ይህው እንግዲህ ፆም ሊፈታ ነው። ተስፋዬ ካሳ በአንድ ቀልዱ ላይ ሁለት ችግር ያላቸው…! (“ር”ን ረዘም ያድርጉልኝ) እናም ሁለት ችግርርርር … ያላቸው ባልና ሚስቶች ብላችሁ አንብቡልኝ፤ ስለ ፆም ፍቺ ያወሩትን እንዲህ ነግሮን ነበር፤

ሚስት “እንግዲህ አሁን ፆሙ ሊፈታ ነው። ምን ይሻለናል?” ብላ ትጠይቀዋለች።

ባል ታድያ ምን አላት፤ “አይዞሽ ሌላ ፆም እንይዛለን” ብሎ “አፅናናታ”

ተስፋዬን ደግሞም ደግሞም ነብሱን ይማርልን!

አሁንም ፆም ሊፈታ የቀሩት ጥቂት ቀናት ናቸው። ገና አመት በዓሉ ሳይቃረብ የጀመረው አስማታዊ የዋጋ ውድነት አሁንም ከልካይ አላገኘም። ከሳምንት በፊት የአዲሳባ ወዳጆቼ እንደነገሩኝ ከሆነ ዶሮ፣ ቅቤ፣ በግ እና አጠቃላይ የአመት በዓል “አክሰሰሪዎች” ዋጋ ሰማይ ነክቷል።

ለምሳሌ ዶሮ አንድ መቶ ሰማኒያ ብር ቅቤ አንድ መቶ ስድሳ ብር ከገቡ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ በዓሉ ሲቃረብ  ስንት ይገባሉ የሚለውን ሸማች ይወቀው።

እንግዲህ አመት በዓልን አመት በዓል የሚያደርጉት በርካታ ነገሮች አሉ። እንደ አስተያየት ሰጪዎች ከሆነ “በአሁኑ ግዜ ከአመት በዓል እሴቶቻችን ውስጥ የቀረን “ሞቅታ” ብቻ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ። እርሱም በማር ጠጅ የመጣ ሞቅታ አይደለም፣ በገብስ ጠላም የተፈጠረ አይደለም… (እነርሱማ የት ተገኝተው…!?) እንግዲያስ ከወዴት የመጣ ሞቅታ ነው…? ያሉ እንደሆን፤ እንክርዳድ የበዛው ኑሯችን ያመጣብን፤ በዓል አዘቦት የማይለይ ሞቅታ ነው ይሉዎታል።

እናም የዘንድሮን በዓል በርካቶች ሳይበሉ ሳይጠጡ ብስጭት ባመጣው ሞቅታ ለማለፍ ተገደዋል እያሉ የሚያወጉ በርክተዋል።

“ማማረር ምናባቱ!” ያሉ የፈጠራ ክህሎት የታደሉ ነዋሪዎች ደግሞ የአመት በዓል ደስታዎችን ለማግኘት የሚያስችል ዘዴ ሲያስቡ ሰንብተው አንድ ማስታወቂያ ማውጣታቸውን ሰምቻለሁ። የስራ ማስታወቂያ ነው ነገሩ። እንዲህ ይላል።

የስራ ማስታወቂያ

የስራው መደቡ መጠሪያ ….. ተዋናይ

የትምህርት ደረጃ…….  የፈለገው ይሁን

የስራው መግለጫ አንድ

እንደ ዶሮ እና በግ ሆኖ  የሚተውን፤ መኖርያ ቤታችን እስከ ዛሬ ድረስ መጣ የተባለውን አመት ባዕል በሙሉ በተቻለ አቅም፤ ዶሮ ሳይታረድ ጠቦት ሳይጣል አልፎ አያውቅም ነበር። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን እነዚህን ማሟላት አልተቻለም። ቢሆንም ግን፤ በመኖርያ ቤታችን ቢያንስ ቢያንስ  የዶሮ እና የበግ ድምፅ መሰማት አለበት ብለን ቆርጠን ተነስተናል። ስለሆነም አመልካቾች የዶሮ እና የበግ ድምፅን አመሳስሎ በመጮህ ለመሮሪያ ቤቱ ድምቀት መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

(ስራው ትልቅ የማስመሰል ጥበብ የሚፈልግ በመሆኑ ባለፈው ግዜ በልማታዊው እግር ኳስ ላይ የተሳተፉ አርቲስቶች ይበረታታሉ!)

