በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የትንሳኤ በዓል ሊመጣ ሳምንት የማይሞላ ግዜ ቀርቶታል። እስቲ በሰላም ያምጣውና ሌላው ቢቀር እንኳን አደረሳችሁ ለመባባል ያብቃን።
አሁን ህማማት ላይ እንገኛለን። በሀይማኖቱ የበቁ ወዳጆቻችን እንደሚነግሩን በዚህ ሰሞነ ህማማት ውስጥ ያሉ እያንዳንዱ ቀናት ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ የደረሰበት ስቃይ የሚታሰብባቸው ናቸው። በተለይም ኢየሱስ በአደባባይ ቆሞ ባስተማረ እና በተናገረ ግዜ የደረሰበት ስቃይ፤ ከአጓጉል ውንጀላ አንስቶ ግርፋት፣ እስራት፣ በመጨረሻም ስቅላትን ያካተተ ነበር።
ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በኋላ እሁድ ትንሳኤ ይሆናል። ደስታም ይበዛል።
ከመንፈሳዊው ጉዳይ ፊታችንን ዘወር ስናደርግ የሚከተለውን እናገኛለን፤
ኢህአዴግ አዲሳባን እና መላውን አገሪቷን “ለሰፊው ህዝብ ጥቅም” ብሎ ከተቆጣጠረ ስንት አመት ሆነው? ግንቦት ሲመጣ ሃያ አንድ አመት ይሞላዋል። (ደህና ጎርምሶ የለም እንዴ!?) አሁንማ ሚስት አምጡ ብሏል! አይሉኝም?
ከደርግ ጋር ሲነፃፀር የኢህአዴግ በትረ ስልጣኑን መያዝ እንደ አዲስ ኪዳን የቆጠሩት ብዙዎች ነበሩ። በተለይ ለዲሞክራሲ ናፋቂዎች ትልቅ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር። “የመናገር እና የመፃፍ ነፃነት ተከብሯል።” ተብሎ ታወጀ። እሰየው ተባለ። “ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ይቻላል ተብሎ ተነገረ።” እንዲህ ነው እንጂ ብለን አደነቅን! “የነፃ ገበያ ስርዓት ተግባራዊ ይሆናል” ተባለ። እልልል… ይህንን ሁሉ አለም የሚያሳዩን እነዚህ እነማን ናቸው? የሚል ውዳሴ ጎረፈ። ህዝቤም በየ መስኩ ተሳትፎውን አሳየ።
ቀን ቀንን እየወለደ ሄደና ዛሬ ሀያ አንድ አመት ሞላን አዲስ ኪዳን ስንል ያሞካሸነውም ዘመነ ኢህአዴግም በመግቢያው ያበሰራቸውን በሙሉ ረሳቸው። ችግር ረሀብ እና እርዛትም በዙ። ነፃ ገበያም ሆነ ነፃ ንግግር ተግባር ላይ ጠፉ። ይልቁንም በአደባባይ ቆሞ መናገር ያስወነጅል ጀመር። እስራት እንግልት ምርመራውም በረከተ። በሁሉም ዘንድ ስቃዩ በዛ! በርካቶችም አሉ፤ “ህማማቱ ገባ”
እውነትም ወዳጄ ኢህአዴግ አዲሳባ ሲገባ አዲስ ኪዳን ሆኗል ካልን አሁን ያለነው በርግጠኝነት ህማማቱ ላይ ነው። ከህማማቱ ቀጥሎ ምን የሚከሰት ይመስላችኋል? እኔ ግን እላለሁ ትንሳኤ እየመጣ ነው! እናም በህማማቱ ላይ ያላችሁ በሙሉ አይዟችሁ!
ለማንኛውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ መልካም ሰሙነ ህማማት ይሁንላችሁ! ተግታችሁ “አቤት” በሉ!
Min egnan ersu asgeddo kedefaren difn 21 amet lemalet falgeh new yemselachw ybalal….
