃ ! አሃ !!!!!!!!!!!!! ባልታወቀ መንገድ የእህል ውጤት ወደ ጎረቤት ሀገር መጓዝ? ? ?አይ የብሔር ብሔረሰቦች ሊቀመንበር ይህንን በዶ/ር ፈቃዱ በቀለ ጽሑፍ ላይ በደንብ አስቀምጬልዎት ነበር ሄደው ያንብቡ። ከዚህ በፊት አቤ እንዳለዎ ፌስ ቡክዎ ላይ አድ ቢያደርጉት ከካድሬዎችዎ በበለጠ ብዙ ነገር እናማክርዎ ነበር። “አድሎ እና ሙሰና” መንግስት የሚታገለው በአንድ እጅ ነው ? ? ? ? ? ሁልጊዜም የሀጢያት ሥራ ሲስራ በድብቅ እና በአንድ እጅ ነው! (እናንት አመለኞች ታች ቤቶች አተረጓጎሙን አታበላሹ) አቶ መልስ ደህና ነዎት? ? ? “የኢትዮጵያ ሕዝቦች መንግሰት” ድሮስ የአላዋቂ ሳሚ “ብሔር ብሔረሰቦች” የት ሄዱ? ? ? ? ? መንግስት እና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው? ለመሆኑ ሕገ መንግስትዎ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም ይላል? ? ? >? እርስበረሳቸው ለሚጣረሱ (ለሚናቆሩ) ግን ይረዳል፤ ያበረታታል፤ ይደገፋል ፤ያሰለጥናል፤አሰልጣኝም ይልካል!!!!!! ለምሆኑ ህገ መንግስትዎ የመዘዋወር እና የመንቀሳቀስ መብትን እንዴት ይተረጉመዋል? ሕገ ወጥ ሰፈራ (ሞፈር ዘመት) በተለይ አማራ!! ክቡርነተዎ ተመስገን ደስአለኝ አማካሪዎችዎን በጨረፍታ ሲናግር እኔ ግን ሕገ መንገስትዎን በቀጥታ አልወደድኩልዎትም!!! ሰው ካልተማረ አምና ከአቻአምናው ፤ ችግር ሳያበዛ ዘንድሮ ለነገው ፤ ጅግና ተነስ እና እምቢኝ በቃ በለው!!!!!!

  13. seyfe says:

    ወሬነኛ ስራው ወሬ ነው። ኣደር በያም እንደዛው።
    አውሩ ግድየለም ወሬኛ ድሮም ነበረ አሁንም አለ ይኖራልም።
    ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጥ ሰው ሆኖ ወደ የስራው ለሚንቀሳቀስ የወሬኛ ሲሳይ መሆኑ ኣይቀርም። ይታወቃልም።
    የሚያናድደው ግን ይሄን የወሬኞች ብሎግ ሳላስበው መክፈቴ ነው።
    ወሬያቹ ወደ ስራ ወደ በጎ ኣድራጎት ወደፍቅር ስራ ይቀይርላችሁ!!!!

    ሰይፈ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s