ጤና ይስጥልጅ ወዳጄ እንዴት አሉልኝ። ጤና ኑሮ ሁሉ አማን ሁሉ ሰላም ነው? የኔ ነገር መቼም ሰሞኑን ሳቀርባቸው የነበሩ አጫጭር ጨዋታዎች ላይ አንድም ግዜ እንኳ ሰላም ሳልልዎት ቀጥታ ወደ ወሬዬ ስገባ “እንዴት ያለው ወሬኛ ወጥቶታል!?” ብለው ሳይታዘቡኝ አይቀሩም። ለዚህ ነው ዛሬም ሌላ ትዝብት ሳይከተለኝ ቀድሜ ሰላምታ ያቀረብኩት። “ምናለ ሁሉ ሰው እንዳተ ከጥፋቱ ቢፀፀት” ይበሉና ያኩሩኝ እንጂ…
እኔ የምልዎ ወዳጄ እኒህ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከዚህ በፊት ባንዲራን “ጨርቅ” ብለውት አስኮርፈውን አልነበር? ከዛ በስንት ግዜው “የባንዲራ ቀን” ብለው አሳውጀው ክብረ በዓል ክብረ በዓል ሲያንበሻብሹን ህዝቡ “በአስራ ምናምን አመታቸውም ቢሆን እንኳን ተፀፀቱ” ብሎ ይቅር ብሏቸው ሲያበቃ፤ አሁን ደግሞ ሰው አያየኝም ብለው ነው መሰል፣ በጎረቤት አገር ኬኒያ ባንዲራውን እንዴት እንዴት እንደዘቀዘቁት ተመለከቱልኝ?
አይዬ… እኚህ ሰውዬ ምን እየነካቸው እንደሆን እንጃ? ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ (አድሮ ቃሪያ ሆኑሳ! ብዬ ብተርትባቸው ደስታዬ ነበር።)
የምር ግን ጠቅላይ ሚኒስትራችን ምን እየነካቸው ነው እንዲህ ህዝባቸው እንደ አይኑ የሚያየውን ነገር ሁላ ማጣጣል እና ማንቋሸሽ የሚቀናቸው። አንዳንድ በነገሩ ብስጭት ያሉ ግለሰቦች ምን እያሉ እንደሚናገሩ ሰምተውልኛል? “አቶ መለስ ልክ እኛን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መጠቅለል የጀመሩ ግዜ እርኩስ መንፈስ ደግሞ እርሳቸውን ጠቅሏሏቸዋል!” እያሉ እየተናገሩቸው እኮ ነው።
ባንዲራ የሀገራችን ሰው በጣም የሚያከብረው ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ነገር ነው። (እኔ ራሴ አሁን “ነገር ነው” ስላልኩ ህዝቤን ይቅርታ ጠይቃለሁ።) የኛ ሰው ሲለምን እንኳ “አረ በባንዲራው…” ብሎ ከጠየቀ “የለኝም” አይባልም። በአዲሱ የባንዲራ አዋጅ ሳይከለከል አይቀርም እንጂ፤ ህዝቡ ባንዲራውን ከመውደዱ የተነሳ በሰርጉ፣ በለቅሶው፣ በቤት ምርቃቱ ሁሉ አይለየውም።
በነገራችን ላይ አዲሱን የባንዲራ አዋጅ ጠንቅቀው ያውቁታል? (ይሄኔ በሆድዎ… በየቀኑ አዳዲስ አዋጅ ይወጣልና ስንቱን አውቀዋለሁ? ብለው ሊጠይቁኝ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ።) የምርም ግን አገራችን በኢኮኖሚ እድገት ብቻ ሳይሆን በአዋአጅ እድገትም ከሌሎች አገራት ጋር ስትነፃፀር ታላቅ እመርታ እያሳየች እኮ ነው። የመያድ አዋጅ፣ የሽበርተኞች አዋጅ፣ የመሬት አዋጅ የባንዲራ አዋጅ… የወዘተ አዋጅ… (ይህንን ልብ ያለ አንድ ወዳጄ ምን አለ መሰልዎ…? ይቺ ሀገር ከዚህ በፊት በምን ነበር የምትተዳደረው…? ብሎ ጠይቆናል። አንድ ችኩል መላሽ ታድያ “በግብርና” ብሎ መልሶለታል።
