ትላንት ፀሎተ ሀሙስ ነበር። ቀኑን የጀመርኩት ግን በፀሎት አይደለም በሀዘን ነው። ይሄኔ ምን ሆነክ ይላል ብልህ ሰው፤ አዎ እንደርሱ ነው የሚባለው።

በፌስ ቡክ መልዕክት ሳጥኔ ፤ “አንድ ኢትዮጵያዊ ኩዌት ውስጥ በድንገት ሞቶ ተገኘ ልጁ ወደ ኩዌት ከመጣ ገና ሶስት ወር እንኳ አልሞላውም” ሲል ከወዳጆቼ አንዱ መርዶ አስቀምጦልኛል። መልዕክቱን አንብቤ እንደጨርስኩ ድብርት እና ሀዘን በላዬ ላይ ተከመረ። አጠገቤ የነበረውን ጓደኛዬን ጠየቅሁት፤ እስከ መቼ ነው በተሰደድንበት ሁሉ እንዲህ አይነት ስቃይ እና አበሳ የምናየው? አልኩት። እርሱም “ምርጫ ቢኖረው ኖሮ  “መ” እልህ ነበር” አለኝ። “መ” መልሱ የለም ነው። ወይ ጣጣችን!

ከጥቂት ቁዘማ በኋላ እንደ ምንም ድብርቴን ለማራገፍ ድጋሚ ወደ ፌስ ቡክ መንደር ጠልቄ ገባሁ። በርከታ ወዳጆቼ የአመትባሉ ገበያ አሳስቧቸዋል። አንዳንዶች “በግ እናከረያለን ዶሮ ቅርጫ እናቃርጣለን…” የሚሉ ሹፈቶችን ለጥፈዋል። በርካቶችም ዘና ዘና የሚያደርጉ አስተያየቶችን ሰጥተውበታል።

የአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ፤ “በዚህ አመት በዓል ኢትዮጵያ ውስጥ ዶሮ 250 ብር እየተሸጠ እንደሆነ ሰማሁ፡፡ ኢትዮጵያ ያላቸሁ የፌስ ቡክ ጓደኞቼ እውነት መሆኑን ታረጋግጡልኛላችሁ? ወይ ስምንተኛው ሺ!”  የሚል ፅሁፍ ከጥሩ እንስት ዶሮ ጋር ለጥፎ አገኘሁት። ግማሹ “አይ ሁለት ከሃምሳ… ተጋኗል ሁለት መቶ ብር ታገኛለህ” ብሎ ሲያፅናና ሌላው ደግሞ “በሁለት መቶ ሃምሳ ዶሮ የት እንደሚገኝ ለነገረኝ ውለታ እከፍላለሁ” ብሎ  እየፃፈ ተስፋ ያስቆርጣል።  እኔም የተሰጡትን አስተያየቶች ከኮመኮምኩ በኋላ ለማንኛውም ብዬ የዶሮዋን ስዕል “ሴቭ” አድርጌ  ጉዞዬን ቀጠልኩ።

ኢዮብ ብሃነ አንድ ግጥም ለጥፏል፤

እህል ተወደደ፣
ቅቤም ተወደደ፣
ስጋም ተወደደ፣
ፍቅር ከሀገር ጠፋ ዋጋው ተወደደ፣
ምሁር ከሀገር`ራቀ እየተሰደደ፣
ከሀገሬ ገበያ ቁጥሩም የጨመረ
ዋጋው የቀነሰ፣
የካድሬ ብቻ ነው ህዝብ እያስለቀሰ።

