ቆይ ቆይ አይደናገጡ! መጀመሪያ የቱ ግድብ? ብለው ይጠይቁ እንጂ፤ “ወይኔ ቦንዴ? ወይኔ ደሞዜ” ብለው ሀዘን አይግባዎ!
መንግስታችን አባይን ለመገደብ ከማሰቡም በፊት በትጋት ሲገድብ የነበረው ድረ ገፆችን፣ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ጣቢያዎችን እንደነበረ የታወቀ ነው። እንደውም አንዳንድ አሽሟጠጮች እንደሚሉት ከሆነ መንግስት ያለ ምንም ዕቅድ አባይን ልገድብ ብሎ የተነሳው፤ ድረ ገፅ እና ራዲዮ ጣቢያ በመገደብ ያዳበረውን ልምድ በመተማመን ነው ይሉታል።
ትላንት ዘላለም የተባለ የልብ ወዳጃችን በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ “ስጋትን ስለመግለፅ” ብሎ እንደለጠፈልን ከስቅለተ አርብ ጀምሮ ከዚህ በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ተገድበው የነበሩ ድረ ገፆች በሙሉ ተከፍተዋል። እኔም ይህንኑ ዜና እንዲያረጋግጥልኝ በጠየቅሁት ግዜ በመሃላ አረጋግጦልኛል።
አሁን በቅርቡ ይቺን የኔዋን ምስኪን ብሎግ ጨምሮ ሎሎችም ብሎጎች ለሳምንት ያህል ወደ ወደ አገር ቤት እንዳይገቡ ታግተው ሰንብተው ነበር። የዛኔም መንግስት የግድብ ስራውን እያጧጧፈ እንደሆነ ግንዛቤ ወስደናል። (“ግንዛቤ ወስደናል” አሪፍ የካድሬ ንግግር ናት ብዙ ግዜ በገንዘብ ከሚደረጉ ስብሰባዎች በኋላ የስብሰባው ተሳታፊዎች “ገንዘብ አግኝተናል” አይሉም ግንዛቤ አግኝተናል ነው የሚሉት።)
እውነትም ታድያ ከብሎጎቹ ቀጥሎ አብዝተው ዴሞክራሲን የሚሰብኩ የፌስ ቡክ ታጋዮችም ጭምር የግድቡ ሰለባ ሆነው ነበር። እኛም በያለንበት “ጨምሯል ግድብ ጨምሯል” እያልን ስናንጎራጉር ሰንብተናል።
አሁን ግን ይኸው ከስቅለተ አርብ ያነሳ ቢያንስ እስከ ሰኞ አመሻሹ ድረስ ከዚህ በፊት ታግደው የነበሩ ስለ ኢትዮጵያ የሚያወሩ ድረ ገፆች እንደ ምንጬ አባባል “ፏ” ብለው ይታዩ ነበር። እንዴት ነው ነገሩ መንግስት ተቀየረ ወይስ ዌብሳይቶችን ሲገድብ የነበረው ሰውዬ ደህና አይደለም? ወይስ መንግስት ተፀፀተ? እነዚህን ጥያቄዎች እርሱ ባለቤቱ ይመልሳቸው።
ነገሩ ግን በዚሁ ካዘለቀው በጣም ጥሩ ጅምር ነው። እግረ መንግድ ታድያ እነ እስክንድር ነጋ ውብሸት ታዬ እና ርዮት አለሙን የመሳሰሉ ጋዜጠኞች የተገደቡበት የቃሊቲ ግድብም ቢፈርስ፤ እንዲሁም ብቸኛዋን ፍትህ ጋዜጣ እየደረሰባት ያለው “ሰፋጣ” ቢቆምላት መንግስትን “የዴሞክራሲ አርበኛ” ብለን እንሸልመው ነበር!
ከዚህ በፊት ያልኩትን አሁንም እደግመዋለሁ። የመናገር እና የመፃፍ መብት መገደብ የኤሌክትሪክ ሀይል አያመነጭም እናም በጅምሩ “መንግስቴ በርታ በርታ…” ብዬ ላዜምለት እወዳለሁ።
ወዳጄ እንግዲህ አሁን ጎግልዎ ላይ ያሻዎን ድረ ገፅ ታይፕ አድርገው ያሻዎን መረጃ ማግኘት ይችላሉ ማለት ነው። ታድያ ዛሬም ሊገደብ ስለሚችል ቀልጠፍ ቀልጠፍ ይበሉና በኢቲቪ የሚመጡ ህመሞችን ያስታግሱ!
ተሸውደሀል…….ምንም የለም….መንግስታችን በሳት የሚጫወትመሰልህ….ሎል
zare iko ayseram . yante blog bicha new miseraw zare. but yesterday, all website was working
THAT IS AMAZING. MAY BE SOMETHING HAD HAPPENED TO THE GUY WHO WAS BAN THESE WEBSITES!!
GOOD ARTICLE ABE!!
ENKUAN ADERESEK BTW!!
Char ware yaseman new mechame, yich Blog, kamgedab alfa electric mamencha jemerachilin malat new,Abiyis yalakimu new, blogachin gin berhanwon endezeh tabira ba Ethiopiyachin.
simply rubbish!
long live to free journalists like you The future of democrat Ethiopia is highly dependent on the free press!!!
ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ ብሎ ጀመረ ነው ያሉት አሁን ማ ይሙት አቤ መንግስት ያንተን ብሎግ እንደ ብሎግ ቆጥሮት ዘጋው ስትል ትንሽ አታፍርም ይልቅ እስክንድርን ሽልማት ሊሸለም ነው አሉት ለአሸባሪው የሚገባው ሽልማት ፈንጅ ና ቦምብ የመሳሰሉትነገር ስለሆነ የዚ ሽልማት sponsor ደግሞ የሽብር አባታቹ ከሆነው ኢሳያስ ሌላ የሚቀርብ ሰው ስላማይኖር እባክህን ተቸገርለት አስመራ ህደህ ተቀበልለት እሱ እንደሆን እድሜ ለናንተ ”አንበሳ” እያላቹ የአንበሶች መጫወቻ አድርጋቹሁታል
ሃይ ዮሴፍ ወዳጅህ መይሳው ነኝ። በጣም የምታስገርም ሰው ነህ። ቢያንስ ለራስህ ታማኝ ካልሆንክ ለድርጅትህ እንዴት ታማኝ ልትሆን ትችላለህ…? የአቤ ብሎግ ተዘግቶ በጎን ሌላ ብሎግ http://abetokichaw2.wordpress.com/ በሚል ከፍቶ ለአንድ ሳምንት ያክል ሲጠቀም እንደነበረ ቢያንስ ቢያንስ አስራ ስምንት ሺህ ጎብኚዎች ምስክር ናቸው። እንዴ ፍሬንድ ማስተባበልም ቢሆን እኮ የሚመስል ነገር ሲሆን ነው! እኔ ግን ከሁሉ የሚገርመኝ ሁሌ ይሄ ብሎግ እንደማይረባ እየተናገርክ ጎራ ሳትል አለመዋልህ ነው። ስለ እስክንድር ያወራከው ምንም የሚገባ አይደለም እባክህ ደግመህ በአማርኛ ጣፍልን! (ለማንኛውም ታዝናናኛለህ) ኪኪኪ
ዮሴፍ በህይወቴ ውስጥ እንዳንተ አይነት አሻንጉሊቶች ያዝናኑኛል አና እባክህ ቢያንስ በቀን አስር ጊዜ እዚች ብሎግ ላይ ብቅ በልልን እንደ ኢሀዲግ ሊግ ስብሰባ የቀን አበል ባናስብልህም ብሎግ ያፈራውን ምክር እንለግስሀለን
Minale ABE Ye ESAT gidib biferese!
ለወትሮ ይችን ብሎግ በመጎብኘት ብቻ የምታወቀው እኔ የአቤ ቶኪቻው አድናቂ ዛሬ የተነሳችው ርህስ በጣም ስላስደሰተችኝ አስተያየት ልሰጥ ወደድኩ እዚህ ጋ የአድናቂና ተደናቂ ታዛቢዎች: እንዴ! የስከዛሬው ርህስ አላስደሰተውም?ብላቹ ታስቡ ይሆናል እኔ ግን የማልወደው የአቤ ፅሁፍ የለም ! እላችዋለሁ ነገር ግን የዛሬዋ ወሬ በጣም አስደሳች ዜና ነገር ሆናብኛለች እናም አስተያየት ለመስጠት ወደድኩ:: አቤ,ያወራህልን ነገር እውነት ሆኖ ከተገኘ በእውነቱ አገራዊ እውነታዎችን መስማት ለሚወዱ ውድ ኢትዮዽያውያን ትልቅ ዜና ይመስለኝል እናም አቤ ይችን ዜና መሰል ወሬ ተከትለን,እንኯአን ደስ አለህ!! እንኯአነ ደስ አለሽ!!ልንባባልበት የሚገባ ይመስለኛል በዚህ የግደባ ስራ ውስጥ ያሉ ዋና የስራ ኢደት ባለቤቶችንም ልናመሰግናቸው ይገባል ባይ ነኝ:: ለአገር እና ለህዝብ የሚጠቅመው, በህዝቡ ህይወት ላይ የሚታዩትን ማለቂያ የለሽ ችግሮች መገደብ እንጂ ህዝቡ እንደ ችግር መርሻ እና እራስን እንደ ማፅናኛ የሚጠቀምባቸውን ቦታዎች በመገደብ መሆን የለበትም!! ባይ ነኝ…. ማለቴ ነን!! ይሄ የሁላችንም ሀሳብ ነው ብዬ ስለማስብ::አቤ, ለምታቀብለን ነገሮች በሙሉ እናመሰግናለን. ደና ሁንልን!! ,
PM MELESE to president Girma (Tenanekegn)
ያኔ ሲነግረኝ ሰው ፈርቶ
አቛቛምህን አይቶ
ለኔ እንደማትሆነኝ
አልሰማም አልኩና
ስትቆም ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
እምቢ አለ ሆዴ ካለሱ
መቆም ሲጥር በራሱ ።
እግሩ ሊሄድ ሲነሳ
ዎፌ ቆመች እምቦሳ።
ስትቆም ሆዴ ባባ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
ባለፈው ሞተ ብለው ቢነግሩኝ
እኔ አላምንም አልኩኝ
ተናነቀኝ ተናነቀኝ እምባ።
ዮሴፍ በተደጋጋሚ ብዙ አሰተያየት ሰጪዎች እባክ ይህ ብሎግ አይመጥንህም ብለው ምክር ቢሰጡህም ሊገባ አልቻለም ፡፡ ዳሩ እናንተ መቼ ይገባችዋል ፡ እስኪ በዚ ከገባ እኔ ደግሞ ልንገር ፡፡
ዋይ አንተ ለዮሴፍ ሎዚ ኖጎር ምናባንስ ፈልገ ነው ፡ አይገባህም እንዴ ዋይ ወዲ ቆርዳድ ፡፡ ለዚ አንድም ነገር አታገኝም ፡ ለዛ አዲስ ፡ አድማስ አታነብም ፡፡ ሙን አይነት ጮሙላቃ ነው እባካችው ፡፡
Hi Abe !! Think you very much!! nice to read your post! and Free press and free Journalists like you!!
@meretwork……open ur eye, he is not free journalist. he is struggling to overthrow EPRDF.