በሰንደቅ አላማው አዋጅ በርካታ ነገሮች ተካተዋል። አብዛኛዎቹ በኮከቧ ለይ ያጠነጠኑ ሲሆኑ፤ በጥቅሉ ግን “ባንዲራን ያዋረደ ይዋረዳል” አይነት ትርጉም አለው።
እና ታድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አዲሱ አዋጅም ህዝቡም እንዲህ የሚያከብረውን ሰንደቅ እየደጋገሙ ክብሩን ዝቅ ማድረግ ምን ይሉት ፈሊጥ ነው…? ደሞስ ሰሊጥ እንጂ ፈሊት ኤክስፖርት አይደረግ፣ አይለጠለጥ፣ አየሸጥ፣ አይለወጥ…! እውነቴን እኮ ነው በአጉል ፈሊጥ ከህዝብ ጋር ከመቀያየም አራዳ መሆኑ አይሻልም ይላሉ ወዳጄ? ለነገሩ እርድናውስ ከየት ይመጣል? ነገር ግን ቢያንስ ምክር በመስማት አራዳ መሆን ይቻላል።
አረ ጎበዝ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን መክሮ አራዳ የሚያደርጋቸው፤ አንድ ሰው እንዴት ይጠፋል? አስቲ በቅርብ የምታገኟቸው ከሰሙ በምክር ካልሰሙ በአሽሙር ንገሯቸው፤ ለነፍስ ይሆናችኋል።
እውነቴን እኮ ነው፤ መቼም ጆሮ ለባቤቱ ባዳ ነው። የሳቸውንም ጆሮ ደፍረን ባዳ ነው ባንለው እንኳ ቢያንስ ግን “ያኮረፈ ዘመድ” ከመሆን አያመልጥም እና፤ ስለርሳቸው የሚባለውን በሙሉ አጥርቶ የሚሰማላቸው አልመሰለኝም።
ቢሰሙማ ኖሮ ቢያንስ ትንሽ ትንሽ ጥንቃቄ ያደርጉ ነበር። ይህው ባለፈው ሰሞን አያታቸው፤ የአቶ ዜናዊ አባት የሆኑት አቶ አስረስ ለጣልያን በባንዳነት አገልግለዋል። የሚል በፎቶ የተደገፈ መረጃ በፌስ ቡክ ላይ ተለጥፎ ነበር። ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ያሳዩዋቸው ያልተገቡ ባህሪያት ከዛ የተነሳ ነው ብለው የሚጠረጥሩ በርካቶች አስተያየት ሰጪዎች መጥተዋል።
ለምሳሌ ከኤርትራ ጋር ያንን ሁሉ ጦርነት አድርገን ስናበቃ ራሳችን ባሸነፍነው ጦርነት ባድመ ስትሰጥ ዝም ማለታቸው፣ ከዛ በፊትም ቢሆን አሰብን ያህል ወደብ ለመከራከር የሚያስችላቸው በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች እየነበሩዋቸው “ግመል ውሃ አጠጡበት” ብለው እንደዋዛ መተዋቸው፣ “የአክሱም ሀውልት ለደቡብ ምኑ ነው?” ብለው ህዝብ እና ህዝብን ማራራቃቸው፣ ባንዲራን ጨርቅ ነው ማለታቸው፣ አሁን ደግሞ ይለይላችሁ ብለው፤ ባንዲራውን መዘቅዘቃቸው… ይሄንን ሁሉ ከአያታቸው አቶ አሰረስ ጋር እያያዙት አሁንም ሰውዬው ሀገሪቷን ጥምድ አድርገገው ከያዙ ጥቅመኛ ባንዳዎች ጋር እያመሳሰሏቸው ነው። ቀድሞ ያደረጉትን እንኳ ይሁን ጉርምስናም ጉልምስናም ይዟቸው ነበር ብለን እናስብ…!