እንዴት እንዴት አድርገህ አገናኝኅው በናትክ? አቦ ይመችህ!! ለማንኛውም ሁልጊዜም የኢህዴግ አካሄድ የጆርጅ ኦርወእልን አኒማል ፋርም ያስታውስኛል::ከድጡ ወደ ማጡ…
http://www.george-orwell.org/Animal_Farm/0.html
thanks Meri &Abe
እኔ ደግሞ እላለሁ የህማማቱ ቀናት አጭር ይሆኑ ዘንድ ተግታችሁ ጸልዩ
ወይ ቸኩሎ ማንበብ! ከህማማቱ ቀጠሎ ትንሳኤ ነውና በርቱ!ያልከው….. ከህማማቱ በሗላ ወያኔ ይነሳል ያልከ መሰሎኝ ኢህድግ በራሱ ላይ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ እረምጃ ሊወሰድ ነው ብዬ ተገረመኩ መቼም አንዳንድ ጊዜ የሸነጠው ከተወለደ ብዬ ነው!! ለነገሩ የዚህ የቡድን አህያ ሾ ዞጠኝ ሞቶ…አብዮት ጊዜ ዲሞከራሲ መሰቀል አደባባይ በነጻ ታድሎ ስብሰባው ሲበተን ሕዝቡ በኮንትሮባንድ መለመን ጀመረ።የመናገር መብት”ሰላምታ” ብቻ! የመጻፍ መብት የፍቅር ደብዳቤ ለዚያውም ካርድ ላይ ወይንም የፍቅረኛን ሥም ማስነቀስ(ታቱ) ማስራት! ተቀናቃኝ ፓርቲ በምርጫ አካባቢ ብቀ ብለው ለኢቲቪ ፕሮግራም የሚያዳምቁ፣ የፖለቲካ አጀንዳቸውን በቃል እነጂ በጽሑፍ ያልቀረፁ! የነጻ ገበያ ? ? በፈለከው ቦታ አምርተህ, የፈለከው ቦታ ወስደህ, በሚያዋጣህ ዋጋ የመሸጥ፣ ግን አውራ ፓርቲውን ከማሞገስ፣ ከመርዳትና ከመጠበቅ አትቦዘን!!! አንዳንድ ጊዜ የውስጥ አዋጅ እና መመሪያ ሲወጣ ስታይ አትደናገጥ ተግባራዊ አይሆንም ይልቁንም ሕዘቡ ውስጥ ገብተህ አማር አልቅሰህ አላቅስ !! በብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በብፁህ አባታቸው አቶ ለገሰ(መለሰ) ቃል የተወሰደ….ጸሎት አብዝታቸሁ የትንሳኤው ሰዓት እንዳያመልጣችሁ ተግታቸሁ ጠብቁ የደከሙም ቢኖሩ አበረታቷቸው ኢህአደግ ያልፋል ቃላችን አይጠፋም ጮክ ብለን “አቤት” እንላለን በለው ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን>>>>>>>>>>>>>>>>*<<<<<<<<<<<<<<<<<<<
ህማማቱ በርግጥ ከባድ ነው ? ከፊት ያለው ትንሳሄ ሲታሰብ ግን ከ ሃያ አንድ አመት ፡ የበሽታ ዘመን በዋላ ፡ አልጋን ተሸክሞ እንደመሄድ ይቆጠራል ፡ በደሰታ ብዛት ፡፡ ድጋሚም እግዚያቤር ያለውን ቃልም እናሰባለን ፡፡
ህዝቤን ልቀቅ ********* ህዝቤን ልቀቅ ********** አዎን ወያኔ ህዝቡን ልቀቅ እና በትንሳሄው ይደሰት ፡፡
አኔ ደግሞ እላሎ አሁን ባላቹሁበት ከቀጠላቹ (ከረገጣቹ) ከህማማቱ ብኋላም ሌላ ረጅ……..ም ህማመት ይጠብቃቹኋል ወይ አካሄዳቹ(ጭሆታቹሁን)ቀይሩ ያው እስካሁን ያየነው ጭሆት ብቻ ነው ብየ ነው አለበለዚያ ሌላ አድስ አይነት ጭሆት አሳዩን 21 አመት ሙሉ አንድ አይነት ጭሆት ደስ አይልም ይልቅ ጉሮሮቹሁን ሌሌላ ረጅም ጭሆት አዘጋጁት ምናልባትም እስከወድያኛው መልካም ፋሲካ