ብሎጋችን ላለፈው አንድ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንዳትገባ ታሽጋ ሰንብታ ዛሬ ድጋሚ “ግድየለም ትግባ’ ተብሎ ተፈቅዶላታል። በርካታ ወዳጆቼ ከኢትዮጵያ ሆነው እንዳነበቡኝ በስታስቲክሱ ላይ ባየሁ ግዜም ገቡ ገቡ ገቡ! ብያለሁ።
ባለፈው ግዜ ወዳጃችን ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ዌብሳይት የተዘጋ ግዜ “በህግ አምላክ” ብሎ ሲያበቃ ሲከፈት ደግሞ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑን ተናግሮ ነበር። እኔም ዘጊዎቹንም ከፋቾቹንም ለማመስገን እንደማልወድ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ።
ቀድሞውንም ከወዳጆቼ ጋር የሆድ የሆዴን ልጫወት የከፈትኩትን ብሎግ መዝጋት አግባብ አልነበረም።
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ብሎግን መገደብ የኤሌክትሪክ ሃይል አያመነጭም። እናም እባካችሁን ቀጥሎም አትገድቡን እናውጋበት… እንዋጋ አላልኩም!!!
ውድ የብሎጌ ታዳሚዎች እንግዲህ ባመቻችሁ መስኮት እየገባችሁ እንገናኛለን ማለት ነው!
እንዲያው ቢጨንቃቸው ነው እንደዚ የሚዙትን የሚጥሉትን ያሳጣቸው !!!
ወደዱም ጠሉ እኛ እና አንተን ለማራራቅ የሚደረገው ሴራ መቼም አይሆንም በልልኝ ለነዚያ ጬኒዎች ላስተካክለው ተአይነ ጠባቦቹ ቻይኖች
yelijoch dibibikosh chewata eyetechawotu new. des yilal yehager astedadariwoch honew sayikuraru yihen chewata sichawot
Abe nebse… Liben eko new yemitarisegn!!! I love you man!
abe nebs neger…..yimecheh abo