እንዴት ማለፊያ ግጥም ናት ብዬ መውደዴን ለመግለፅ “ላይክ” የሚለው ላይ ጠቅ አድርጌ አለፍኩ።

መሰረት ሊ የተባለች ወዳጃችን ደግሞ እንዲህ የሚል ለጥፋለች፤

“በቅርቡ በአሰሪዎችዋ ድብደባ ደርሶባት፥ ህይወትዋ በአሳዛኝ ሁኔታ በሊባኖስ ላለፈው ወ/ሮ ዓለም ደቻሳ መታሰቢያና ልጆችዋን መርጃ እንዲሆን በማሰብ ሀሙስ ሚያዝያ 11/2004 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የኪነ-ጥበብ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። በፕሮግራሙ ላይ ወጣት ገጣሚያን እንዲሁም ታዋቂ የኪነ ጥበብ ሰዎች ይገኛሉ። እርስዎም በፕሮግራሙ ላይ ታድመው እየተዝናኑ ለወ/ሮ ዓለም ደቻሳ ቤተሰብ ስተዋፅኦ ያደርጉ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።”

እነዚህን ልጆች ያኑርልን! ስል በልቤ ምርቃት አወረድኩ። መሰረትን ጨምሮ የማህሌት፣ የጆማኔክስ፣ የዮሃንስ እና የታምራት ታም “መለያ ስዕሎች” ለአለም ደቻሳ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተዘጋጀ ፎቶግራፏን ያካተተ የጥሪ ካርድ ሆኖ አገኘሁት። በዛም ውስጥ ተቆርቋሪነታቸው እና ለወገን አለሁ ባይነታቸው ታየኝ። በዕውነት እናንተ ልባሞች ናችሁ እና የእናንተ አይነት ልብ የት እንደሚገኝ ለመሪዎቻችን ጠቁሙልን እስቲ ልላቸው ወደድኩ።

አሁንም የፌስቡኬን መንገድ ይዤ ቁልቁለቱን ወረድኩት…. ሌላ አሳዘኝ ወሬ።

“ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን በስደት እና በእብደት ላይ” በሚል ርዕስ በሪያድ የሚገኙ እህቶቻችንን ስቃይ የሚያሳይ ቪዲዮ…! በጣም አሳዛኝ ነው። በአንድ ቤት ውስጥ ለመቁጠር እንደሞከርኩት ወደ አራት የሚጠጉ እህቶቻችን በአዕምሮ መቃወስ ሲሰቃዩ ተመለከትኩ። በእውነቱ ሀዘኔ በረታ “ሙዴም ተከነተ” ፌስ ቡኬም አስጠላኝ ኮምፒውተሬም “ደበረኝ” እስከመቼ ነው በየሰዉ አገር የምንሰቃየው። መቼ ነው ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ አገር የምትሆነው? እስከ መቼ ድረስ መልሱ “መ” ሆኖ ይቀጥላል? ብዬ ከኮምፒውተሬ ገለል አልኩኝ።

ከተወሰኑ የቁዘማ ሰዓታት በኋለ ኮምፒውተሬን ከፈትኩ፤ ኢንተርኔቴን አገናኘሁ። ወደ ፌስ ቡክ መንደርም  ድጋሚ ጎራ አልኩ።

“እምዬ ኢትዮጵያ የጀግኖች እናት እስቲ ፈልጊልኝ የሚከራይ ቤት” የሚል ፅሁፍ ተለጥፎ አየሁ። ይህንን ፅሁፍ ከዚህ በፊትም አይቼዋለሁ። እውነትም የሚከራይ ቤት እንኳ ኢትዮጵያችን ብታገኝልን ቢያንስ በየ አረብ ሀገራቱ እህቶቻችን አየሰቃዩም ነበር። ብዬ እያሰብኩ…  ወረድ አልኩ። አሁን አሪፍ ዜና አየሁ።

እስክንድር ነጋ ታላቅ አለም አቀፋዊ ሽልማት አገኘ!