ይሄ የሆነው ግን አሁን በቅርቡ ነው። ኬኒያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ እና የኛይቱ ኢትዮጵያ ላሙ የተባለ የጋራ ወደብ ለመገንባት ኬኒያ ላይ ተገናኝተው ነበር። እንግዲህ በዚህ ዝግጅት ላይ ነበር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክቡሩን ባንዲራ (ለዛውም ኮከብ ያለበትን… ምን ያስቅዎታል?) እውነቴን ነውኮ አዲሱ የባንዲራ አዋጅ “ኮከብ የሌለው ባንዲራ መያዝ ነውር ነው” ብሎናል…! በርግጥ በዛው ልክ ባንዲራውን መዘቅዘቅም ነውር ነው። እርሳቸው ግን ዘቅዝቀው ይዘውታል።
እስከ ዛሬ ድረስ እንደምናውቀው ባንዲራ የሚዘቀዘቀው ወይም የሚቃጠለውና የሚቀደደው በሀገሩ መንግስት ላይ ተቃውሞን ለመግፅ ነበር። ታድያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡን ነው የራሳቸውን መንግስት ነው የሚቃወሙት…!?
ልቦና ይስጣቸው ወይም ሌላ የሚወዱት ሀገር እና የሚወዱት ባንዲራ ይስጣቸው ብዬ በአንድ እግሬ ቆሜ እፀልያለሁ! ያግዙኝ ወዳጄ!
በመጨረሻም
“ይሄን ጉድ አየህው?” ብሎ ፎቶግራፉን የላከልኝን የልብ ወዳጄ ሲሳይን አመስግኑልኝ።
አይ አቤ ሰው መስለውሃል፡፡ እነርሱ ኮከቡ ካልተዘቀዘቀ ምን ጨነቃቸው ብለህ ነው!
hahahaha Abebe funny reply
waw this is just another bomb shell writing!!
keep up bro!!!
የሌላ ኃገር ባንዲራ ሊሆን ይችላል፧ ምናልባት ተጋባዥ መሪ ሆነው።
አዋጁ ባንዲራን የገለበጠ ራሱ ይገለበጣል። አይልም እንዴ እንደገለበጡት ይገልበጡ!!!
እስኪ መጀመርያ ለዚች አገር መለስ ከሰራው 1% ቱ እንኳን ለመስራት ሞክር ከዛ አፍህን ክፈት እፍህን ስትከፍት ደግሞ ጭንቅላትህ ወለል ብሎ መታየቱ አትዘንጋ ምን ይመስላል ልጄን በምን እንደማስፈራራት ታወቃለህ ?ያንተን ምስል(ፎቶ)በማሳየት ነው
Yosef ,this dude has never done any good thing except filling urs and ur friends’ big fuckin tummy,u are pig man!u should ashamed what u have said as an Ethiopian (if u are).Hodam, ante ferifari belteh seldelah dont think everybody is like u, unfortunately Most Ethiopians need their dignity and self respect!!!!!Finally i would like to tell u that u r Nonsense.
antem lij aleh?……ebetim til yiwelidal alu
I think the Kenyans should have asked him whose Flag he is carrying, in fact, they may have. Who know! Ehe asdabe aheya!
አይ ዮሴፍ፣
አሁን ማይሙት መለስ የሰራውን ስራ ያንተ የምታስፈራራት ልጅህ እንኳን አትሰራውም ብለህ ነው?