የስራ መግለጫ ሁለት

እንደ ዘመድ ሆኖ የሚተውን፤ ከዚህ በፊት በነበረን ልምድ ለአመት ባዕል በመኖሪያ ቤታችን ዘመድ ተሰባስቦ በልቶ፣ ጠጥቶ ሙያችንንም አድንቆ ይሄድ ነበር። ዘንድሮ ግን ዋናዎቹ ዘመዶቻችን በቤታችን ምንም እንደሌለ እና ገበያውንም ደፍረን እንደማንሸምት ይረዱታል ብለን እናምናለን! ይህንን ሁሉ ችላ ብለው እንኳ ቢመጡ ተሳቀው ከመመለስ ውጪ ቀድሞ የለመዱት አይነት መስተንግዶ ለማድረግ አቅም የለንም።  በመሆኑም እንደ ዘመድ ሆኖ የሚጫወት ተዋናይ ማግኘት አስፈላጊ ሆኗል። አመልካቾች ምንም ሳይበሉ ሰይጠጡ ጎረቤት ጉድ እስኪል ድረስ የቤታችንን ሞያ እያደነቁ ድምፃቸውን ከፍ አድወርገው ማውራት ይኖርባቸዋል። ከቤት በሚወጡ ግዜም አረማመዳቸውም ሆነ ጨዋታቸው “እሁድ የቁብ ጠላ ስለጋ ስለጋ…” እንደሚለው ዘፋኝ መሆን ይጠበቅበታል።

አመልካቾች ለመመዝገብ በሚመጡበት ግዜ ለበዓሉ ማድመቂያ የማይመለስ፤ ቄጤማ፣ ጠጅ ሳር፣ እንዲሁም እንደ እጣን የመሳሰሉ ጢሳጢሶችንም ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ።

የደሞዝ ሁኔታ…

ውይ ለካ ይሄም አለ… በቃ ተዉት እንደሚሆን እንደሚሆን እናልፈዋለን!

About abetokichaw

ራሱን አቤ ቶኪቻው እያለ የሚጠራ አንድ ግለሰብ በአዲሳባ ከተማ ይኖር ነበረ። በአዲሳባ ከተማ በሚኖርበት ግዜ የመንግስትን ያልተስተካከለ አስራር ሲያሽሟጥጥ መንግስት ተቀየመው። ምን መቀየም ብቻ… ከሀገር እንዲሰደድ ሁሉ አደረገው እንጂ! ይህ ግለሰብ… ከዚህ በፊት ሁለት ሽሙጣዊ መፅሐፍትን ያሳተመ ሲሆን “የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች” እና “ስላቆች” ይሰኛሉ። አሁንም ቢሆን የማይሆን ነገር ካየሁ ከማሽሟጠጥ አልመለስም የሚለው ይህ ስደተኛ… እነሆ በዚህ ብሎግ ላይ ደግሞ በሽሙጥ የአፃፃፍ ብልሃት ቢያንስ በሳምንት አንድ ግዜ ልከሰት ብሎ “ሀ” ብሏል።

9 responses »

  1. astin says:

    ahhehehe

  2. ጥጉ says:

    አቤ! ልሳቀው እንጂ! ሌላ ምን ይባላል!?
    ሰራዊት ፍቅሬ ልማታዊ አርቲስት ስለሆነ ይህንን ማስታወቅያ
    በነጻ አይሰራም ብለህ ነው?

    • Addis says:

      አረ ምን ትላለህ ከበሽታም ሽንታም ሆነውብናል ጥቂቶቹ አርቲስቶቿችን አርቲስቶቿችን ልበል እንጂ እኛ አርቲስቶች ለናንተ ነን እያሉ ስለሚዘባበቱብን ይብላኝ ለነሱ ለማፈሪያዎቹ ለማያፋሩበት ህዝብ ግን እኮ አዛባ ሆኑበት ይገርማል አድምጥልኝ ጥቂቶቹን ማለቴ ነው

  3. rediet says:

    Hahahahahahaha…..abe ahun gena gedeliken………gin yihe ken weyane eskale dires and ken memitatu aykerim…….”ere geta hoy….ke weyane nuro gelagilen enjiiiiiii”….tnx abe

  4. Time19 says:

    Hahahahhaha..kkkkkkkkkkkkkkk…
    አቤ!!!! ማሽላ እያረረች ትሥቃለች እንደተባልው ሆኖብኝ ነው ከልቤ እያዘንኩ ጥርሴ ለመሳክ የሞከረው። ምን ይደረግ በራሳችን ችግር መሳቅና እራሳችንን ማጽናናት ሥራችን ከሆን ውሎ አድሯል።
    እናመሰግናለን።
    እነዚህን ሆዳም ፎግረህ ብላ አርቲስቶች ጥሩ ነግረህልኛል።
    ከችግራችን በላይ ያቃጠሉን እነሱ ናቸው።