ታዋቂው እና ተወዳጁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ “ፔን ኢንተርናሽናል” ከተባለ ድርጅት PEN/Barbara Goldsmith Freedom to Write Award. የተባለውን ሽልማት አገኝቷል።

እንደሚታወቀው እስክንድር ነጋ በአሁኑ ግዜ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይገኛል። እንደማይታወቀውም እስክንድርን ከባለቤቱ ከልጁ እና ከጥቂት የተመዘገቡ ሰዎች ውጪ በቃሊቲ ማንኛውም ሰው ሄዶ ሊጠይቀው እንደማይችል ሰምተናል።

እስኬው ይህንን ሽልማት ማግኘቱ ሲያንሰው ነው። በሸላሚዎቹ መግለጫ ላይ እንደተገለፀው እና እኛም ስናየው እንደኖርነው እስክንድር እያንዳንዷን ቃላት ሲፅፍ ሰዎቻችን ደግሞ እስከ ሞት የሚያደርስ ጉንጉን እንደሚሸርቡለት ያውቃል። ይህንን ተጋፍጦ ነበር የሚፅፈው። በነገራችን ላይ እስክንድር ስለ ፃፈ ብቻ ከሰባት ግዜ በላይ እስራት ደርሶበታል። እርሱ ግን ወይ ፍንክች! አሁንም ያው ነው!

አንበሳ … ቀነኒሳ ሳይሆን እስክንድር ነው። ብንልስ… (ቴዲ ቢሰማ አስተካክሎ ይዘፍናት ይሆን…?)

አሁን መሸ

ኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን ጠራሁት “…እንኳንስ ጠርተውኝ…” ብሎ ብቅ አለ። የዜና ሰዓት ደርሷል። የዛሬው ዜና አቅራቢ ያ አሽሟጣጩ ነው። እርሱ ሰውዬ ይገርመኛል እንደምን አመሻችሁ… ሲል ጠረቤዛውን በግንባሩ ገጭቶ ነው። ከዚህ በፊት “የመተጣጠፍ ብቃትህን እናደንቃለን ቢሆንም ግን ማጎብደዱ ሲበዛ ሽሙጥ ይመስላልና በቅጡ አድርገው” ብለን ለማስመከር ሞክረን አልተሳካልንም።

ዜናው ቀጠለ “በዛሬው እለት ፀሎተ ሀሙስን አስመልክቶ የትህትና ምሳሌ የሆነው የእግር ማጠብ ስነ ስርዓት ተካሄደ። ብፁህ አቡነ ጳውሎስ የካህናትን እግር አጥበዋል” ብሎ የአቡኑን ትህትና ሊያሳየን ሞከረ።

እኔም በሀሳቤ የአቡኑ በርካታ ትህትናዎች መጡብኝ…

ትህትና አንድ

የዛሬ ስንት አመት እንደሆነ እንጃ በመስቀል አደባባይ የደመራ ስነ ስርዓት ይከናወን ነበር። ታድያ አባታችን ፀሎት እንዲመሩ መነጋገሪያ “ማይክራፎን” ተሰጣቸው። እሳቸውም የዛኔ በምን ተበሳጭተው እንደነበር እንጃ “እስቲ ዞር በሉልኝ ምድረ ጭቃ!” ሲሉ በቀጥታ ቴሌቪዥን ተላለፉ። እኔም ለርሳቸው “ትህትና” አምስት ሳንቲም እስከማክል ድረስ ተሸማቀኩላቸው።

ትህትና ሁለት

እኔ የምለው ቦሌ መድሃኒያለም ልንሳለም ስንሄድ ዛሬም መጀመሪያ የምንሳለመው የብፁህ አባታችንን ሀውልት ነው አይደል? ከትህትናቸው ብዛት የገዛ ሀውልታቸውን መርቀው የከፈቱ ብቸኛ ሰው “አባታችን” መሆናቸው ነው። (በነገራችን ላይ አቡነ ጳውሎስን ዋና ዋና የኢህአዴግ ሰዎች “ብፁህ አባላችን” ነው የሚሏቸው ሲባል ሰማሁ። እውነት ነው እንዴ እስቲ አጣሩልኝ! (ይቺ እንደ ለከፋ ትቆጠርልኝ))