ቱልቱላ
meles sorry pm what did he have done for us nothing we are who we are now just by natural evolutionary process and and evolution is not the result or contribution of any one. there so many people who consider the PM is extra ordinary yes he is but EVIL extra ordinary which is of no use. @ yousef pleas when u compare two persons make comparability test first. don’t be stupid by comparing a journalist with PM who are totally in too different place to contribute for the country. try to act a civilized man don’t always follow ur emotions. i am just trying to…. and the way u punish ur kid is it is better if u show her ur comment honestly she will be scared 😦
Nurochen kulkul yetezekezekew anesena bandirachenem tezekezeke? Yihuna,
oh yesef ligih endante chinklatua mesrat kakome koytual ,balege nat nat malet new masferarya tifeligalech lenegeru keahiya lig min yitebekal yaw endante ahya enji
ማስፈራራት ምና ምን አይገባኝም ለመሆኑ እውነት ሀገራችን ጠቅላላይ ሚኒስቴር አላት? ለሆዱ ያደረ ብቻ በአገራችን ላይ እንጀራና ሽሮ መብላት እንደ ብርቅ እየተቆጠረ ያለበት ደሃና ሀብታም ልዩነቱ የሰፋበት ሀገር ላይ አጉል ለባንዳ ተቆርቋሪ ለመሆኑ የምናደርገውን እናውቃለን እናቶቻችን በተጨነቁበት ሰዓት ዛሬም የሌለ ካድሬ እኛ ማንም መራን ማንም ሀገሪቷ ላይ ስደት ፣ ረሀብና ሰቆቃ መጥፋት አለበት፡፡ እኔማ አንዳንዴ ዕድገት ዕድገት ሲባል ከዚ ሌላ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች እንዴ እኛ የማናውቃት አብሶ ዕሮብ ዕሮብ የሚቀርበው የህትመት ዳሰሳ ሆዳሞች ሁሉ ቀን ይፋረደን መቼም ሕግ በእኛ ቤት አናውቅም ብለዋውል ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ይሁን እግዚአብሔር አገራችንን ይባርካት፡፡
[…] ♦ March 24, 2012 ♦ 13 […]
[…] abetokichaw ♦ March 24, 2012 ♦ 13 Comments […]
ሰንደቅ ዓላማውን የዘቀዘቁት መለስ የራሳችንን ወደብ ሰጥተው የሰው ሀገር ወደብ ሲቀላውጡ ነው ወደብ ሸቀጥ ነው በገንዘብህ የምትገዛው፣ከፈለጉ ግመላቸውን ውሀ ያጠጡበት ወዘተ… ያልቀባጠሩት የለም ነበር ተሳዳቢው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ለሳቂታውፓርላማ፣ለአሳርኛው ህዝባችን።አሁን ደግሞ አማራጭ ወደብ ፍለጋ፣ላይታች ሲማስኑ እያየን ነው፣ለምን ያኔ እንዲያ ብለው ነበር የሚላቸው የለም ተጠያቂነታቸው ለማን መሆኑን የተደነገገ ማሰሪያ ህግም የለም።ካሻቸው ፓርላማውን(ወጉ አይቀር መቼም ፓርላማ ልበለው)የዐይናቸው ቀለም ከደበራቸው መበተን ይችላሉ፣በህግ የተፈቀደ አንባገነንነት ያላት ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ትመስለኛለች።
ወደብ ወሳኝ ነገር አለመሆኑን የነገረን መለስ ዛሬ ደግሞ ወደብ ፍለጋ ኬንያ ድረስ ሲኳትን እያየን ነው።ዜናውን ያበሰረን ኢቲቪ ነበርወደብ አልባ ሆኖ ካለችግር መኖር እንደሚቻል የነገረንም ኢቲቪ ነበር፣ሰውዬውም የመረጃ ማዕከሉም አልተቀየሩም።በኬንያ የሚገነባው ወደብ ለኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ለአዲሲቷ ጎጆ ወጪ ደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ መሆንና ከወደቡ ጋር የነዳጅ ማጣሪያ አብሮ እንደሚሰራ ኢቲቪ አበሰረን፣የራሳችንን ወደብ፣የነዳጅ ማጣሪያ፣ባህር ሀይል አሳልፈን ለምን እንሰጣለን?ተብለው ሲጠየቁ ለሰላም ብለው መሆኑና ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ጦርነት ናፍቂዎች ናቸው ሲሉን የነበሩት ሰውዬ ዛሬ ስለ ሌላ ሀገር ላይ ስለሚሰራ ወደብ፣የነዳጅ ማጣሪያ፣ ጅቡቲ ላይ ስላለን የባህር ሃይል ጠቃሚነት ይለፍፉብናል።ሰላም ለማምጣት የተባለው የኤርትራ ጉዳይም ከሰባት ዐመት በላይ ሊዘልቅ አልቻለም፣ወደቡም ሰላሙም የለም ግን ማን ይጠይቅ?
አገሪቷንም ዘቅዝቋታል ለኔ ቅምም አይለኝም የእሳቸው ነገር ይሔው ከመዘቅዘቅም አልፎ ዠቅዠቅዠቅ እያደረጋት አይደል
ኣይ አቤ!
የዌብ ሳይት ጀግና ብቻ ሆነህ ቀረህ፤ fail finder
ውሻው ይጮሀል፣ ግመሉ ግን መንገዱ ይቀጥላል ነው ያሉት
እናንተ ስትጮኹ ሰውየው ግን ስራቸውን እየሰሩ ነው፤