  5. tamirat says:

    ለዚህ ክፍት የስራ ቦታ ከሰራዊት ሌላ የሚመጥን የለም ለምን መሰለህ እሱ ከፓይለትነት እስከ የእግርኳስ ጨዋታ አሰልጣጘነት ድረስ በማስመሰል ይከረባበትልሀል

  6. በለው! says:

    የወጣውን የትወና ማስታወቂያ በተመለከተ እኔ አመልካች ሁለገብ ኮመዲያን ታማኝ አገልጋይ ባልሆንም ሰሞኑን የማነሳሻ የደሞዝ ጭማሪ በራሱ ለበአሉ ድምቀት ከፍተኛ ተሳትፎ አለው ይሀን የሥራ እድል የሚአገኙ ቢቻል የተበጠበጠ ኩበት በውሃ አቅጥነው አካባቢውን የሚረጩ፣ቢያንስ አባ-ወራ እማ -ወራ ሆነው አካባቢውን በልተው ጠጥተው እንደተጣሉ ተቆጥሮ በጩኸት የሚአዳምቅ፣በእየ አካባቢው እነኳን አደረሳችሁ እያሉ በውሸት ሰላምታ ልብ የሚያደርቁ፣በአነዳነድ መጠጥ ቤቶች የተጋበዙልኝ ድንፋታ የሚያበዙ፣ኢንዲታይላቸው ድህነት እንደቀነሰ ለማረጋገጥ ተሰብሰበው ስለልማት(ኢነቨስትመንት) ስለመሸጥና መግዛት፣ ሰለመጫን እና ማውረድ፣ስለ ቀረጥ ክፍያ እንደበዛባቸው የሚዘላብዱ፤ ኬንያ ጅቡቲ ግብፅ ሄደው ስለጃፓን የሚያወሩ፤ ሁሉ መዘጋጀት አለበት,,, እናት የድሮ ልጆች የበግ ቀንድ ከውሻ እየነጠቁ የራሰጌ መብራት ይሰሩ ነበር የዛሬ…ብለው ሳይጨርሱ ልጅ ቀጥሎ ዛሬ ጊዜ ..የእጅ ሥራ የለም…. የአፍ-ሥራ ነው *የራስጌ መብራት የለም የሳሎኑም በተራ ነው ለዚያውም አባይ ተገድቦ ከኬንያ,ከጅቡቲ,ከሱዳን ከተረፈ ነው። *ዛሬ በግ የለም… ሕዝቡ ሁሉ በግ ሆኗል። ያልበሉ ይብሉ፡ የጠገቡም ያካፍሉ፡ለፅድቅ ከፆሙት በችግር ሳይበሉ ለሚያድሩትም ፈጣሪ አምላክ ይጠብቃቸው፡ አላግባብ ጠግበው ለሚተፉ ግን ይሰራቸው። እግዝዎ ማህርእነ ላለፉት ሃያ ዓመት……. ማህረነ በእንዝዕትነ ማርያም እንበል በፍጥነት ከመጪው ጥፋት አሜን!!!!!!! ከሀገረ ካናዳ

  7. sam says:

    I love it….woye nuro!!!

  8. WEY NURO says:

    ተመስገን ነው እንጂማ ሌላ ምን ሊባል!!! እኔ የምለው አቤ አንድ ያልታየክ ነገር አለ እኮ ለዐብይ ጦም መፈሰኪያ በ25.00 ብር ቴዲ አፍሮን ጥቁር ሰው አልበም መግዛትና መዝናናት፡፡ በቃ ጠላ፣ ድፎ ዳቦ፣ ዶሮ ወጥ፣ ግሩም የገብስ ጠላ፣ ቁርጥ (የስጋ ማለቴ ነው ዘንድሮ ጥጋብ በጥጋብ ስለሆንን እንጀራ ስድስት ቦታ ነው የተቆረጠው) አቤት የምግብ ብዛቱ፡፡ ውይ ከዚህ እንዱን የምትበሉ ካላቹ ስትበሉ እኔን አስታውሱኝ አደራ!! መቼም ኢቲቪ የሚያውቃት ኢትዮጵያ የችጋር ቅርጫት ከሆነች ያው እድሜውን ታውቃላችሑ! ለማንኛውም ጦም ለምትፈቱትም ሆነ ለእንደእኔ አይነቶቹ አዲስ ጦም ለምትጀምሩ መልካም በዓል ይሁንል፡፡ በቴዲ አዲስ ነጠላ ዜማ ቻዎ፡ ‹ደስ የሚል ስቃይ›

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s