በመጨረሻም

ስለ ስቅለት

ስለ ስቅለት ትንሽ ለማለት ሳስብ ስብሀት ገብረእግዚአብሄር ትዝ አለኝ አንድ ወቅት ይህንን አውግቶ ነበር እስቲ እናስታውስ፤

ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ቀራኒዮ እየሄደ ነበር። መንገድ ላይ አንድ የዛፍ ጥላ ያለበት ቦታ አገኘ። ይሄኔ ትንሽ ፋታ ባገኝ ብሎ ርምጃውን ቀስ አደረገ። ታድያ ዛፉ ጥላ ስር አንድ ባለ ሱቅ ነበር እና በግርግሩ ገበያው እንዳይቀዘቅዝ አስቦ “ባክህ ሂድ አትንቀራፈፍብኝ” ብሎ ጌታን አመናጨቀው። ኢየሱስም ቀና ብሎ አየውና “እኔስ እሄዳለሁ አንተ ግን እስክመለስ እዚሁ ትጠብቀኛለህ!” ብሎት ሄደ። ስብሀት እንዳለን ከሆነ ያ ሰውዬ አሁንም ጭምር ሀገር እየቀያየረ ይኖራል።

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

24 responses »

  1. ዮሴፍ says:

    ”በሞኝ ክንድ የዘንዶ ቤት ይለካበታል”በትግርኛ ደግሞ (ዘይኩሩምትካሲ ሑጻ ቆርጥመሉ ) ብርትኳን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ገዜ ቃሊቲ እንድትገባ ያደረጋት ነገር በስዊድን (አገሩ እርግጠኛ ባልሆንም)ለደጋፊዎችዋ አደረገችው የተባለውን ንግግር ነው እሱም ጥቂት ደጋፊ ነን ባዮች(እንደ አቤ የመሳሰሉትን ማለት ነው) ”የነጻነት ታጋይ ኢትዮፕያዊትዋ አን ሳን ስኩ የሴት አንበሳ ጀግና ማንም አይነካሽም እኛ አለን አሁን በነጻነት መናገር ትችያለሽ ”ብለው የልብ የልብ ሲሰጥዋት የዋህዋ ብርትኳን ከመቀጽበት ወደ ”አንበሳ” ትቀየርና እስዋም በተራዋ ” አኔ ለመንግስት ምንም የጠየኩት የቅርታ የለም እድሜ ለናንተ ከአሁን ብኋላም መንግስት ምንም ማድረግ አይችልም”በማለት ተናገረች አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ ቡዙ አልቆየችም አድስ አባበ እንደ መጣች ግን ቃሊቲ እያለች ያላወራረደችው ሂሳብ ነበራት መሰለኝ የ21 ወራት ሂሳብ አወራርዳ ለሁለተኛ ግዜ ”ዳግመኛ አይለምደኝም አንበሳ ነሽ ሲሉኝ አንበሳ የሆንኩ መስሎኝ ነው እና መንግስት ይቅርታ አድርጎ እንደገና ይፍታኝ ”ብላ ከሼቤ ነጻ ወጣች ድሮም እንዛ ያጨበጨቡላት ሰዎች መሞከርያ ለማደረግ ነው አገር ግቢ ምንም አትሆኝም ብለው የላክዋት 21 ወር ሙሉ ቃልቲ ስትቆይ ግን አንድ ሰው እንኳን ዞር ብሎ ያያት ሰው አልነበረም አና አሁንም አቤ እስክንድርን ”አንበሳ”ነህ ስትለው ያኔ ያንተ ብጤዎች ብርትኳንን በነፍስዋ የተጫወቱባትን አሳዛኝ ነገር አስታወስከኝ ይመችህ ግን እንደው አቤ ሳልጠይቅህ እንዳላልፍ ነው መታሰር አንበሳ የሚያስብል ከሆነ ለምን አትታሰርምና አንበሳ አትሆንም አንበሳ መሆን የሚጠላ ሰው የለም በየ ነው ምንም እንኳን መልክህ ከጅብ ጋር ቢመሳሰልም መልካም ፋሲካ

    • Nura says:

      you’re such a dick head, you don’t even know what you’re talking about, why don’t you go fuck yourself cause this is not your place, you won’t understand what people say here because it’s beyond your level of understanding, may be Addis zemen is the right paper for you. cheka ras

    • ሀጎስ says:

      አታ ዮሴፍ ምን ነካህ ብርቱካን የታሰረችው ሰው አንበሳ ስላላት ነው ትላላህ? አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ይላል አማራ ሲተርት። ምን ለማለት ፈልገህ እንደዚህ እንዳልክ ማብራሪያ እፈልጋለሁ።

    • Binyam Birhanu says:

      Yosef hasabihin yemeglets mebt binorhim sewochin bemezlef lay yatekore bayhon melkam new. Yemititsifew neger yehasab liyunetihin geltso lewiyiyitu astewatso kemadreg yiliq antenu melsu eyasgemeteh new. hasabochin sayhon gilesebochin matqat tegebi yalehone yekirikir hidet silehone tarem.

    • mimi says:

      ዮሴፍ በትክክል የኢሃፓ ወይም የሻእቢያ አባል ነው:: ያረጀና የበሰበሰ አስተሳሰብ:: አስመስሎ ለማስጠላት ነው ሙከራው::ዓትስሙት:: ብዙ ጊዚ ሲጽፍ ስድብ ያበዛል ለዛውም ከሰው አፍ የማይጠበቅ:: ይህ የሚያሳየው ህዝብና መንግስት የበለጠ እንዲጠላሉና አደጋ እንዲከፋ ለማድረግ ያሰበ ይመስላል:: ሃሳብን ማንቅዋሸሽ ወይም ማጥላላት ጥሩ ነው የአምላክን ስራ መሳደብ ግን የአሳዳጊ በዳይን ያሳያል::

    • Tikur Sew says:

      አይብ አንጎል

  2. meles yeweged says:

    abe thanks for the great piece and keep up the great job, of course together with the help of few brave ethiopians, we will remove the weyane cancer racist and criminal group and it is going to be only a matter of time, god bless you and wishing you MELKAM FASIKA

  3. Kulich says:

    “እስክንድር ያመነበትን፣ የሚያምንበትን ነዉ የሰራዉ። ሌላ አይደለም። በኢትዮጵያ ዉስጥ ዲሞክራሲ እንዲያብብ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ነዉ ሲሰራ የነበረዉ። አንድ ቀን አንድ ችግር እንዲሚያጋጥመዉ እያወቀ አምኖበት የገባበት ነዉ። “ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል

    I admire Eskinder for his courage and commitment to freedom and democracy. He has been a real nightmare for Meles and cronies. They jailed him several times. They permanently barred him from printing a newspaper. They tried to push him out of the country but he told them he will never go to exile. He is as adamant as ever. He courageously exposed the crimes of Meles and his cronies. Now, they once again put him in jail. One thing is certain: they may be able to jail him but they cannot and will not be able to jail his spirit.

  4. ethiopiawiw says:

    ምርጥ ጽሁፍ አቤ :: ብዕርህ ትባረክ::ሰዎች በሚናገሩት ወይም በሚጽፉት የጭንቅላታቸው ደረጃ ስለሚለካ መጻፍህን ቀጥል

    እስር ቤት ቃሊቲ ብቻ አይደለም መላ አገራችን ኢትዮጵያ እስር ቤት ከሆነች ቆየች

    መልካም ትንሳኤ

  5. leo says:

    at yosef ende ante aynetu qemalame ye dedebit mehure ezhi bota baylekesekese tiru aymeselhem. yehe ye qemalam, nefete yetemola chneqelate yalachew ye dedebitoch mesebasebiya yadelem,,, bothane chenqelate kelelechew yeqemalam dedeboch boota felege. huletegnam ezhi banayhe yemeretal. gezehe derso antem anbesa eskemethone, ke agothe sere honeh ager aqoshesh agere zeref, engerhalew antem anbesa yemethonbet geze eyqerebe new. malkam fasika

  6. chuppy says:

    From the the begining he (yosif) tried to mention us his ethincity and wrote discusting things however we are not hate you but we really oppose your maner and ideology so pls don’t be a flat person.

  7. mikru says:

    @ yosef: yemigerm chinklat kemiger/kemayetatam sim gare yezehal. Menagerna metsaf endih ante endemetelew lehod eyaderu bitcha kemeseleh kelem yakebeluh astemariwocheh chimer efferu! Lenegeru tasib zend chinklat sayhon hod tadeloh bemin tamir ende sew biyanc sewoch yasebuten yemenager mebtachew tefetrowawi mehonun sew eskinegreh atekoyem neber! ere lemehonu ante min temeslaleh. ene gemit ketebalku, tsehufehen say malet new, ensesa enkuwan neh beye alamenim… letmhert indihoneh sewoch hasbachewen letkawem techilaleh, tadia tenkek eyalk, yemitawk eyemeseleh alawkinetehn endih ende ahunu endatasabek!!!!!!

  8. ETHIO says:

    @ yosefe ! u tried to write to suggest someone who does not need any comments cuz he is not ur type and totally different from u .reason 1; u are using ur ethno-centered shaped mind and childish as wel as animalstic thinking but THE REVERSE IS TRUE 4 Abe. reason 2; his article contains with relevant and accurate information,but urs is to insult others reason 3;Abe writes about his country and his people but u do NULL…….bla bla………….

    @Abe it is ur article’s power which makes me honest to log in my facebook everyday/at list/ .
    plze let them to shout /bark/ those null’s and continue ur lovely job!!!!!!!!!!

  9. Meyisawu says:

    Abe wondimachin let me ask u one question yihe mutcha yosef emibaln sewu des baleh bota talewu bitibal yet titilewalehi?kaliti endatilegne letelatim yitazenalina!

  10. bawukew says:

    hmm there are ppl dead ppl and then ppl like Yosef who know nothing…. benatih indante aynetochu nachew hibret indaynoren yaregun tewew isti yale ante ayinetu hasabachinin indigelts isti izih inkuan tewen

  11. Mah says:

    መተንፈስም ሊከለከል ነው እንዴ? ተወልዶ ካደገብት ሃገር እንደባይተዋር አንገብግበው አስወጡት፡፡ አሁን ደሞ በሰው ሃገር ምን አርግ ነው የሚሉት? ኸረ ጉድ ነው ጎበዝ!

  12. Gardachew says:

    Abe, don’t listen and fade-up with persons whose minds are empty. Yes, You are the real Ethiopian.
    @Yoseph alferedebhim, bad chinkilat selhonk new

  13. Eyoel says:

    አቶ ዮሴፍ ምንያለህ ሰው ብትሆን ነው? ብርቱካን የታሰረችው አንበሳ እያሉ ስላደፋፈሩዋት ነው የምትለው? ካላውክ አላወኩም ነው የሚባለው ብርቱካን ቃሌ በሚል ርዕስ ከመታሰሩዋ በፊት አንድአንቀዕ ዕፋ ነበር። ታዲያ በዚህ አንቀዕ ላይ ብርቲካን የኔ ያለችውን እና ያመነችበትን ነገር ነው ያንፀባረቀችው ሙሉውን ማንበብ ከፈለክ ደግሞ በአዲስ ነገር ጋዜጣ ወይም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ታገኘዋለህ። ለማንኛውም የማታውቀውን ነገር ዝም ብለህ ባትዘላብድ ጥሩ ነው።

  14. ሽብር ሽብር ፧ ይላል ፡፡ says:

    አቤ የዮሴፍ መሰሎቹን የሚናገሩትን ያውቃሉ እና ይበልጥ ለነሱ እና ለመንግስታቸው እንዲገባቸው በደንብ አድረገ አሽማጥ ፡፡ ቆይ ዮሴፍ እንደው አንድ ተሳሰቶ ደና ነገር የሚጽፍ ካድሬ የላችውም ? ለምን የነሱን አታነብም ፡ ግን ሳሰበው አቤ የሚጽፈው ነገር እንደሚመች ነው ፡፡ ያው ለግምገማ ምናምን በለ ከሆነ የምታነበው ጥሩ ፡፡ በተረፈ መታሰር ካልከው በኢትዮጰያ እኮ አንተን ጨምሮ ሚሊዮኖች እስረኞች ነን ፡፡ መሪዎች ቢቻላቸው ሁሉንም ህዝብ አስረው ለብቻቸው ቢኖሩ ደሰታቸውን አይችሉትም ፡፡
    ሰለዚ ምስኪን ኢትዮጰያ ልጆች የከፈሉት መሰዋትነት እንደዚ በጥርቅሞች መጫወቻ ሆኖ በማለፉ አሁን ሁላችንም የህሊና እስረኞች መሆናችንን አትርሳ ፡፡ ሲቀጥል ብርቱካንም ሆነች እስክንድር በአንተ አፍ የሚጠሩ ሰዎች አይደሉም ፡፡ ብርቱካን ባመነችበት የመጻነት መንገድ የምትጓዝ ፡ እስክንድርም ሰለ እውነት ሲል እየጻፈ የኖረ ሰው ነው ፡፡ የተሰጠው ሽልማት ሲያንሰው ነው እንጂ አይበዛበትም ፡፡ ዳሩ አንተ ምን ታደርግ ጋዜጠኛ አሸባሪ ተብሎ የታሰረባት ሀገር ላይ እየኖርክ ምንም ብትናገር አልፈርደብህም ፡፡ ከመጻፍ በፊት ደጋግመ አሰብ ፡፡

  15. Melese As an Abebe says:

    Guys i Gues Yosef may be Melese or Berekete we got nice lesson how those Pesudo leaders act ? cause they do hv lots of times on bercha like melese Zenawi was say am Abebe in VOA English program lesson this http://www.ethiotube.net/video/5709/Meles-Zenawi-as-Abebe-Asking-question-on-VOA

  16. […] ወደ አቤ ቶክቻው:: ከዚህ ሳምንት የአቤ ጽሁፎች ቀልቤን የሳበችው የፀሎተ ሀሙስ […]

  17. SAMI says:

    AS USUAL INTERSTING THANKS FOR SHARING US.

  18. Alexo DD says:

    Do not be distracted by what a person like Yosef says. He is degrading himself by trying to dehumaize Abe. Focus on grand issues and sometimes amusing comments Abe and followers raise. Ignore Yosef. Don’t post anything in reply to whatever he rambles. Let him shout alone. Never listen to him. He is an ordinary distractor and hatemoneger.
    Be blessed.

  19. በለው! says:

    እህል ፡ተወደደ፡ ልጅም ፡አለቀሰ ቅቤም፡ ተወደደ፡ አፍን ፡አላበሰ ስጋ ፡ግን ፡ተዋርዶ፡ ተልከሰከሰ ፍቅር ፡ጣእም ፡አጥቶ፡ በጣም፡ ረከሰ ጭስ፡ በአይን ፡ገብቶ፡ አላስለቀሰ ውሃ፡እሳትን፡ናቀ ፡በከንቱ፡ፈሰሰ ድሃ፡በቁም፡ሞተ፡እንደተጠበሰ ክፉ፡ቡዳ፡በልቷት፡ለገሠ፡መለሰ!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s